እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር (ሄኖክ የሺጥላ)

የበደሌ ቢራ ፋብሪካ ከ ኣዲስ ኣበባ 483 ኪ.ሜ  ርቀት ላይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ኢሉ-ኣባ-ቦራ ( Eloo The father of  Holstein  Friesian) ኢልባቡርከተማ በሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ስኩውር ሜትር ይዞታ ላይ ስራውን እንደ ኣውሮጳውያን ኣቆጣጠር በ 1993  ማከናወን የጀመረ ትልቅ የቢራ ማምረቻ ድርጅትነው።

ኢሊባቡር መልካም ምድራዊ ኣቀማመጡም ሆነ ምድራዊ ልምላሜው፥ እንደ በቆሎ ፤ ገብስ፤ ጤፍ፤ የቅባት እሎች፤ ማር፤ ከነ ቦራ ደሞ ወተት፤ ቅቤ እና ወዘተየሚዘራባት፤ የሚታጨድባት፤ የሚቆረጥባት፤ የሚታለብባት ሃገር እንድትሆን ኣድርጉዋታል።

ኢሊባቡርን የጽሁፌ መንደርደሪያ ኣደረኩ እንጂ ዋናው ነጥቤ እሱ ኣይደለም። ዛሬ መናገ ወይም መጻፍ የፈለኩት ቴዲ ኣፍሮ በቅርቡ በመላው ኢትዮጵያ የሙዚቃዝግጅቱን እንዲያሳይ ወኪል የሆነውን የበደሌ ቢራን ያለመጠጣት ኣድማ ( boycotting)  በመላው ኢትዮጵያ ይደረግ ዘንድ ኣንዳንድ ግለሰቦች የጀመሩትን ነገርሰምቼ፤ ለምን በደሌን፤ ለምን ቴድን የሚል ጥያቄ ለሚጠይቁ፤ መልስ የሚመስለኝን ለመተየብ፤ ከተቻለም ለማሳየት መመኮር በመሻቴ ነው ።

ቴዲ ኣፍሮ በቅርቡ በጋዜጣ ላይ ስለ ኣድዋ ድል በሰጠው ኣስተያየት የተቆጡ፤ የተቀየሙ ግለሰቦች፤ ቴዲ ኣፍሮ ጥቁር ሰው ብሎ ንጉስ ሚኒሊክን፤ ከዛም በላይየኣድዋ ድልን በመዘከሩ የተበሳጩ የህብረተሰብ ኣካሎች፤ ቴዲ ኣፍሮ ከዚህ ቀደም ጃ ያስተሰርያል ብሎ በመዝፈኑ ቂም የቁዋጠሩ ሰዎች፤ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን በ 1936  የኢጣልያንን የተለከለ  የኬሚካል መሳሪያ መጠቀምን በመቃወማቸው፤ ኢትዮጵያን የ ዩናትድ ኔሽን ኣባል በማድረጋቸው፤ ቅራኔዎችን ኣብርደው ያፍሪካን ህብረት በመመስረታቸው፤ ለነዚህ ጉልህ ኣስተዋጾዎቻቸው በመዝፈኑ፤ ለነዚህ ለተጠቀሱት መልካም ስራቸው መታሰቢያ የጭንቅላቱ ውጤትየሆነውን ምዚቃ በማበርከቱ፤ ቴዲ ኣፍሮ ፤ ኣቀንቃኝ ና ኣዝማሪ ፤ ገጣሚና ሰኣሊ፤ ሃያሲና ደራሲ፤ ጸሃፊ ተውኔቱና ብላታው፤ ኣፉን በለጎመበት ዘመን፤ በብእሩየታሪክ ጋሻ፤ በግጥሙ ለቆሰለ ታሪክ ማገገሚያ፤ በዘፈኖቹ ( ከ ማሊ ሱፊዎች ባልተናነሰ መልኩ) የነብስን ክር እየተጫነ ያላስለቀሰው፤ ያላስተከዘው፤ ሰው እንደሌለየገባቸው ሰዎች፤ በይበልጥም የኣድዋ ድል፤ የጥቁር ኣንበሳዎች ድል መሆኑን ያሳየበት በመሆኑ እና ይህም የሚያማቸው ሰዎች፤ ዛሬ በደሌ ቢራ ቴዲ ኣፍሮንስፖንሰር ስላደረገ፤ በደሌ ቢራን  ያለመጠጣት ኣድማ ጠርተዋል። ኣሁን ቴዲ ኣፍሮን ኣብዶ በረንዳ ( የጫት ማከፋፈያ በረንዳ ነው) ቢሆን ስፖንሰር ያረገው ምን ሊሉ ነበር።። ባረገው እና የተከታዮቻቸውን መልስ ባየን።  ኣንድ ጊዜ ቆይ ጠብቁኝ ሳቄ መጣብኝ ያለው ተናጋሪ ማን ነበር።

