ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች? … ግርማ ሞገስ

ኢትዮጵያ ከውጭ ወረራ ረጅም የነፃነት ዘመን እንዳላት የአገር ተወላጅ እና የውጭ አገር የታሪክ ተመራማሪዎች ያረጋግጣሉ። ይሁን እንጂ በስልጣኔ ግን ብዙም እንዳልገፋች ይኸው ዛሬ የእኛም ትውልድ ሳይቀር የሚያየው ሃቅ ነው። ይኽ እንዴት ሊሆን ቻለ? ረጅሙን የነፃነት ዘመን በስልጣኔ ወደፊት ለመራመድ ለምን አልተጠቀመችበትም ኢትዮጵያ? ምን ስትሰራ ነበር? የሚሉት የቁጭት ጥያቄዎች የሁላችንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄዎች ናቸው። በ19ኛው ክፍለ ዘመን በራሳቸው አነሳሽነት አውሮፓውያን ጎብኚዎችን እና ሚሲዮናውያንን እየተከተሉ ከአገራቸው ወጥተው የፖለቲካ ሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የኢኮኖሚ፣ የመንገድ ስራ የመሳሰሉ ዘመናዊ (Secular) ትምህርት ቀስመው አገራቸውን ለመርዳት ወደ አገራቸው የተመለሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ምሁራን የእነ ነጋድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ (1886-1919) ሁሉ የቁጭት ጥያቄ ነበር። በጣት የሚቆጠረው የነገብረ ሕይወት ትውልድ የውጭ ትምህርት ቀስሞ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ባፄ ምኒልክ ዘመን ነበር። ይሁን እንጂ ለዘመናዊነት በር የተከፈተው ባፄ ኃይለ ስላሴ ዘመን እንደነበር፣ በኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በ1942 ዓመተ ምህረት (እ.ኤ.አ. 1950) የአዲስ አበባ የተፈጥሮና የሶሻል ሳይንስ ኮሌጅ መከፈቱን፣ ኮሌጁ የተደራጀው በኢትዮጵያ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመክፈት በንቃት ይሰሩ በነበሩ ካናዳውያን እየሱሳውያን (Jesuits) ሲሆን የተማሪዎቹ ቁጥር ከ100 በታች እንደነበር ክፍሉ ታደሰ (The Generation, p. 15-16) ያመለክታል። እሱም ቢሆን እጅግ ዘግይቶ የመጣ በውቅያኖስ ላይ ያረፈ ትንሽ ጠብታ ያህል ነበር። ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች?…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 11, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to ኢትዮጵያ ለምን ኋላ ቀረች? … ግርማ ሞገስ

 1. ሰለሞን

  January 11, 2014 at 6:11 PM

  ምን ነካህ ግርማ ለመሆኑ ሰለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታውቃለህ ? አታውቅም ብታውቅ ኖሮ ቤተክርስቲያናን በ እውቀት ማነስ ማለትም ከመንፈሳዊ እውቀት ውጭ ለሌላው ባዳ እንደሆነች አትጽፍም ነበር። እስቲ ይህ ሁሉ የነጭ መንጋ በቱሪስት ስም ኢትዮጵያ ውስጥ እየገባ ለምን ይሆን የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ጥንታዊ የብራና ጹሁፎችን በውድ ዋጋ የሚገዙት ? ከአክሱም ሀውልት ምን ትማራለህ ያንን ወጥ ድንጋይ እንዴት አቆሙት ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ ዛሬም ድረስ አለምን የሚያስደምመው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ቤተክርስቲያናትስ እንዴት ታነጹስ ብለህ ጠይቀሀል? የዘመን አቆጠጠሮችን ስሌትስ የዚች ቤተክርስቲያን ለቃውንቶች ቀመር አይደለምን ? ቤተክርስቲያን በአለማችን አስራ ስድስት ፕላኔት እንዳሉ ታውቃለች ሳይንስ እየተንገዳገድም ቢሆን ወደ 11 ደርሳል። ስለ ቤተክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ እውቀት ነጮቹ ደርሰውበት ቤተክርስቲያናችንን እያስመዘበራት ነው። እስቲ ጥንታዊ ቤተክርስትያን ውስጥ ግባና ሰ እሎችን ተመልከት እንዴት እንደታነጹ አጢን አንድ ነገር ሊገባህ ይችላል ወይም እራስህን እንዲህ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ ይህ ስልጣኔ ለምን ተቓረጠ ወይም እንዴት ላይቀጥል ቻለ ብለህ ጥያቄህን ልታስተካክል ትገደዳለህ ። ሌላው ስለ ሁለት አካል አንድ ባህርይና ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ በተዋህዶ እምነትን መግለጽ ትልቁና መሰረታዊ ነገር ነው።ስለዚህ ጉዳይ የተክለጻዲቅ የታሪክ መጽሀፍ ላይ የተጻፈውን ከምትጠቅስ ከቤተክርስቲያን ተዋቂ አገልጋዮች እንዱን ብትጠይቅ ልዩነቱን ቀላል አድርገህ አትገልጸውም ነበር። ለማንኛውም ቤተክርስቲያና የ እውቀት ምንጭ ነች ነገር ግን የነጮችን ሴራ ሳናውቅ እነሱ እኛ ቤተክርስቲያናችንን እንድንቅና እንድንጠላ እንዲያውም ተጠያቂ እንደሆነች የሰበኩትን ተክትለን ከቤተክርስቲያን ስንርቅ እነሱ ግን በጀት መድበው እየመዘበራት ነው ። ለምን ይመስልሃል መልሱን ላንተው ትቸዋለሁ

