ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ሰኞ የወያኔን ኤምባሲ ይዘጋሉ

በህዝባችን ላይ የሚካሄደው አፈናና የረሃብ ግርፋት ያብቃ!! ለነፃነታችንንና ለሰብኣዊ መብታችን መከበር በጋራ እምቢ እንበል! በሚሉ ወቅታዊ መፈክሮች ዙሪያ ተሰባስበን በስልጣን ላይ ያለው የወያነ አረሜናዊ ስርዓት ለመቃወም

(February 7 ቀን 2011 ዓ.ም ከጥዋቱ 8፡30am ጀምሮ) በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት የእምቢታ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ስለሆነ ወገን ህዝብና ሀገር ወዳድ ለሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የቀረበ የህዝባችን የድረሱልኝ ጥሪ ነው።

ዛሬ በዓለማችን ዙሪያ ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለሰብኣዊ መብትና ለዲሞክሲ ስርዓት መከበር ህዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዞው፣ መድፍና ታንኪ ሳይበግራቸው እምቢ ለነፃነቴ ብለው አደባባይ በመውጣት በጉልበት ስልጣን ኮርቻ ላይ ተቀምጠው ለዘመናት ሲጨቁኑና ሲባልጉ የነበሩ አምባገነናዊ ስርዓቶች በህዝባዊ ዓመፅና በተባበረ ክንድ ሳይወዱ በግድ መንግለው ከዙፋናቸው ሲጥሉዋቸው በዓይናችን እያየን ነው።

ታዲያ እኛ ኢትዮጵያውያን በጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት ክቡር መስዋእትነት ማንነታችንን ጠብቀን ለጥቁር ዓለም ሁሉ የነፃትና የአልገዛም ባይነት ተምሳሌት ሆነን ታፍረንና ተከብረን የኖርነውን ያህል ዛሬ በተለያዩ ቦታዎች የዲሞክራሲና የነፃነት ብርሃን በሚፈነጥቅበት የሰለጠነ ዘመን እንዴት ወደኋላ ወደ ጨለማ ዘመን ተመልሰን የባርነት ተምሳሌት ለመሆን በቃን?
በዜጎቻችን ላይ እየደረሰው ያለው አፈና በሀገሪትዋ ያለው ሁኔታ ራሱ ተናጋሪ ሆኖ ሳለ በአንድ አምባ ገነናዊ መንግስት አገዛዝ ስር ወድቀን፣ በየተራ እየተመታን፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፍን፣ ዘላለም የበይ ተመልካችና የውጭ እጅ ጠባቂ ሆነን እስከመቼ እንኖራለን? ወያነ በመካከላችን የጥላቻ መርዝ እየረጨ እንዳንተባበር እኛን ሆድና ጀርባ አድርጎ ለያይቶ እየተገዛን የምንኖረው እስከመቼ ነው? የሚሉት ጥያቄዎችና ሌሎች አንገብጋቢ ሀገራዊ ጉዳዮች የማያሳስበው ኢትዮጵያዊ አለ ብሎ ለማመን ያስቸግራል።

የዚሁ ሰላማዊ ሰልፉ አላማና መነሻም “እሾኽ በእሾኽ ይወጣል” እንዲሉ በመካከላችን ሊፈጠሩ የሚችሉትን መለስተኛ ልዩነቶችን በመከባበርና በመደማመጥ አቻችለን ለጋራ ችግራችን ቅድሚያ በመስጠት አደባባይ ወጥተን በንሮ ውድነት እየተሰቃየ ከሚገኘው ከጭቁኑ ህዝባችን ጎን በገራ የምንቆምበት ወቅቱ አሁን መሆኑን ጊዜው እየነገረን ነው። ስለሆነም “የተደጋገመ የውሃ ጠብታ ዓለት ይበሳል” እንዲሉ በየጊዜው አደባባይ ወጥተን የምናሰማው ጭኾት የህዝባችን ጠላቶች

ዕድሜ ለማሳጠር ትልቅ ትርጉም አለውና በተጠቀሰው ቀን በጋራ እንሰለፍ እያልን ወገናዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ስንተባበር እናሸንፋለን !!

በዋሽንግተንና አካባቢዋ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማሕበረሰቦች በመተባበር

Info. 202 656 8070 Email – joinus@march4freedom.org

በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው።

International Dr ከእስራኤልና ቻይና ኤምባሲ በስተጀርባ።

February 7, 2011 ዓ.ም 8፡30am ይጀምራል

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 6, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.