ኣዲሱ የቴዲ ኣፍሮ ኣልበም (ጥቁር ሰው) የብዙዎቹን እትዮጵያዊያኖች ድምጽ ያስገኘለትን ያህል፤ ንጉስ ሚኒሊክ በድሎናል፤ ጡታችንን ቆርጦዋል፤ ወዘተ ወዘተርፈለሚሉት ደሞ፤ ከሚኒሊክ መፈጠር፤ ከታሪክ ኣንቅጽነቱና ኣኩሪ ገድሉ ጋር የጀመሩትን  እጹብ ጸብ ውሃ የሚደፋበት በመሆኑ፤ ጠላት ሊያፈራበት እንደሚችልመገመት ብዙም ኣይዳግትም። እናም ‘ነዚህ ሰዎች ቀደም ብዬ እንደ ጠቀስኩት፤ በደሌ ቢራን ያለመጠጣት ኣድማ እናድርግ እያሉ ነው። ልክ ናቸው፤ ህዝብበጥላቻም በቢራም ሰክሮ እንዴት ይሆናል፤ ባንዱ ብቻ ይበቃልና።

በነገራችን ላይ ይህንን ኣድማ ለማስመታት ከሚራወጡት እና ከሚሯሯጡት ሰዎች መሃከል ኣንዱ ጃዋር መሀመድ መሆኑን ሰምቼ ኣፍሬ ጥፍሬ ውስጥ ልገባነበር። ባንድ ወቅት ይሄ ወጣት ፖለቲከኛ ስለ ራሱ ሲናገር  “እኔ እናቴ መንዜና የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነች ኣባቴ ደሞ ኦሮሞና ሙስሊም ነው ፤ ታዲያ ከኔበላይ ኢትፖጵያዊነትን የሚወክል ምንነት ኣለ ወይ” ብሎ ነበር። መልሱ ሊሆን ይሚችለው ጃዋርዬ በውነትም የለም፤ እንዳንተው ኣቶ መለስም እኮ የተላቀቀነገርን ማጣበቅ የሚችል (ኡሁ የሆነ) (UHU…glue) ደም ነበራቸው፤ ግን ደሙ ሳይሆን የደሙ ባህሪ ነው ወሳኙ ነገር። የተሸከምነው ደም  ሳይሆን  በውስጣችንያፋፋነው ስብዕና ነው ማንነት ፤  ማንነት ስራ ነው እንጂ ኣንተ እንዳልከው የ-ኢ-ተጎራባች ዘር ደም ውህደት (ኬሚስትሪ ውጤት ኣይደለም)፤ ክርስቶስ ( ኤሳው… ኣለይሁ ሰላም) በ-በረት ተወለደ ብለን እናምናለን፤  ግን እንደ ሰብኣዊ ፍጡር በ-በረት መወለዱ ሳይሆን ሰው ሆኖ ሲኖር ያደረገውን ነገር ነው የምናስበው፤ ስለ ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) ኣንድ ሙስሊም ሲያስብ ስለ ዘራቸው ሳይሆን ስለ ስራቸው ነው የሚያስበው ብዬ ኣስባለሁ ።  ባንድ ወቅት ይሄውሰው፤ ፹ ከ ፻ የሚሆነው የሃገሬ እስላም ኦሮሞ ነው፤ እናም የእሮሞ ህዝብን ኢምፓወር ማድረግ፤ እስልምናን ኢምፓወር እንደማረግ ነው ኣለን፤ለመስማት ኣይደል የተፈጠርነው እናም ሰማነው፤ ባሜጃ ኣለን ዝም ብለን  ሰማነው፤ ቀጥሎም ኢትዮጵያ ኣውቶ ኦፍ ኦሮሚያ  ኣለን  እሱንም ሰማነው። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ኣውት ኣፍ ኦሮሚያን ወደ ፈርንጅኛ ስቀዳው ( the child give birth of her mother) ኣይመስላችሁም ? ለመተርጎም የተገደድኩት የመጀመሪያው ራሱ እንግሊዘኛ መሆኑን ስለ- ተጠራጠርኩ ነው። ለነገሩ ስታንፈርድና ኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ እኮ መፈክር ኣያስተምሩም።

