ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች

ኢ.ኤም.ኤፍ – ከአፍሪካ ለአለም ዋንጫ ካለፉት አስር አገሮች መካከል፤ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ይገኙበታል። እሁድ ኦክቶበር 13 ኢትዮጵያ እና ናይጄርያ – ኦክቶበር 19 ግብጽ ከጋና ጋር ይጫወታሉ። ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ ጋር ለምታደርገው ግጥሚያ ከወዲሁ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ባለፈ፤ ከሌላ አገር ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደረጉም። ሱፐር ስፖርት ድረ ገጽ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ግን፤ ግብጽ ለኢትዮጵያ ያቀረበችውን የወዳጅነት ጨዋታ ውድቅ አድርጋዋለች።

Ethiopian-National-Team

ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሲሰጥ፤ “አዎ ከግብጽ በኩል የወዳጅነት ጥያቄ ቀርቦልናል። ሆኖም በግብጽ አገር መረጋጋት የለም። በ እንዲህ አይነቱ አለመረጋጋት በሌለበት አገር ጨዋታ ማድረግ አንችልም። ለነገሩ ከዚህ በፊት እኛ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርጉ ጠይቀናቸው ፈቃደኛ አልሆኑም። የአሁኑ የኛ ውሳኔ ለተጨዋቾቻችን ደህንነት ሲባል የተደረገ እንጂ፤ ግብጽን ካለማክበር የመጣ አይደለም።” ብለዋል።

በ እርግጥም በግብጽ አገር ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ኦክቶበር 19 ቀን ከጋና ጋር የሚደረገው ጨዋታ በዝግ ስቴዲየም ውስጥ እንዲሆን በፊፋ በኩል ተወስኗል። የት ሊሆን እንደሚችል ገና አልታወቀም። ቀኑ ሲደርስ ደግሞ ተመልካች በሌለበት ይጋጠማሉ ማለት ነው። ለጋና ተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እስካሁን የትኛው ስቴዲየም እንደሚጫወቱ ይፋ አልተደረገም።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 3, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች

  1. Pingback: ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አላደርግም አለች - EthioExplorer.com | EthioExplorer.com