እንኳን ደስ ያለሽ! (ጌታቸው አበራ)

(ቀደም ሲል የዓለም-አቀፍ ሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ በቅርቡ ደግሞ የዩኔስኮን የነጻ ፕሬስ ሽልማት ላገኘችው ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት አለሙ መታሰቢያ)

ለነጻነቴ ስትሟገቺ ለመከራ የተዳረግሽ እህቴ ሆይ!
“ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” ክቡር ቃል ለምድር ለሰማይ።

… እንኳን ደስ ያለሽ!

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to እንኳን ደስ ያለሽ! (ጌታቸው አበራ)

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  April 29, 2013 at 4:11 AM

  እኔም እንኳን ደስ አለሽ ለማለት ከዚህ በፊት በልደትሽ ላይ የቋጨዃትን ግጥም”ጝጥም”አድርጌ አቀረብኳት::
  /////…ተሻለኝ ሕመሙ።///////
  ድፍረትሽ ውስጤ ነው አይነጥፍም ቀለሙ፤
  የልቤን ሲያውቅልኝ ተሻለኝ ሕመሙ።
  ባንቺ ልሳን ያንን”የቅዱስ”ለምድ ለባሽ፤
  ቆዳውን የሚያወልቅ ቀን አልፎ ሲመሻሽ፤
  ቀልቡን ገፈፍሽና ቆሞ ባደባባይ፤
  ባንዳነቱን ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲያይ፤
  በክርስቶስ ንግዱ ሲገባ እንደሸቀጥ፤
  በክት-ሕሊናው ደፍሮ እንደይሁዳ ሊሸጥ፤
  ፓስተር ቆብ ጀቡኖ…
  ሽማግሌን ሆኖ፤
  ድ-ብቅ ሹ-ክክ ብሎ…
  የሚያስታርቅ መስሎ፤
  ፈገግ ብሎ ሲጠጋ:-ያ ምላሱን ሲስል፤
  “ቀንዱን!!!” አልሽው እቱ!
  አይጥ እስኪመስል።
  ርዕዮት ዓለሙ:-
  በድፍረትሽ ብቻ ተሻለኝ ሕመሙ::
  እንደዚህ ነው ትግል ጠላትን መዋጋት፤
  በሰላም ሥም ሁሌ ባርነት ከመጋት።
  እሱማ ሠይጣን ነው ምኑ ነው ዳንኤል፤
  ቀን ቀን ከሰው ውሎ ማታ ከጋንኤል፤
  የደም ፅዋ ጠጪ ከጉጅሌ ጋራ፤
  ፀሐይ የሞቀው ነው እማኝም አልጠራ።
  ምን ይዞ መሰለሽ ከእነሱ የገጠመው፤
  የሚጠጡት ደም ነው፤ሌላ ምን ሊጥመው?
  አለዚያማ ጎበዝ በእነዚያ ሁሉ ዓመት፤
  “ሲገድሉ አላየሁም” ብሎ ይምላል በዕውነት???
  መቼ ይምላል አሁን ሐቁን ልቡ ያውቃል፤
  ያኔ እንደጓጎለ በደሙ ይታነቃል።
  እናም የዳንኤል ሠይጣናዊ ሕመም፤
  አባብሎ ማስገደል ሆኗል በቃል ቅመም።
  ይሄን ያወቅሽልኝ ርዕዮት ዓለሙ:-
  በድፍረትሽ ብቻ ተሻለኝ ሕመሙ::
  አይነጥፍም ቀለሙ:-
  ርዕዮት ዓለሙ!!!

  መድኅኔዓለም ቀላሉን አድርጎ ከሕመምሽ ይፈውሽ ዘንድ በፀሎት አልረሳሽም::

  በልደትሽ ሰበብ ኢትዮጵያዊ የደፋር ወኔሽን ፓስተር ዳንኤል ላይ ላስከነዳሽው ውድ የትግል እህቴ ርዕዮት ዓለሙ የተጻፈ።