እና ዛሬ  በደሌ መጣ እና ወንድሜ ጃዋር  ሰማኒያ ከመቶ ካለው ሃሳብ ጋ ግንባር ለግንባር ተጋጨ (head on collusion) እናም  ሁለት የሚጋጩ ነገሮችንእንግዲህ እናስተውላልን።

፩)  መቼም ፹ ከመቶው  እስላም ኦሮሞ ነው ብለኽን፤ ኣንተም በዘር ብቻ ሳይሆን በእምነትም ጭምር ጠበኽ፤ ኣልገባኝም ታዲያ እንዴት ነው፤ እነማን ቦይ ኮት እንዲያረጉልኽ ነው ጥሪውን ያቀረብከው፤ ፳ ፐርሰንቱ እስላም ያልሆነው ኦሮሞ ? ደሞ ከ ፹ ከመቶ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ውስጥም ቢሆን ኣዲስ የበደሌ ኣድመናኛ ማግኘት ይቸግራል ብዬ ኣስባለሁ፤ ምክኒያቱም እነሱ ላንተ ሲሉ ሳይሆኑ ለዲናቸው ሲሉ ድሮም እንዲህ ኣይነቱን ነገር ይነኩት ነበር ብዬ ኣላስብም፤ በፍጽም ኣያደርጉትም፤ ታዲያ የማይጠጡ ሰዎችን ነው ኣድማ የጠራነው፤  ወይስ ሙሉ የኢትዮጵያዊነት ማሳያ ምሳሌ እንድትሆን ያደረገችህ የመንዜዋ እናትህን ዘመዶች፤  እኔ ኣላውቅም ፈራሁ  ሄኖክ ነው ያለኝ የልጅነት ጉዋደኛዬ፤ ባንድ ትልቅ የውሃ ጉድጉዋድ ውስጥ እንሹለክ ስለው።  እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር።

