ኢትዮጵያ፡- ሰማይ ተደረመሰ! ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም

 

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ሰማዩ  ተደረመሰ!

ብዙዎች አንባቢዎቼ ‹‹ተረት ተረት የመሰረት››ን የመኝታ ተረቶች ምን ያህል እንደምወዳቸው ያውቃሉ፡፡ በቅርቡ  በጣም የምወደውን የመኝታ ሰአት ተረት “የፒኖኪዮን ታሪ በአፍሪካ” ጽፌ ነበር፡፡

ለመሆኑ ሰለ ሚጢጢዋ ጫጩት ክፉኛ ዽንጋጤ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?

ይሄዉላችሁ  አንድ ቀን ሚጢጢዋ ጫጩት ጓሮ መሬቱን በመጫር ላይ ሳለች፤አንዲት ነገር አናቷ ላይ ዱብ አለባት፡፡‹‹እረገኝ››፤ ‹‹ሰማዩ ተደረመሰ! ቶሎ ሄጄ ለንጉሡ ልናገር፤ አለች፡፡ ሚጢጢዋ ጫጩት ሄኒ ፔኒን እስታገኝ ድረስ ሮጣ ሮጣ ሮጣ፤ ሲታገኛት፤ ምንድን ነው ልብሽ እስኪፈነዳ የሚያሮጥሽ አለቻት:: እንዴ ሄኒ ፔኒ ሰማዩ እኮ እየተደረመሰ ነው:: ታዲያ ለንጉሱ ልነግር ነዋ አለች፡፡ ሚጢጢዋ ጫጩትና ሄኒ ፔኒ ይህንኑ ደግመው ለዳኪ ዳድል፤ ለጉሲ ሉሲ፤ ለተርኪ ለርኪ፤ ለፎክሲ ሎክሲም በእግረ መንገዷ ላይ ሲያገኛቸው ነገረቸው፡፡ ይህን የሰማውም ፎክሲ ዎክሲ ቀበሮ: ታዲያ እኮ እኔ ወደ ንጉስ ቤት የሚያደርሰውን አአቁአራጭ አውቃለሁ ኑ ተከተሉኙ አላችው፡፡ ያ ተንኮለኛ ፎክሲ ዎክሲ ቀበሮ ግን በነዚህ በሚያማምሩ ባለላባዎች  ጓደኞች: በመንደላቀቅ ሊቀረጣጥፋቸው ወደ ጉድጓዱ በር ነበር የወስዳቸው፡፡ ተሰባስበው ወደ ፎክሲ ዎክሲ ዋሻ ሊገቡ ሲሉ፤ የንጉሱ የአደን ውሾች ሲጯጯሁ ሰሙ፡፡ ፎክሲ ዎክሲም ይህን ሲሰማ ጉድ እንደፈላበት አውቆ በአቆራራጭ በጫካው ውስጥ በመሹለክለክ የንጉሱ የአደን ውሾች ከኋላው ሲከተሉት መለስ ብሎ ሳያይ እምጥ ይግባ ስምጥ ሳይታወቅ ጠፋ፡፡

የሚጢጢው ጫጩት ታሪክ በኢትዮጵያ ያለውን መንግስት መባነን፤ ቅዠት፤ ፍርሃት፤የሚያሳይ ነው፡፡ ለሕብረተሰቡ መድረስ ያለበትን ዜናና ኢንፎርሜሽን ፈላጭ ቆራጩ ግፈኛው መለስ ዜናዊ ለማፈን በተንቀሳቀሰ ቁጥር ሰማዩ ይደረመስበታል፡፡ በ2010 የአሜሪካን ድምጽን የአማርኘውን ፕሮግራም ለማፈን የማይታመንና የተለመደውን የውሸት ጣቃ በመተርተር ሲወነጅል: ‹‹በተለያየ መንገድ እንደተረዳነው ላለፉት በርካታ ዓመታት የአሜሪካ ድምጽ የአማራኛው ሬዲዮ አሳፋሪ የሆኑትን እንደ ሩዋንዳው ሬዲዮ ሚል ኮሊንስ፤በሚመስል መልኩ አጥፊና አጋጭ የሆነ ጨርሶ የጋዜጠኝነትን ስርአት ያልተከተለ፤ አጥፊ ፕሮፓጋንዳ እንደሚዘራ ተገንዝበናል›› በማለት የአሜሪካን ድምጽ ሬዲዮ ጣቢያን፤የሩዋንዳ እልቂት ሬዲዮ ጣቢያ ለማድረግ ተንደፋድፈዋል፡፡

