ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን ለጋዳፊ መንግስት እንዲዋጉ እየተገደዱ ነው

EMF – ቁጥራቸው ከ250 እንደሚበልጥ ይናገራሉ። በሊቢያ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰባት ሰአት (1 ኤ.ኤም) ላይ ያናገሯቸው የአድማስ ሬዲዮና የ ኢ ኤም ኤፍ ጋዜጠኞች ቃላቸውን በትክክል ለመቀበል ድምጻቸውን መቅዳት ነበረባቸው። ያሉበትን ሁኔታ አንዱ ካንዱ እየተቀበለ፣ አንዱ አንዱ ላይ እየተደራረበ፣ ሁሉም በሚናገረው ቋንቋ ሲያስረዳ ያሉበትን አሰቃቂ ሁኔታ ለመረዳት አይከብድም ነበር።

የኮሎኔል ጋዳፊ ደጋፊዎች “ወደ ማልታ እንወስዳችኋለን” ብለው አንድ ቦታ እንደሰበሰቧቸው የሚናገሩት እነዚሁ ስደተኞች፣ እውነት መስሏቸው ከተሰበሰቡ በኋላ፤ ከትራብለስ ከተማው 30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው፤ ቱሻ ወደሚባል እስር ቤት እንደወሰዷቸው ገልጸዋል።

ቱሻ ካስገቧቸው በኋላ ወንዶቹን እየመረጡ፣ መሳሪያ መተኮስ የሚችሉና የማይችሉ ካሉ በመጠየቅ ለመለየት ሞክረዋል። “አንችልም” ያሏቸውን ትለማመዳላችሁ በማለት ሲለዩዋቸው፣ “እኛ መዋጋት አንፈልግም፣ ስደተኞች ነን” ያሏቸውን ደግሞ እንደደበደቧቸው፣ ውስጥ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን፣ ሴቶቹን ጡታቸውን በኤሌክትሪክ ኃይል እያቃጠሉና እየገረፉ እንዳሰቃዩዋቸው በምሬት ተናግረዋል።

“ነገ እና ከነገ በስቲያ ምን እንደሚፈጠር አናውቅም” የሚሉት እነዚሁ ስደተኞች፣ የፕሬዚዳንቱ ሰዎች፣ ከመሃላቸው መልምለው ጦርነት መሃል ሊከቷቸው መዘጋጀታቸውን በመግለጽ “ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ድረሱልን” ብለዋል።

የሊቢያው ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ የሚከታተለው ሱዳን ያለው የኢትይጵያ ኤምባሲ፣ ዓለማቀፍ ቀይ መስቀል እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ምንም ያደረጉልን ነገር የለም፣ ያናገረን ሰውም የለም .. የሚሉት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ፣ ጨለማ እስር ቤት ሆነው ምግብ ከቀመሱ 12 ሰአት እንደሆናቸው፣ የሚያድሩበት ቦታም ከሽንት ቤት ጋር የተያያዘ መሆኑን፣ ሌሊትን ቀንም መተኛት እንደሌለ፣ እጅግ አስጊ ሁኔታ ላይ ነን ብለዋል።

ከመካከላቸው 17 ሴቶች እንዳሉ የተናገሩት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች “ምናልባት የሚደርስብን አይታወቅምና ስማችንን እንንገራችሁ” በማለት የሚችሉትን ያህል የሴቶችም የወንዶችም ስም ዝርዝር ሰጥተዋል።

ከመካከላቸው በጥይት የተመቱና የተደበደቡ መኖራቸውን፣ ዳቦ እንዲገዙላቸው ከዚህ በፊት ከመካከላቸው የላኳቸው  ሶስት ወንድሞቻቸው ወጥተው ሳይመለሱ መቅረታቸውንና በህይወት መኖራቸውን እንደሚጠራጠሩ ገልጸዋል።
ቃለ ምልልሱን ያድምጡ!

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

ጥሪ

ይህን የወገኖቻችንን ድምጽ እየሰማ ዝም የሚል አንጀት ያለው ማነው? አንዲት ስልክ መደወል አይከብደንምና ሊቢያ ለሚገኘው የቀይ መስቀል ቢሮ በስልክ ቁጥር (218) 917 422663 እንዲሁም ሱዳን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በስልክ ቁጥር (249) 11471156 እንዲሁም ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ የአፍሪካ ዴስክ ሃላፊ

Fatoumata LEJEUNE-KABA  Tel. (41 22) 739-7995

Communications Officer   Mobile: (41) 79 249-3483

Central, East, West and Southern Africa lejeunek@unhcr.org 

በተለይም ዜናው በአል-ጃዚራ እንዲቀርብ ቤን በኢሜይል አድራሻ Ben.Rayner@aljazeera.net  ዝርዝሩን በመጻፍ እና Tel: (+974) 4489-7446 / 4489-7451 / 4489-7449

በመደወል አቤቱታችንን በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እናቅርብ ስንል እንጠይቃለን።

Part Three

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

Part Two

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

Part One

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 28, 2011. Filed under AUDIO. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.