| News sites | Audiovisuals | Advocacy groups | Political Org | Sport/culture | |
|---|---|---|---|---|---|
| » Amharic | » Abugida | » Addisdimts | » SMNE | » Andinet/UDJ | » Ethiosport |
| » Addis Voice | » Addis Neger | » DW Amharic | » EHRCO | » Andinet/USA | » ESFNA |
| » Cyberethiopia | » EcadForum | » VOA Amharic | » Advocacy Ethiopia | » EPRP | » Libro |
| » ER | » EthioGuardian | » ESAT | » Ethio American | » EPRP D | » Athletics Ethiopia |
| » Ethiofreedom | » EthiopiaZare | » Ethiotube | » NES Global | » Ginbot 7 | » AddisCulture |
| » Nazret | » Quatero | » Awrambatimes | » Gasha | » OLF | Music sites |
| » EthioMedia | Local src | » Diretube | » Amnesty | » ONLF | » Ethiosound |
| » Zehabesha | » Addisfortune | » Ethiosound | Blogs | » Timret | » Lucyzare |
| » Tadias | » Capital | » Lucyzare | » Tesfaye G/Ab | EPRDF src | » Music |
| » Africa media | » Ethiosun | » Ethiosound | » Abe Tokichaw | » Aigaforum | » » » » »» |
| » Maledatimes | » Reporter | » Ethio Diaspora | » Z'Ethiopia | » Walta | » » All Links » » |
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2001 ዓ.ም. January 06, 2009) ፦ ያለአግብብ የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ ታላቅ አለማቀፋዊ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግና በተለይ እውቁን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮንና የመጀመሪያዋን የኢትዮጵያ ሴት የፖለቲካ ድርጅት መሪ የሆነችውን ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳን ሁኔታ በጉልህ የሚያሳይ አለማቀፍ የአዘጋጅ ኮሚቴ ተቋቋመ። [View poster and cities, pdf]
ረቡዕ ጃንዋሪ 14/2009 በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በትውልድ ሃገራቸው የሚካሄደውን የማናለብኝነት የህግ ጥሰት ለአለም ማህበረሰባትና መንግስታት በአንድነትም ሆነ በተናጠል እንዲያሳውቁ የሄው አዘጋጅ ኮሚቴ የገለጸ ሲሆን በተለይ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች የሚኖሩባቸው ከተሞች በህብረት በመውጣት የአገዛዙን የህግና የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማሳየት ጉልህ ሚና መጫዎት እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል።
በሰልፉ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር በእስር የሚንገላቱትንና ፍትህ አጥተው የሚሰቃዩ ወገኖችን ሁኔታና በተለይ በአሁኑ ሰዓት በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ ያስቆጣውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳንና ዝነኛውን የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ ካሳሁንን ሁኔታ በጉልህ በማሳየት (ሃይላይት በማድረግ) የተቃውሞው ሰልፍ እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።
ይህንኑ የሰላማዊ ሰልፍ በመደገፍና በመተባበር ጃንዋሪ 14/09 በሲያትል አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ከፍተኛ ዝግጅት እያካሄዱ መሆኑን አዘጋጆቹ ጠቁመው ከመቸውም ጊዜ በበለጠ የዚህን አስከፊ አገዛዝ ለማጋለጥ በሲያትል ሲቲ ሴንተር ሰልፍ የሚደረግ ከመሆኑም በላይ ለከፍተኛ የመንግስት አካላት በተለይም በኮንግረስና ሴኔት አካባቢ ትኩረት እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
በሲያትል የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አጎራባች የሆኑት የቫንኩቨርና የፖርትላንድ ነዋሪዎችም እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።