መለስ ለመላው ዓለም በዓለም እጅጉን አስጊ የሆኑትን ሽብርተኛች አትዮጵያ ውስጥ ይዣለሁ፤ አስሬያለሁ፤አደገኞች የሆኑትን ዎደር የለሽ በነጻ የመጻፍ የ2012 የፔን ተሸላሚውን እስክንድር ነጋን፤ ወጣቷን አይበገሬ ወጣት ጋዜጠኛና የ2012 የ ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን በጋዤጠኝነት ጥንካሬ ተሸላሚዋን ርዕዮት ዐለሙን፤ እንዲሁም ጀግናውን በመለስ የፍርሃት አስተዳደር የተዘጋው የአውራአምባ ታይምስ ኤዲተር ውብሸት ታዬን ቃሊቲ አስገብቻለሁ በሚል የእብለት ቱልቱላ ደንፍቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካው ሴኔተር ፓትሪክ ሊሂ ባቀረቡት የኮንግሬስ ሬኮርድ ንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞች በሰላማዊ መንገድ ተግባራቻውን እንዳያከናውኑ አሰቸጋሪ ሁኔታ በመፍጠር እስንድር ነጋን የመሳሰሉት በጋዘተጠኝነት ሙያቸውም በፖለቲካውም ምድር እንዳይነቀሳቀሱ አድርጓቸዋል በማለት ተናግረዋል፡፡

ኢትጵያውያን በሃገራቸው የተነፈጋቸውን በነጻ ኢንፎርሜሽና ከተለያዩ ነጻ ዘጋቢዎችና ሚዲያዎች ማግኘት እንዳይችሉ መለስ በሚቻለው ሁሉ በመሽከርከር በማገድ ላይ ይገኛል፡፡ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች (ሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ) እንደዘገበው፤ የኢትዮጵያ መንገስት ማንኛውንም የኢንፎርሜሽን ልውውጥ እንዳይቻልና ኢትዮጵያዊያን ከዓለም ሁኔታ ተነጥለው እንዲኖሩ በማድረግ ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሚጢጢ ጫጩቶች እጅግ ከመደናበራቸው የተነሳ፤ ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩዋቸው ማተሚያ ቤቶች እንደ ብርሃንና ሰላም ባሉት ማተሚያ ቤቶች የሚታተሙት ጋዜጦች በሙሉ ፖለቲካዊ ምርመራ ሳንሱር እንዲደረግባቸው አድረጓል፡፡ በተቀረጸው የሕትመት ውል ኮንትራት  አንቀጽ 10 ስር ‹‹ሕግን የሚጻረሩ ህትመቶችን ስለመከልከል›› በሚለው ውስጥ ማተሚያ ቤቱ ምንም አይነት ሕግን የሚተላለፍ ጉዳይ ያለ መስሎ ከተሰማው ላለማተም መብት አለው፡፡ የመጻፍ ነጻነት የተከበረ ነው  በምንም ሁኔታ ሳንሱር አይኖርም የሚለውን የህገመንግስቱን አርቲክል 29ኝን ይጻረራል ብሎል፡፡ ነጻና ገለልተኛ ለሙያው ታማኝ የሆነና በራሱ የህግ ልዕልና የሚመራ ከአገልጋይነት የነጻና ሕዝባዊ የሆነ ዳኛ ብቻ ነው በበቂ ምክንያት ላይ በመንተራስ የሚዲያን ነጻነት ሊገታ የሚችለው፡፡ ያም ሆነ ይህ ለመለስ ዜናዊና ለኩባንያው ስለ ሕገመንግስታዊ ሕግ መናገር ማለት፤ ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ አለያም ውሃ ቢወቅቱት እምቦጭ እንደማለት ከንቱ ድካም ነው፡፡

