እንዲህ ብለው ነበር!

“ለአገራቸው የማዕዘን ድንጋይ፤ የትውልድ ፋና ወጊ የሆኑ ጸሐፍት አባባሎችን፤ ቀነጫጭቤ ልኬያለሁና ለወግኖቻችን እንደሚሆን አርጋችሁ አቅርቡት” በማለት ይህንን ለኢ.ኤም.ኤፍ. የላከልን አሥራደው (ከፈረንሳይ) ነው።

*****************

ሰው የሚመከረው፣ አንድም ከፊደል፣ አንድም ከመከራ ነው ::

አንድ ቃል ከፊደል ጥበብ፤

አንድ ቃል ከመከራ መዝገብ፤

አንድም በሳር «ሀ» ብሎ ፤

አንድም በአሳር «ዋ» ብሎ::

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

**************

እድሜዬን በሙሉ፣ አልጋ ላይ ታስሬ፤

ታምሜ ስማቅቅ፣ ስሰቃይ ኖሬ፤

አሳሬን ጨርሼ፣ ይኸው ዛሬ ገና፤

እንቅልፌን አግኝቼ፣ ማረፌ ነውና፤

የምትሄዱ በዚህ፣ በመቃብር ቦታ፤

እንዳትቀሰቅሱኝ፣ እለፉ በርጋታ ::

አንጋፋው ደራሲ ከበደ ሚካአኤል

************

አጥንቱን ልቅበረው፣ መቃብር ቆፍሬ…

ጎበናን ከሸዋ ..አሉላን ከትግሬ…

አገሬ ተባብራ፣ ካረገጠች እርካብ …

ነገሯ ሁሉ ..የእንቧይ ካብ ..የእንቧይ ካብ

ከመርስኤ ሃዘን ግጥሞች

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 17, 2011. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.