ዛሬ ጀርመን ያላትን ቅርጽ እንድትጠብቅ ወይም እንዲኖራት ያደረገው ኦቶ ቮን ቢስ ማርክ፤ የደም ትግል ውጤት ነው። ታዲያ ጀርመኖች በ ቢስ ማርክ ተናደው ፒሊሲነርን ( የጀርመን ታዋቂ ቢራ ነው) ቦይ ኮት እናርግ ኣላሉሉም። በፈረንሳይ እንዲህ የሚባል ታሪክ ኣለ፤ በኣሜሪካም፤  ኣረ ሆመር በጥንታዊያኖቹ የግሪክ ዘመን ስለነበረው ጦርነትም ጽፎዋል፤ ስለ ስርኣቱ፤ ስለ ኣገማምኖን እና የወንድሙ መንግስት፤ ስለ ሄለናዊው ስርኣት፤ ከዚያም በሁዋላ እነ ዳንቴ ስለ ጻፉት ስለ ዲቫይን ኮሜዲ፤ ፍሬድሪክ ዊልሃልም ኒቺ ስለተራቀቀበት የማህበረሰብ ስነ ልቦና፤ እነ ኣልበርት ካሙ ስለጻፉለት የፈረንሳይ ማህበረስብ እና በየስራቶቹ ውስጥ ስለ ነበርው ፍዳ፤ እነ ልዮ ቶሎስቶይ በሰላ ብእራቸው ስለዘገቡት የሩሲያ የጭቆና ቦለቲካ፤ እነ ፓብሎ ፒካሶ ጉሬንሽያ ብለው ስለገለጹት የስፔን ከተማ ስለ ስንቱ ለዚህ ለወጣቱ ፖለቲከኛ እንንገረው  እስኪ ባክህ ጁሃርዬ ገረፍ ገረፍ ኣርጋቸው (በቃ እንደውም ለዚህ ክረምት  ለፐርሰናል ዲቨሎፕመንት…ትመለከታቸው ዘንድ እጠይቅ፤ሃለሁ (ማሳሰቢያ በኣብዛኛው በኣማራ ጻሀፊ ኣይደልም የተጻፉት ቢሆኑም ደሞ ኣነተ ኣምሳ ፐርሰንት ኣማራ ኣይደለህ እንዴ፤ የምሬን እኮ ነው)

በታሪክ ላይ ጥላሸት መቀባት በፍጹም ለማንም ኣይሳካም፤ ወደድንም ጠላንም፤ ጠቅልለን የምንጎርሰውን እንጀራ የፈጠሩት ኣባቶቻችን ናቸው፤ ለሆዳችን ያለን ቅርበት ለታሪካችንም ይኑረን። ቴዲ እንዳለው ክፉውን በክፉ ለመመለስ ማሰብ ሌላ ክፉነት ነው። ሁለቱ ደሞች እንደ ደም ይሰሩ፤ ያስቡ ዘንድ ሰው እንሁን።

( Henoke Yeshetlla)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 28, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

4 Responses to እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር (ሄኖክ የሺጥላ)

 1. Pingback: እኔ ኣላውቅም ፈራሁ ጃዋር (ሄኖክ የሺጥላ) - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com

 2. Andualem

  December 28, 2013 at 11:04 PM

  leave him .Jouhar is infentile

 3. samson Ali

  December 30, 2013 at 11:05 AM

  Yehe leje Sente ametu new? Tebarek !

 4. በለው!