ድንበር አልባ ጋዜጠኞች እንደሚሉት ብቸኛ የኢንተርኔት ግልጋሎት ሰጪ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም› ቶር የተባለውን ዓለማ አቀፍ የኔት ወርክ አገልግሎትና የተዘጉ ድህረገጾችን በስውር መክፈቻ ለመዝጋትና ለማፈን መሳርያ ገዝቷል:: ቶር እንዳሰባሰበው መረጃም ከማርች እስከ ጁን 2012 ባለው ወቅት በቶር ተጠቃሚ የሆኑትን ግለሰቦች ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ መሃል ከ350 እንደማይበልጡ ዘግቧል፡፡ይህም ያን ያህል ወጪ የወጣው ከ80 ሚሊዮን ህዝብ መሃል ከ400 የሚያንሱ ግለሰቦች በመጠቀማቸው ነው ማለት ነው፡፡ ምን ይሉት አስተሳሰብ ነው ይሄ ወይስ ጭርሱን ገዢው መንግስት በፍርሃት ርዶ የሚያደርገውን ማጣቱ ነው፡፡

ሰማዩ እየተሰነጣጣቀ ነው!

የግል ኮምፒዩተርና የራሳቸው ኢንተርኔት ካላቸው ባሻገር በገጠርም ሀፖነ በከተማው ውስጥ ያሉት ወጣቶች መሃል የስካይፔ እና የሌሎች በኢንተርኔት ስልክ መጠቀሚያ አገልግሎቶች በጣሙን ተወዳጅነት አላቸው፡፡ያም ሆኖ ግን የነዚህ ተጠቃሚዎች ከቁጥር የማይገባ ከመሆኑም ባሻገር የሚገኘውም አገልግሎት ዋስትና የሌለው ብል እንደበላው ጨርቅ የሚቆራረጥና ተስፋ አስቆራጭ አገልግሎት ነው፡፡ የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ክፍል ጥናት እንደሚያሳየው፤በፍሪደም ሃውስ ፍሪደም ኦን ዘ ኢንተርኔት 2011 ላይ ሲያስረዳ ኢንተርኔቱ ከተገኘ በኋላ በአዲስ አበባ ሳይበር ካፌ ውስጥ አንድ መልእክት ከፍቶ ለማንበብ ያውም በብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ስድስት ደቂቃዎች ይወስዳል፡፡በሰብ ሰሃራ አፍሪካ ካሉት ሃገሮች ሁሉ በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የኢነርኔትን መልአክቶች የምትቆጣጠር ሃገር ኢትዮጵያ ብቻ ነች፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ዪንተርኔት ተጠቃሚው ቁጥር 0.5 በመቶ ከሰማንያ አምስት ሚሊዮን ሕዝብ መሃል ነው፡፡በዚህም ሁኔታ ከሴራሊዮን ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ነች አንደኛ ሴራሊዮን ትሆናለች፡፡ሌላ አብሯቸው የተሰለፈ የዚህ አጸያፊ ተግባር ተሳታፊ አልተገኘም፡፡

ምንም አንኳን ኢትዮጵያ በብዛት የሰው ቁጥር ያለባት ሃገር ብትሆንም፤እርባና ቢስ የሆነ መዋቅር ያላትና መንግስት የቴሌኮሙኒኬሽንን አገልግሎት በሞኖፖል የያዘበት ሃገር በመሆኗ የዲጂታል ሚዲያውን እድገትና የሕብረተሰቡንም ተጠቃሚነት እንዲያቆለቁል እያደረገው ነው፡፡ በአህጉሩም ካሉት ሀገራት በሙሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አነስተኛው ቁጥር የሚገኝባት ሀገር ናት፡፡ በአፍሪካ ካሉት ሁሉ ከፍተኛውን የኢንተርኔት መቆጣጠርያ መሳርያ ያስገባችና ለዚያውም ለተሻለ የሃገርና ሕዝብ አገልግሎት የሚችለውን ገንዘብ የሕዝብን መብት ለማፈኛ መጠቀሚያ አድርጎታል፡፡ የነጻ አስተሳሰብ መብት ገፈፋን በይበልጥ በማጠናከር፤የነጻው ፕሬስን በማገድ፤እና በ2005 ምርጫ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከስር መሰረቱ ምርጫውን ካሸነፉበት ጊዜ አንስቶ የዚህ መሰል አጸያፊ ተግባር ገዚው መንግስት በማከናወን ላይ ነው፡፡