 2. እንግዳ1

  January 11, 2014 at 6:50 PM

  ጥሩ ጅምር ነዉ:: በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ ጥናት ሊደረግ ይገባል::አቶ ግርማ ከታሪክ አንጻር ብዙ አሳዉቀዉናል:: ለሀገሪቱ እድገት ግን እርሳቸዉ የሚሉዋቸዉ ምክንያቶች መሰረታዊ ምክንያቶች አይመስሉኝም:: በወቅቱ የነበሩት ማህብራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች ሥልጣንን በሰላማዊ መንገድ መመስረትን የሚፈጥሩ አይመስለኝም:: የም’እራቡ ትምህርት እንደ አንድ የ’እድገት ምንጭ መቆጠሩ ራሱ ትክክል አይመስለኝም:: ሀገር በቀል እዉቀት ሊያድግ ለምን አልቻለም? ብለን ስንጠይቅ ብዙ ያልተመለሱ ነገሮችን እናያለን። ያክሱም ስርወ መንግስት እንዴት ወደቀ…የዉጭ ሀገሮች ሚና ምን ነበር…ሀገሪቱ ከዉጪዉ ዓለም ጋር ተቆራርጣ አልነበረምን_በቱርኮች ምክንያት::በክርስትና ስም ግብጾች ያስገቡት የስንፍና ባህል…የለምን….

 3. derbi kejela

  January 14, 2014 at 6:22 AM

  አቶ እንግዳ ያገናዘቡት ትክክል ነዉ::
  ግርማ ሞገስ ላቀረበዉ ጥያቄ የሰጠዉ መልስ የከሰረ ነዉ::
  በአንድ በኩል የኛ የቤተ ክህነት ትምህርት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ መስፋፋት አለደረገም ሲል በሌላ በኩል ያዉሮፓ ፈረንጅ ብቻ የሳይንስና ትክኖሎጅ ፈጠሪ አስመስሎ ጥሩንባ ይነፋል::
  አዉሮፓ በጭለማ ዉስጥ ሲኖር ሳይንስና ቴክኖሎጂን የለበጠዉ ከአረብ አረብ እስላም ነዉ:: የአረቡ ደግሞ የወደቀዉ የቱርክ አኦስማን ደንቆሮዎች በስፍራዉ ተተክተዉ ሲሆን ምእራብ አዉሮፓ ድግሞ ክ15ኛዉ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በባሪያ ንግድና ቅኝግዛት ሰፈራ ለ19ኛዉ ክፍለ ዘመን የንዱስትሪ አብዮት መጀመርና መስፋፋት አመቺ ሁኔታ ተፈጠረ::
  ያለፈዉን እንኩዋ ትተን ለምን ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ወዲህ ኣጤ ሐይለ ስላሴ ከምንም ጅምረዉ ከፍተኛ ጥረት አድርገዉ ነበር:: ለምን ጥረቱ ከሽፈ?
  ለምሳሌ ደቡብ ኮሪያ: ቻይና ጃፓን ወዘተ ባጭር ጊዚ ዉስጥ ከፍተኛ እድገት አሳይተዋል:: ኮሪያ በ30 አመታት ዉስጥ ከፍተኛ ርምጃ አድርጋለች::
  አኢትዮጵያ ለምን ሁዋላ ቀረች?
  አጤ ሐይለ ስላሴ መልምለዉ ያሳዱጉት ያስኮላዉ ትምህርት ዉጤት ነዉ አገሪቱን መቀመቅ ያዉርዳትት:: ይህ ባንዳና ወራዳ ከሃዲ ቅጥረኛ ስግብግብ አስመሳይ ትዉልድ ነዉ ታላቅ ደንቃራ ሆኖ ያለዉ:: ስልጣንን በአቁዋራጭ ለመያዝ ሲል ሕዝብን ያናቁራል: ሃይማኖት ይክዳል:: ባሕል ያውድማል:: በራሱ ሳይሆን በፈረንጅ ጌቶቹ ሳንባ ይተነፍሳል:: ያስኮላዉ ትዉልድ የፈረንጅ አፕቲት እንጅ የስራ ችሎታና ሙያ የለዉም:: ያየዉን የሚመስል: ለመሆን የሚንጠራራ በጣም ወራዳ ነዉ::
  ድክመቱን: ስግብግብነቱን: ወኔቢስ ወሽካታነቱን ባለፉት አባቶችና ትዉልድ ላይ ለመላክክ ያላደረገዉ ጥረት የለም:: ይህ አጋሰስና የፈረንጅ አሽከር የሆነዉ ትዉልድ ተመንግሎ ሌላ በራሱና በጥንት አባቶቹ ማንነት ኮርቶ መስራት የሚችል እስክሚፈጠር ድረስ ኢትዮጵያ በቅኝ ተገዥነትና በችጋር ተመጽዋችነት ትቀጥላለች:: ወደፊት ሳይሆን ወደ ሁዋላ ጉዞ ስለጀመረ ቶሎ ድራሹ እንዲጠፋና ኢትዮጵያ ከዚህ ሁነእታ ነጻ ትወጥጣ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳት::