  December 30, 2013 at 1:51 PM

  “ነፃ እስክትወጡ በቋንቋና የብሔር ፌደራሊዝም ራዕይ ቀውጡ!(ራዕዩን እናሳካላን የሻቢያህወአት ግራ ክንፍ “ከሙስሊም ኦሮሞ ፈረስት የሜንጫ አብዮተኞች የተሰጠ መግለጫ!”
  **********************************************
  ምን አለ የአሸባሪ ህጉ ምን አለ…የእኛ ናቸው አትንኳቸው ሕግመንግስታዊ ጥበቃ ይደረግላቸው አለ። የአንድን ሀገር የኢኮኖሚ ወይንም የህዝብን ማንነት የሚፃረር ሁሉ ሕጋዊ ጥበቃ ሊደረግልት ይህንንም በሕዝቦች መካከል የግጭትና አመፅን የሚያነሳሳ ወይንም ዕቅድ የሚያወጣ ሁሉ በህግ ተጠቂ መሆን ነበረበት..”ተማክረው የፈሱት ፈስ አይሸትምና” የኢህአዴግ ሹማምንት ደስታቸውን እየገለፁ ነው።
  በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ ፶፭/፩ መሠረት የታወጀ፡
  የአዋጁ አስፈላጊነት ሕዝቦች በሰላም በነፃነትና በተረጋጋ ሁኔታ ለመኖር አላቸው መበት ከሽብርተንነት አደጋ ሁልጊዜ መጠበቅ አለበት በመሆኑ፡ ሽብርተኝነት ለተያያዝነው የዲሞክራሲና ልማት ግንባታ ፀር በመሆኑና ሕገመንግስታዊ ሥርዓታችንን በማናጋት የህዝባችንን ደህንንትና ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ፡
  **ከአሜሪካ ከእንግሊዝ ከተባበሩት መንግስታት ማኅበር አባላት ነጥብ ሳይቀር የተኮረጀ ድንቅ ሕግ እየተባለ በፓርላማና በሚዲያ ላይ የተፃፈን ኮርጀው እያነበቡ በኅብረት የሚቆሉበት የአሸባሪዎች ሕግ ምን ይላል?(አስኮራጅ ሀገሮች እነደእኛ በብሔርና ቋንቋ የተከለሉ ፌዴራላዊ ሥርዓት አላቸውን?የውጭ ጠላትን ለመከላከል ያወጡት ሕግ? ወይንስ የውስጥ የሥልጣን ኅይላቸውንና የኢኮኖሚ ምንጫቸውን ለማስከበር ያወጡት ሕግ?የእኛ አሸባሪዎች እንዴት ብዕር ይዘው የሚፅፉ ጋዜጠኞችን ሲወነጅል ሲያስገርፍ ሲያሰድድ የውርስ ንብረት ሲነጥቅ፣በግለሰብ ተሰራን ቤት ሲወረስ፣ ዕድሜ ልክ ሲያስር፣ ሰይፍ ሆኖ ሲነሳ ፣(ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን! እየተባለ ሲያስደነፋና ጠረጴዛ ሲያስደበድብ እጅ ሲያወራጭ፡አድርባይ ምሁር ሲሞላፈጥ ይታያል ለጭፈራና ለቁጥር መሙሊያ የሚንቆለጳጰሱት “ብሔር ብሄረሰቦች” እዚህ ሕግ ላይ የሉም ህዝቦቹ ብቻ ተጽፈዋል። ምክንያቱም በዘርና በቋንቋ የተቧደነና አንዱ በአንዱ ላይ አመጽ እያስነሳ የሚኖር ሕገመንግስታዊ ሥርዓትና መንግስታዊ የወሮ በላ ቡድን ስለሆነ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ አሸባሪ ይሆናሉ!!ለዚህም ሻቢያህወአት (ሻቢያንም) የቀጠናው አታራማሽ እንጂ አሰባሪ አላላም፡ ብሔር ብሔረሰቦች የሚያነሱትንም የሜንጫ አብዮት እነደ ሥልጣን ማስጠበቂያ እንጂ እንደወንጀል (ሽብር)አይቆጥርም። ለመሆኑ በብሔርና ቋንቋ በክልል ተቧድኖ የማይማሰል ሠፈርና መንደር አለን? ከነጻ አውጭውና ነጻ አግቢው ሽቢያህወአት አድዋ>>መቀሌ አዲግራይት..አጋሜ..የላይ ባድሜ የታች ባድሜ…የሸዋ…የሃረር..የወለጋ ኦሮሞ እና ሌሎችም!(እቂጡ ላይ ቁስል ያለው ውሻ እንደልቡ አይጮህም ማለት ይህ ነው።ሻቢያህወአት/ኦነግ/ኦብነግ ሙስሊም ኦሮሞ ፈርስት! አንድ አካል ሀለት አምሳል ያላቸው የሀገርና ሕዝብ አጥፊ ባንዳ ቅጥረኛ መሰሪ ናቸው።