አንድ ዜጋ ስካይፕ የኮምፑተር ስልክ መነጋገሪያን በመጠቀሙ ብቻ መለስ ዜናዊ ለ15 ዓመታት ማሰርን ለምን ፈለገ? ታዛቢዎች እንደሚሉት ይህ የቴሌ የውሸት ቀላማጅ ሕግ፤ በእርባና ቢስ ዲክታተሮች መደናበርና መቅበጥበጥ፤ ንፍገት ጥቅም ፍለጋ የተነሳ ተግባር ነው፡፡ የቢቢሲ የቀድሞ የዜና ዘጋቢ ስትናገር፤ ገዢው መንግስት ይህን የሚያደርግበት ዋነኛው ሰበብ በመንግስት የሚተዳደረው ቴሌኮሙኒኬሽን በዚህ ገዳዳ ሕግ በመጠቀም ሕብረተሰቡን በአቅሙ ስልክ የሚያስደውሉትና ኢንተርኔት ካፌዎች ከስራ ውጭ በማድረግ ለማዘጋትና ብቸኛ አገልግሎት ሰጪነቱን በማረጋገጥ አሁንም ቀድሞም እንደሚያደርግ እጅጉን በናረ ዋጋ ከሕብረተሰቡ አቅም ጋር ባልተመጣጠነ ተመን ንግዱን ለመቀጠል እንዲችል ነው፤ብላለች፡፡ ከዚህ ባለፈም ገዢው መንግስት ባስገባው ብዙ የሃገሪቱ ገንዘብ በፈሰሰበት መቆጣጠርያው ስካይፕ የኮምፑተር ስልክ መነጋገሪያ በቀላሉ ሊጠለፍ ስለማይቻልና አስቸጋሪነቱ ደግሞ የስለላውን ስራ ስለሚያከሽፍበትም ነው፡፡ በዚህ አካሄዱ ገዢው መንገስት ከሕገመንግስቱ መመርያ ውጪ እንደፈለገው በማድረግ የህዝብን መብት ደግሞ ደጋግሞ ለመግፈፍ እንዲያስችለው የወጣው አዋጅ የሚያሳፍርም የሚገርምም ነው፡፡

የቴሌኮም ቀላማጅ ህግ  እወጃ 2012

አሁን በስፋት የሚነገርለት የቴሌኮም የቅልመዳ አዋጅ እንደሚናፈሰው ወሬ ሳይሆን አሁን፤ ገና በረቂቅ ደረጃ ላይ ነው፡፡ ሆኖም ግን ቀድሞ የነበሩትን ህግ ተካ ወይም በነዚያ ላይ ተመስርቶ ወጣ ተባለም በራሱ ወጣ ቢባልም ረቂቅ የሚባል አንድም አዋጅ ለመለስ የማሕተሙ ፓርላማ ቀርቦለት አያውቅምና አሁንም እንደተለመደው ያለቀለትና በመለስ ተፈርሞ ከቀረበ ፓርላማ ተብዬውም አገልግሎቱን ለማረጋገጥ እንደተለመደው እጃቸውን አውጥተው (አውረዱ እስኪባሉ) ያጸድቁታል፡፡ የመለስ ቃል ሕግ ነው፡፡  እርባና የሌለውን ሰብስቦ መለስ እስካቀረበው ድረስ ፓርላማውም ማሕተሙ ነውና በመርገጫ አስነክቶ ማረጋገጫ ያሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህም ይህም የቴሌኮም የውሸት አዋጅ መጽደቁ የታወቀ ነው አለምንም ጥርጥር የተረጋገጠ ነው፡፡ ግን ይህ የቴሌ አዋጅ ምነድን ነው?

