ኢትዮጵያ በጊኒ 4ለ1 በሜዳዋ ተሸነፈች

(ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ፦)እሁድ ሴፕቴምበር 5/2010 በአዲስ አበባ ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገ የ እግር ኳስ ውድድር የጊኒ ብሄራዊ ቡድን የኢትዮጵያ አቻውን 4ለ1 አሸነፈ። ብሄራዊ ቡድናችን በቅርቡ ውጤት ያስገኛል በሚል ናይጄ-ግሊዛዊ ዜግነት ያለውን የውጭ አሰልጣኝ ቢያመጣም 4ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል።

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን በአዲስ አበባ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አዲስ አበባ ስታዲየም እየጣለ ባለው ዝናብ የተነሳ በመጨቅየቱ ውድድሩ ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲዘዋወር ተደርጓል ያሉት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች በብሄራዊ ቡድናችን ደካማ አጀማመር በጣም ብዙዎች ማዘናቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ጊኒና ኢትዮጵያ ለ6ኛ ጊዜ በታሪካቸው በተገናኙበት በዚህ ጨዋታ ጎል በማግባት ቅድሚያውን የያዘው የዋሊያዎቹ (ኢትዮጵያ) በ29ኛው ደቂቃ ላይ ቢሆንም እንደ አጀማመራቸው ፍጻሜያቸው ሳያምር በደጋፊያቸው ፊት 4 ጎሎችን አስተናግደው አንገታቸውን ደፍተዋል። ጊኒዎች በ37ኛው እና በ45ኛው ደቂቃ ሁለት ጎሎችን አግብተው 2ለ1 እስከ እረፍት ሲመሩ የቆዩ መሆኑን የዘገበው ጨዋታውን የተከታተለው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ቀሪዎቹን 2 ጎሎች ሊያገቡ የቻሉትም ባለቀ ሰዓት 80 እና 90ኛ ደቂቃዎች ላይ ነበር።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለማድረግ በተደለደለበት በምድብ ቢ ውስጥ ናይጄሪያና ማዳጋስጋር ይገኛሉ። ሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ባደረጉት ጨዋታ ናይጄሪያ 2ለ0 አሸንፋለች። ቀጣዩን ጨዋታ ካማዳጋስካር ጋር በአንታናኒዮ ኦክቶበር ላይ እንደሚያደርግ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል።

ኢትዮጵያ ከጊኒ ጋር ባደረገችው ጨዋታ የነበረው አሰላለፍ፡ በረኛ፦ ቢኒያም ተፈራ፣ ተከላካዮች ዳንኤል ደብሬ፣ መንግስቱ አሰፋ፣ ሳምሶን ሙሉጌታና ተስፋዬ በቀለ፤ አማካዮች አሸናፊ ግርማ፣ ተስፋዬ አለባቸው፣ ሽመልስ በቀለ፣ አጥቂዎች ኡመር ኡክሪ፣ ታፈሰ ተስፋዬና በዳሶ ሆራ በ 4 -3-3 ፎርሜሽን ነበር።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 6, 2010. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.