  ” የፓለቲካ ተንታኝ የሰላም ትግል በታኝ ሜንጫ ስለው የህወአት መሥራችን ሊ/መንበር የሙስሊም ኮሚኒቲ አባላትን በተለያዩ ሀገራትና አህጉር የቁርሾና በቀል ፣የሀገርን ኢኮኖሚና መከላከያውን የመቆጣጠር ስልት የሚነድፉ፣ በሚዲያ ወጥተው የሕዝቦች ግጭት አፈጣጠር የፖለቲካዊ አካሄድ ትንተና የሚሰጡ፣ የሚያሰጡ፣የሚያበረታቱ፣ በአዳራሽ ሰብስበው ሲያስጨበጭቡና መፈክር ሲያሰሙ ለሽብርና ለፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ የገቢ ምንጭና የኢህአዴግና ሻቢያ የውስጥ ለውስጥ መሸጋጋሪያ ሚስጠር አቀባይ ሆኖ የሚያገለግለውን “የኦሮሞ ዝምታ” “የከይሲው ማስታወሻ” ፎጋሪ ደራሲ እያሞካሹ በሚዲያ የሚደግፉ ባንዳዎች ፍም ሲገልጡ፣ ካድሬዎች ከገዢው መንግስት ውስጥ እሳት ይዘው ሻቢያህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ በቡድን(በህብረት)በጋዝ ለማጥፋት ተነስተዋል!? ውስጡን ያልፈተሸና ያላጠራ ቡድን(መንግስት)በሌላው ንፁሐን ዜጎች ላይ በብሔራቸው ማንነት ብቻ ጣቱን ቢቀስር ይህ በእራሱ የአሸባሪ ተባባሪ ደባቂ አሰልጣኝና ሙሉ ደጋፊ እራሱ ኢህአዴግ ነው ማለት አደለምን!?

  ጥር፪ሺ፩ ዓ.ም “ሽብርተኛ ድርጅት ማለት፡ ፪(ትርጓሜ)
  (ሀ) የሽብርተኝነት ድርጊትን የመፈፀም ዓላማ ያለው ወይም የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈፀም አቀ የተዘጋጀ፣ያስፈፀመ የፈፀመ ወይም እንዲፈፀም በማናቸውም ሁኔታ የረዳ ወይም ያነሳሳ ከሁለት ያላነሰ አባላትን የያዘ ቡድን ማህበር ወይም ድርጅት ነው
  (ለ)በዚህ አዋጅ መሠረት በሽብርተኝነት ተሰየመ ድርጅት ማለት ነው።

  ፫.የሽብርተኝነት ድርጊቶች፡

  ፩. ማንም ሰው የፖለቲካ የሀይማኖታዊ ወያም አይዶሎጂያዊ ዓላማን ለማራመድ ሆን ብሎ፤
  (ሀ) መንግስትን በማስገደድ ወይም በማስፈራራት፤* (ለ)ሕዝብን ወይም የአንድን ህዝብ ክፍል በማስፈራራት ወይም፤* (ሐ)የሀገርን መሠራታዊ የፖለቲካዊ የህገመንግስታዊ የኢኮኖሚያዊወይም ማህበራዊ ተቋማትን በማናጋት ወይም በማፍረስ

  ፭.ለሽብርተኝነት ድጋፍ መስጠት. (ለ) የሙያ የልምድ ሞራል ምክር ወይም ድጋፍ የሰጠ እንደሆነ** (መ) የገንዘብ ወይም የፋይናንስ ወይም ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው አገልግሎቶችን ያቀረበ ወይም የሰጠ እንደሆነ፤ (ረ)ማናቸውም ዓይነት ውልጠና ወይም መግለጫ የሰጠ እንደሆነ** (ከ፲ ኣመት እስከ ፳፭ ዓመት በሚደርስ ፅኑ እሥራት ይቀጣል።)