  • እንግዳ1

   January 15, 2014 at 4:00 AM

   “…አጤ ሐይለ ስላሴ መልምለዉ ያሳዱጉት ያስኮላዉ ትምህርት ዉጤት ነዉ አገሪቱን መቀመቅ ያዉርዳትት:: ይህ ባንዳና ወራዳ ከሃዲ ቅጥረኛ ስግብግብ አስመሳይ ትዉልድ ነዉ ታላቅ ደንቃራ ሆኖ ያለዉ:: ስልጣንን በአቁዋራጭ ለመያዝ ሲል ሕዝብን ያናቁራል: ሃይማኖት ይክዳል:: ባሕል ያውድማል:: በራሱ ሳይሆን በፈረንጅ ጌቶቹ ሳንባ ይተነፍሳል:: …” ለማለት ምን ማስረጃ አለህ? አንድን ትዉልድ በደፈናዉ መኮነን ተገቢ እና የምሁር ተግባርም አይመስለኝም::
   የሚያሳዝነዉ ደግሞ በሚከተለዉ መደምደምህ ነዉ: “…ይህ አጋሰስና የፈረንጅ አሽከር የሆነዉ ትዉልድ ተመንግሎ ሌላ በራሱና በጥንት አባቶቹ ማንነት ኮርቶ መስራት የሚችል እስክሚፈጠር ድረስ ኢትዮጵያ በቅኝ ተገዥነትና በችጋር ተመጽዋችነት ትቀጥላለች:: ወደፊት ሳይሆን ወደ ሁዋላ ጉዞ ስለጀመረ ቶሎ ድራሹ እንዲጠፋና ኢትዮጵያ ከዚህ ሁነእታ ነጻ ትወጥጣ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳት::”
   ሁለት ነጥቦችን ላነሳ እፈልጋለሁ: 1ኛ. ህብረተሰብ ተከታታይነት አለዉ_አንተ የምትለዉ ትዉልድ ጠፋ ማለት አንድ ከፍተኛ ክፍተት ነዉ:: ለነገሩ ደርጉ በቀይሽብር አንድ ትዉልድ አልደመሰሰም ብለህ ነዉን?
   2ኛ. ከላይኛዉ ጽሁፍህ ክርስቲያን መስለኸኝ ነበር:: ክርስቲያን ደግሞ ለሌላዉ ክፉን አይመኝም:: ያዉም ለአንድ ትዉልድ መጥፋት!?
   በሰከነ መንፈስ በጥናት ላይ የተመሰረተ መልስ ይዘህ ብቅ እንደምትል ተስፋ አደርጋለሁ::

 4. Sam

  January 19, 2014 at 9:52 AM

  Girma seems to have read Ethiopian history well. His reading of Ethiopian history could not be interpreted as suspicious. But the question he has raised in the title “why Ethiopia remains backward” is not answered by him in this article. Does any country could excel economically and politically while living under a feudal system? Girma has no answer. In fact, he did not entertain the question to begin with. Most importantly does it make a difference having well-educated few individuals to make a significant change while the feudal system was still intact? Girma seems to believe that is possible. I honestly disagree. Was it possible to make fundamental change while the feudal culture still dominated the way of life in Ethiopia? The question had never been raised so that it is not a stretch to believe Girma does not think the culture stood in the way of progress. We Ethiopians whether we believe it or not are a slave of our own culture. Even those radical leaders of the 1960s student movement leaders were not immune from this handicap. Unless we believe our culture needs a radical surgery progress will remain a pipedream.