ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች – በአሜሪካ አንፀባራቂ ውጤት እያመጡ ነው!

EMF – ከቅርብ አመታት ወዲህ በአሜሪካ ከፍተኛ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወይም ነጥብ በመስቀል፤ ተማሪዎችን በመወከል ንግግር የሚያደርጉት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው የሚያኮራ ነው። እንዲህ ያሉ ቪዲዮዎች ሌሎችንም ልጆች ያበረታታል እና እንዲያዩት አድርጉ። በዚህ ቪዲዮ ላይ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት በአትላንታ ታዋቂ በሆነው ሞርሃውስ ኮሌጅ ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ይታያል። ንግግራቸውን እንደጀመሩ ታዲያ የኢትዮጵያዊውን ስም መጥራት ቢያቅታቸው፤ “ቀጭኑ እና አስቂኝ ስም ያለው” በማለት ስሙን ለመጥራት ትግል ሲገጥሙ ማየት ፈገግ ያሰኛል።
On this video we will watch president Obama struggling to pronounce በፀጋው ታደለ, one of the best distinguished graduate from Atlanta MoreHouse College.

ከዚያ በተረፈ ግን እንደስሙ በፀጋው የታደለው ተማሪ ባገኘው ከፍተኛ ውጤት ሌሎች ኢትዮጵያውያንንም የሚያኮራ ሆኗል። በነገርዎ ላይ በፀጋው የካፒቴን ታደለ ልጅ ነው። ወንድሙ እና ሌሎች ቤተሰቦቹ አትላንታ ነው የሚኖሩት። በፀጋው ስኮላርሺፕ አግኝቶ ከኢትዮጵያ ነበር የመጣው። በኮሌጁ የመጨረሻውን ከፍተኛ ነጥብ (ከአንድ A- በቀር በሙሉ A) አምጥቶ ነው የተመረቀው። ትምህርቱን ከመጨረሱ በፊት ከቢል ጌት ካምፓኒ ጋር ስለተፈራረመ ወደ ሲያትል ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላኛዋ በዳላስ ነዋሪ የሆነችው ሮዛ ኤሳው ናት። በአንድ ጊዜ ሶስት ዲግሪ አግኝታለች። በፖለቲካ ሳይንስ፣ ሰብአዊ መብት እና ኮሚዩኒኬሽን በአንድ ጊዜ ሶስት ዲግሪ በማግኘት ተመርቃለች። ነገሩን ለየት የሚያደርገው የሷ ሶስት ዲግሪ ማግኘት ብቻ አይደለም። በዚሁ ሳምንት እህቷ፣ እናቷ እና አባቷም በተለያየ ትምህርት ዲግሪ ጭነዋል። በአንስ ጊዜ ስድስት ዲግሪ አንድ ቤት ውስጥ ገባ – ማለት ነው።
Six degrees in one week – Ethiopian Family

የኢትዮጵያውያኑን ነገር ካነሳን ካልቀረ አንድ ነገር እንጨምር። ሰሞኑን ከተመረቁትና ከሁሉም ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ አንድ ኢትዮጵያዊ ተማሪ ንግግር ሲያደርግ ቤተሰቡ ለዚህ ስላበቁት አመሰገናቸው። እናቱን ግን በመጨረሻ ወቀሳት፤ “ትንሽ ቅር የሚለኝ ነገር እናቴ አማርኛ አለማስተማርሽ ነው” አላት። ስለሆነም ልጆቻችን የአሜሪካን ትምህርት እውቀት ብቻ ሳይሆን የአገራቸውን ባህል እና ቋንቋም እንዲያውቁ እንርዳቸው።
በዚህ አጋጣሚ በዚህ ወር ለሚመረቁት ኢትዮጵያውያን እና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ ኢ.ኤም.ኤፍ. ደስታውን ይገልጻል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 20, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች – በአሜሪካ አንፀባራቂ ውጤት እያመጡ ነው!

  1. ቤሉ

    May 21, 2013 at 10:19 AM

    on your last paragraph ,you need to mention the name of the graduate with valid source .