  ፮.ሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ ስለመሳተፍ

  ፩.የስብርተኛ ድርጊቶችን ለመፈፅም ሰው የመለመለ በድርጅቱ በማናቸውም መልኩ የተሳተፈ እንደሆነ(እንደተሳትፎው ደረጃውከ፭ዓመት እስከ ፳ዓመት በሚደርስ ፅኑ እሥራት ይቀጣል።
  ፪.በሽብርተኛ ድርጅት ውስት በአመራርነት ወይም በውሳኔ ሰጭነት የሰራ (ከ፳ዓመት አስከ ዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ይቀጣል)
  “ተስፋዬ ገብረእባብ ድርጅት እና የጃዋር መሀመድን አሸባሪ ቡድን የሚከላከለውን አንቀፅ ግን ማግኘት አልተቻለም!!”
  **የተኮረጀ ሕግ ትክክል ነው ስህተት የለውም ብሎ ልብ ከማውለቅ ራስን የአሸባሪነት ካባ ማውለቅ!!የኢህአዴግ ትልቁ ችግር ሥራ ፍጠሩ ማለቱ ነው። በውጭው ሀገር ሥራ ፈቶች አውርቶ አደር፤ በትኖና ተንትኖ መኖርን አጥንተዋል። በውስጥም ያሉ በህወአትሻቢያ ጥላ ሥር ተጠልለው በአንድ እጃቸው ሀገርና ህዝብ ሲገዘግዙ በሌላኛው እጃቸው ስለህወአት መፈክር ይላሉ በአፋቸው የቁራ ጩኸት የአዞ እንባ የሚያነቡ አሉ። ኢህአዴግስ ብሉና ተባሉ የመናገርንና የኢኮኖሚውን ጉዳይ ለእኛ!መንቀሳቀስና መዘወዘወር ስትፈልጉ አሳውቁን ፍቃድ እንሰጣለን ይል የለም!!

  **ኦሮሞ ይህንን ሁሉ መሬት ተቸሮት በቋንቋው መናገር ተፈቅዶለት ተረስተው የነበሩ የማይታወቁ ተፈጥረው ይህንን ሁሉ ምሁር ነኝ ባይ ቱልቱላ በእየሀገሩ ደረቱን ነፍቶ፣ ቂጡን አሳብጦ፣ በእየ መሸታ ቤቱ፣ ቡና ቤቱና ሃይማኖት መሰባሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ሲደነፋ ከሚውል ዛሬም የኩበት ጭስ አይኗን የሚያጨናብሰውን፣ ወገቧን የልጆቿ ዳቦ መግዣ እንጨት ሸከማ የቆረጠውን፣ዛሮም በባዶ እግሩ የሚቆራፈደውን ፣በአዛባ በተለቀለቀ መደብ ቅማል፣ ቅጫም፣ ትኋን የሚግጠውን ድፍረስ የወንዝ ውሃ አልቅትና ትል ሆዱን የቆዘረውን፣ ያልፍልኛል ብሎ ሳያልፍ በረሃ የቀረ፣ አዞ የበላው፣ ሆድ ዕቃው የተሸጠው፣የተደፈረች አህትና፣ውሻ እተባለ ማንነቱ የተዋረደው ዜጋ፣ በሰው ሀገር እጅ እግር አንገቱ በሜንጫ የተቀላውን ዜጋ እንዴት መቼ ይታደጉታል? በእርግጥ ዘመኑ የታሪክ ማንበቢያና መራቀቂያ ዕውቅና ማግኛ ወይንስ የተሃድሶ የለውጥ ታሪክ መሥሪያ ነው? ይህ የአርስ በእርስ መተራመስ ለማን ጠቀመ? የት ሀገር ሠራ? እስቲ ኤርትራውያንና ትግሬዎች የሞቱለትን ዓላማ አስታውሱ ውጤቱ ምን ሆነ? እራሱ በሱስና በዘረኝነት የታሰረ ህዝብ እንዴት ግለሰቦችን ከድህነት ነጻ ያወጣል ለባርነት ያዋጣል እንጂ!!!
  **እናንት በዚህ ክፉ ዘመን የወጣችሁ፣ ክፋት አፍቀሪ፣ ክፉ የክፉ ዘሮች ሆይ፣ ለራሳችሁ ክብርና ዝና ይህ ደረቅ ጫት እየመጠጣችሁ፣ የውጭ ሀገር ድርጎት(ደቻሳ እየበላችሁ)ደሃውን በባዶ ሆዱ፣ ተባላ የምትሉ ሁሉ ተጠንቀቁ (ሻቢያህወአት)መንግስትም በዓላማችሁ ተበባሪያችሁ ሆኖ አብሮአችሁም ቢሰራ ሕዝብ የነቃ እለት ግን ወየውላችሁ!በለው! በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