ኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴና የ1966ቱ ሕዝባዊ አብዮት -፩

እንደ መንደርደሪያ

‹‹ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ

ለአገር ብልፅግና ለወገን መከታ››

ትናንትና አሐዱ ባልነው ወርኻ የካቲት የ1966ቱ አብዮት ከፈነዳ ዘንድሮ አርባኛ ዓመቱን ይደፍናል፡፡ ይህን ተከትሎም የተለያዩ ሰዎች፣ ‹‹ይህ ሕዝባዊ የኾነ የኢትዮጵያ አብዮት ተገቢው ታሪካዊ ስፍራና ክብር ተሰጥቶት ሊዘከር፣ ሊከበር ይገባዋል፤›› የሚል አንድምታ ያለው አሳብ ሲያነሡ ቆይተዋል፡፡

የአብዮቱ ጉዞ ፍጻሜ ምንም ይሁን ምንም ይህ አብዮት በአገራችን ታላቅ የኾነ የታሪክ ምዕራፍን የከፈተ፣ ከፍተኛ የኾነ ሕዝባዊ መሠረት የነበረው፣ የብዙ እልፍ ወገኖቻችንን እንባ፣ ላብና ደም ያስገበረ አገር አቀፍና ሥር ነቀል የለውጥ እንቅስቃሴ፣ የዘመናዊቷ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ስለኾነ በቅጡ ሊዘከር ይገባዋል የሚል የመከራከሪያ አሳቦችን ደጋግመን እየሰማንና እያነበብን ነው፡፡

በዚሁ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ጸሐፊ ስለዚሁ የ1966ቱ አብዮት አርባኛ ዓመትን አስመልከቶ ይህ ታላቅና ሕዝባዊ አብዮት በተለያዩ ዝግጅቶች መዘከር ወይም መከበር እንደሚገባው የግል ሐሳባቸውን ያካፈሉበትን መጣጥፋቸውን ማንበቤን አስታውሳለኹ፡፡ Read full story from Reporter

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 13, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.