አዋጁ በፊት ለፊቱ ስታይ፤በሃገሪቱ ላይ ሲሰራበት የኖረው የቴሌኮም አዋጅና መመርያ ሁሉ በቂ አይደለምና ይህን የቴሌኮም አገልግሎት አዋጅ ማውጣት አስፈልጎታል በሚል እቀድ የተጠነሰሰ “ህግ” ነው፡፡ የቴሌኮም አግልሎቶችም የእጅ ስልኮችን አገልግሎት፤የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት፤ማንኛውንም ማስተላለፍና መቀበል ወይም ግንኙነት መፍጠርን ያጠቃልላል፡፡ ማንኛውም ሰው በመፈብረክ፤ በመገጣጠም፤የመገናኛ መሳርያዎችን ከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት፤ከቴሌኮሙኒኬሽን ፍቃድ ውጪ ቢንቀሳቀስ ከ10 እስከ 15 ዓመት በእስራት ይቀጣል፡፡ ማንም ይህን መሰል መሳርያዎች በንብረትነት ይዞም ቢገኝ ከ1 እስከ 4 ዓመት በእስራት መከራውን ይበላል፡፡ ካለፈቃድ ከቴሌኮም እውቅና ውጪ ቢንቀሳቀስ ከ7-15 ዓመት እስራት ይደርስበታል፡፡ የህጉ አርቲክል 6 ማንም የቴሌኮምና መገልገያ በመጠቀም የሽብርተኝነት መልእክት ሲያስተላልፍ ቢገኝ የሸብርተኝነት አዋጁ በሚያዘው መሰረት ከ3 እስከ 8 ዓመት ይታሰራል፡፡….በማለት አንቀጽ በአንቀጽ ደርድሮታል፡፡

ስካይፕን መጠቀም ወንጀል ነው ከተባለና ለእስር የሚያበቃ ከሀነ እኔ ለወገኖቼ ያለኝ ምክር ከውጪው ዓለም ጋር ለመገናኘት ቀድሞ በአያት ቅድመ አያቶቻችን ይደረግ እንደነበረው የጭስ ትነት ምልክትን፤ የአታመና የነጋሪት ጥሪን፤ የፒቶግራም ስእልን፤ የእርግብን መልእክተኛነት ለመጠቀም ማሰልጠንን፤ የሞርስ ኮድን ነጠብጣብ ሳይንስ  መማር ነው:: (ግን: እንተወው የሞርስ ኮድን: እሱም የቴሌን ሃይል ስለሚጠቀም፡፡)

እንደሚታየው ከሀነ ይሄም አዋጅ ያው እንደሌሎቹ ቀርጠ ቀጥል ስራ ነው፡፡ (የጸረ ሽብርተኝነት አዋጅ ተብሎ ባለፈው እንደወጣው አዋጅ ቁጥር 652/2009) የተገኘውም ከብዙ ሃገራት አዋጆች ነው እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ካሉ (ወየር ፍረውድ እንደሚባለው ሕግ ለማለት ነው፡፡)የቴሌኮም አዋጅ ግን ከማንኛውም ሃገር ህግ ጋር ጨርሰ ሊገናዘብ የማይችልና ብቻውን የሆነ ከየሃገሩ ህጎች ተቀነጫጭቦ የተጣበቀና አላቂ ሳሚ ይሉት አይነት ሁነኛ ሕግ ተብሎ ለማስፈራሪያነት ብቻ ሊወጣ የታሰበ ጭንጋፍ አዋጅ ነው፡፡በአዋጁ ላይ የቴሌኮሙኒክሽን ንብረት ይላል፡፡ ይህም ማላት በጥቅም ላይ የዋለ አለያም ሊውል የታሰበና የታቀደ ለማልት ነው፡፡ በዚህ አዋጅም ስር ማንም የመባይል ቀፎ የያዘ ሰው፤ ወይንም የግል ለገናኛ ዎኪ ተኪ፤አለያም ብዝሃ መጠቀሚያ ያለው ኮምፒዩተር በማይክረሰፍት ዊንደው የተፈበረከ፤ከመገናኛው ሚኒስቴር ሳያስፈቅድ ሲገለገልበት ቢገኝ የሚለው አዋጁን ከጨዋታ ውጪ ያደርገዋል፡፡ሌላው ቀርቶ ልጆቻችን ረጂም ክር ዘርግተው ጫፍና ጫፉ ላይ ጣሳ አድርገውበት እንደስልክ አስመስለው የሚነጋገሩበትም በዚሁ አዋጅ ስር ፤በእስሩ ደንብ ስር ይመደባሉ ማለት ነው፡፡ ፈጽሞ ሕሊና ቢስነት ነው!፡፡

ሕጎች በአግልጋዮች የፓርላማ ማህተም ሲፈጠሩ ማንም ቢሆን ቋሊማው ወይም ሕጉ በኢትዮጵያ የመርገጫ ፓርላማ እንዴት እንደተሰራ ማየት የለበትም፡፡ምናልባት አባባሉ ናር ያለ ሊመስል ይችላል፡፡ እውነቱ ግን ከኢትዮጵያ ፓርላማ ውስጥ ሕጎች አይወጡም፤ ይልቁንስ መርገጫ ሆነው ማህተሙን ማሳርፍ ነው የፓርላማው ተግባር፡፡ አስመሳይነት የተሞላበት ክርክር ያውም የሚነሱት ነጥቦች ዋነኛውን እንዳያሰቀይሙ በመዛን ተለክተው ሆኖ ወዲያው ይሁንታው ይሰጣል፡፡ በቃ፡፡ ያንድን ሰው ፈቃድ በመፈጸም ብቻ ሕግ አድርጎ ማውጣት ተገቢነትም ተቀባይነትም የሌለው ነው፡፡ ሼክስፒር እንዳለው  “የራሳቸውን ፈቃድና ፍላጎት ሕግ የሚያደርጉ ሁሉ ሕግ አልባዎች ናቸው ፡፡”

አሁን ለመውጣት ተረግዞ ያለው የቴሌ ሕግ ከሕግ አቀራረጽ አንጻር የጨነገፈ ነውና የህግ እንግዴ ልጅ ሊባል ይችላል፡፡ በይዘትም በቅርጽም ሂደቱም ካለፉት የማይለይ ነው፡፡ በፓርላማው ሕግ ተብሎ በሚወጣው ሁሉ በእጅጉ እገረማለሁ፡፡ በቅርቡ ባሰፈርኩት ጽሁፌ ላይ ሰለ ቆርጦ ቀጥል የሽብርተኝነት አዋጅ ፈላጭ ቆራጩ የመለስ ገዢ መንግስት ከሌሎች ሃገሮች ተሞክሮ በመውሰድና በመቅዳት ወይም በመኮረጅ ያጣመርነው ነው ላላው ምላሽ፤ይህን ስሰማ ለተወሰደው ሃፍረት የለሽ ተግባርና ግልብ አነጋገር ሃገሬ ላይ በደረሰው ጉድ በሃዘን ተሸማቅቄ በእፍረት አንሼ መቀመጤን ገልጨ ነበር፡፡ ነገሩ እንደተባለው ሳይሆን ከማንም ሃገር ህግ ጋር የማይገናኝ ቆርጦ የተቀጠለ ኩረጃ ነው፡፡ የዚህ የቴሌኮም አዋጅ አሳፋሪው ጉዳይ ከብዙው መሃል ለምሳሌ ቅጣቱ ከድርጊቱ ጭብጥ ጋር የማይገናኝና ለአተረጓጎምም የማይሆን ነው፡፡ አንድ ሰው በኮምፒዩተር ላይ ባለ ያውም በራሱ ኮምፒዩተር ላይ በቆጠረ በሚከፍልበት ኢንተርኔት በመጠቀሙ ሳቢያ ለምን ተብሎ ነው የ 15 ዓመታት እስር የሚበየነበት፡፡ምን በደለ ምን አጠፋ፡፡ ይህ ክፋትና ተንኮል ብቻ ሳይሆን ምቀኝነትም ሊባል ሲያንሰው ዕብደት ነው፡፡

ከዚህም ባሻገር የቴሌኮም አዋጅ፤በማንኛውም መመዘኛ ቢሆን ድጋፍ የማያገኝ ማወናበጃ ነው፡፡በሃገሪቱ ያሉት ህገች በመላ በቴሌኮም ላይ የሚፈጸሙትን ደባዎች ለማስታገስ ብቃት የላቸውም ይላል፡፡ ይህ አባባል ግን ድጋፍ የሚሆነው የማስረጃ ብጣሽ እንኳን የለውም፡፡ በነጻ የተካሄደ ጥናትም ሆነ ወይም በገዢውም ትብብር የተደገፈ የኢንተርኔት ማጭበርበር መጠነ ሰፊ መሆኑን የሚያሳይ ብልጭታም የለም፡፡ የሃገርን ደህንነት የሚጎዳ ጉዳይ በዚህ ሳቢያና መሳርያነት መፈጸሙን በተገቢው ማሳመን አልተቻለም ጥናት አልተደረገም፡፡ ሕዝባዊ አስተያየትና ድጋፍም ሆነ የባለሙያ ማረጋገጫ ጨርሶ አልቀረበበትም፡፡ሕጉ ከፍርሃት ውጪ፤ ከመረበሽ ያለፈ አንዳችም ሰበብ የለውም፡፡

ከዚህ የባሰና አስቸኳይ ትኩረትን የሚጠይቅ አሳሳቢ ጉዳይ አለ፡፡ ባለፈው እንደሚታወሰው፤በ2008 በጠራራ ጸሃይ ሰርሳሪ ሌቦች 16 ሚሊዮን ደላር የሚያወጣ የወርቅ ጥርብ ሰርቀው ያለአንዳች ችግር ከባንኩ ቅጥር ሲወጡ ተስተውሏል፡፡ ምንም እንኳን ድርጊቱ የውስጥ አዋቂወች ደባ መሆኑ ቢታወቅና በተወሰኑ ሰዎች ላይ ጣት ቢቀሰርም ምንም የተወሰደ የሕግ እርምጃ አልታየምም አልተሰማም፡፡ በ2007 የመንግስት ሃብት የሀነውን 600 ሚሊየን ደላር ከክልሉ በጅረወንድ ካዝና መሰወሩን ለማ አራጋው ይፋ ሲያደርግም መለስ ዜናዊ አፍንጫን ሲመቱት አይን ያለቅሳል ሆኖበት ለማን ከስራ አሰናብቶ በህዝብ ፊት ክልሉ ካሽ ገንዘቡን ሊያቃጥል ይችላል በማለት የጎዳና ምላሽ ሰጠ፡፡ የዚያ የተቃጠለ ገንዘብ አመድም አልተገኘም፡፡ በፌብሪዋሪ 2011 ለዓለም ገበያ ሊቀርብ የተዘጋጀው 10000ቶን ቡና ከመጋዘኑ እምጥ ይግባ ስምጥጥ ሳይታወቅ መቅረቱን መለስ ዜናዊ በይፋ ተናግሮ ነበር፡፡ በዚህ ሳቢያም ነጋዴዎችን ሰብስቦ በቪዲዮ በተቀረጸ ቃለ መለስ መልእክቱ ‹‹ለአሁኑ ይቅርታ እናደርግላችኋለን ምክንያቱም በዚህ ቡና መሰወር የሁላችንም እጅ ስላለበት አለ፡፡ ሁሉም አይፈራም ጋሜን እየዘፈኑ ቡና ጠጥተው ወደ የመጡበት ተመለሱ፡፡ ባለፈው ዲሴምበር ላይ ፋይናንሻል ግለባል ኢንተግሪቲ ሲዘግብ ኢትየጵያ አነስተኛ የኤኮኖሚ አቅም ያላት ሃገር በ2000 እና በ2009 መሃከል በህገወጥ መንገድ ሃገር እየጣሰ የወጣው 11.7 ቢሊዮን ዶላር፤ ይበላጣል› በማለት ነበር የዘገበው፡፡ እዚህ ላይ ስለሕግ እያለ የሚጣራ እንዳለ እናያለን፡፡ ባለፈው ወር መለስ ‹‹ብሄራዊ ጉዳየችን ስንመከት ዓላማ ያላቸውን ሰዎች ወደ ተራ ሌባነት ሲቀየሩ በማየት ገዢዎችን የሚጋፈጣቸው መተት ምን ይሆን››? በአፍሪካ ስለሚታየው የተራ ማጭበርበር ሁኔታ እስቲ እንመልከትና እኛም እንደመሪነታችን በዚያ ያለንን ድርሻ እናስላ‹‹ አለ:: ታላቅ ጥያቄ ነው›!› የኢትየጵያን ሕዳሴ ሊያመጣ የሚንደረደረው ሰውዬ ይህን ያነሳውን መሪ ጥያቄ መመለስ አይቸግረውም፡፡ለዚህም የተዘጋጀ መልስ ሊኖረው ይገባል፡፡ የጸረ ምዝበራን መታገያ መንገዱን ማስላቱና መተግበሩ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡እነዚህ መዝባሪዎች ሊያዙ የሚችሉበት መንገድ ሊነደፍ ይገባል፡፡ መዝባሪዎቹ በአደራ የተሰጣቸውን የህዝብ ሃብት በየግላቸው ወደ ውጪ ባንክ ሲያሸሹና ሲከለብሩበት፤ የገንዘብ ብክነቱ በሃገሪቱ ላይ የሚያስከትለው ችግር ተመዝኖ መቀጣጠርያ ሊወጣለት ሲገባ ቢመዘን ሚዛን የማይደፋውን የኢንተርኔት ካፌዎችን ለመዝጋት ህግ ማውጣትና ስካይፔን ለመከልከል መሮጡ ትርጉም አልባ አጉል ድንፋታ ነው፡፡

አዋጁ በየትኛውም አቅጣጫ ይተርጎም ቢባል መገናኛወችን ለማፈን፤ ስካይፕን የመሳሰሉ የቴክኖዎሎጂ ውጤተች በመከልከል የነዚህ ተጠቃሚ የሆኑ ሁሉ ደሞ ገዢውን መንግስት ለመጣል የተነሱ ናቸው ብሎ ማሰብ መንገዱን የሳተ አመለካከት ነው፡፡ ይህን ቴክኒዎሎጂ ለመገናኛነት የሚጠቀሙትም በጣት የሚቀጠሩ ናቸው፡፡ በሌላ መልኩ በስካይፕ ሲጠቀሙ የተገኙትን ይያዛሉ ይታሰራሉ በሚል ማስፈራራት ከዚሁ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ውጤትም መጠቀም ለእስራት እንደሚዳርግ ከአዋጁ አስቀድሞ በማስፈራሪያነት አውርቶ ማስወራቱ ለአዋጁ ትግበራ ቅስቀሳ ነው፡፡ ሪፐርተርዊዝ አውት ቦርደርስ እንደዘገበው፤ አዋጁ በጣም የተለጠጠ በመሆኑ ለመቆጣጠርና ፈር ለማስያዝ እጅጉን አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በውስጡ የተካተቱት አንዳንድ ጉዳየጭ የተለባበሱ ናቸው፡፡ በአንቅጽ 6 ስር ያለው ‹‹የሽብርተኝነት መልእክት ማለት ነው?›› በእጅ ስልኮች  ላይ የሚገኘው መለስ ዜናዊ ፈላጭ ቀራጭ ዲክቴተር ነው›› የሚለው የጥሪ ማንቂያ (በኢትየጵያ ደሞ ይህ በጣሙን የሚደመጥ የእለት ተእለት ጉዳይ ነው) እና የዚህ ተጠቃሚም ለ15 ዓመታት እስር ሊዳረግ ነው፡፡

የአንድ አዋጅ መንስኤው ነጻነትን ለማረጋገጥና ነጻና ዴሞክራሲያዊ የሆነ ፍትህ ለህዝቡ ለማስገኘት ሊሆን ይገባዋል፡፡

ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/category/al-mariam-amharic

http://ethioforum.org/?cat=24

 

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on June 25, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.