ኢትዮጵያውያን በቦስተን ማራቶን ካሸነፉ በኋላ ከፍተኛ የቦንብ ፍንዳታ ደረሰ

(EMF) ሰኞ April 15 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. በቦስተን በሚደረገው አመታዊ የማራቶን ውድድር ላይ ከ25 ሺህ በላይ ሯጮች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ከተሳታፊዎቹበፊት መስመር ላይ ይታዩ ነበር። ውድድሩ ሲጠናቀቅ፤ የ23 አመቱ ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ደሲሳ በንቲ 1ኛ ሆኖ ጨረሰ። ኬንያዊው ሚካ ኮጎ 2ኛ፤ እንዲሁም ሌላው ኢትዮጵያዊ ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም 3ኛ ወጥቷል። በሴቶቹም በኩል ኬንያዊቷን በመከተል ኢትዮጵያዊቷ መሰረት ኃይሉ 2ኛ ወጥታለች። ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች እና ደጋፊዎቻቸው አካባቢውን ከለቀቁ ከሁለት ሰአታት በኋላ ያልተጠበቀ ነገር አጋጠመ።

ውድድሩ ከተጠናቀቀ ከሁለት ሰዓታት በኋላ፤ ሌሎች አትሌቶችም እየሮጡ ወደ መጨረሻው መስመር ላይ እየተጠጉ ነበር። ሆኖም በድንገት ከሩጫው መጨረሻ አጠገብ ከሚገኘው ፌርማውንት ኮፕሌይ ፕላዛ የፍንዳታ ድምጽ ተሰማ። ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሰዎች ተጎዱ፤ አንዳንድ አትሌቶችም ሲወድቁ ታየ። ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ ደግሞ ሌላ ትልቅ ፍንዳታ ተከተለ። አካባቢው በጭስ ተሞላ።

Multiple outlets, law enforcement officials, and President Obama are responding with news that a horrific looking scene made clear on Monday in downtown Boston

Multiple outlets, law enforcement officials, and President Obama are responding with news that a horrific looking scene made clear on Monday in downtown Boston

ፖሊስ ትንሽ ቆይቶ እንደገለጸው ከሆነ፤ ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሞተዋል፤ ከመቶ በላይ ሰዎች ተጎድተዋል; ከ6 በላይ ሰዎች አሰቃቂ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከደቂቃዎች በኋላ ደግሞ፤ ከማራቶኑ ስፍራ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው ጆን ኤፍ ኬኔዲ ላይብረሪ አካባቢ ሌላ ፍንዳታ ተሰማ።

በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች ስፍራውን በፍጥነት ዘጉት። ከዚያም የእጅ ስልኮች እንዳይሰሩ ተደረገ። ዘግይቶ እንደተደመጠው ከሆነ፤ የስልክ መስመሮቹን የዘጉት፤ የተጠመዱት ቦንቦች በሴል ፎን አክቲቬት ሊሆኑ የሚችሉ ከሆነ ተጨማሪ አደጋ እንዳይደርስ ነው ተብሏል። ጥቂት ቆይቶም ሌሎች ሁለት ሳይፈነዱ ከሽፈዋል። የተገኙት ቦንቦችም ወታደራዊ ኃይሎች የሚጠቀሙበት ሳይሆን፤ በቤት ውስጥ የሚሰሩ ግን አደገኛ የቦንብ አይነቶች ናቸው።

እስከምሽት እና ለሊቱን የአሜሪካ ሚዲያዎች በዚህ ፍንዳታ ጉዳይ ልዩ ልዩ ትንታኔዎች ሲሰጡ ነበር የቆዩት። አንዳንዶች የፍንዳታውን ምንጭ “አል ቃይዳ ሊሆን ይችላል” ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ የአየርላንድ አሸባሪዎች ላይ አነጣጥረዋል። አመሻሹ ላይ ፕሬዘዳንት ኦባማ በጥንቃቄ ግን ድርጊቱን ከ“ሽብርተኝነት” ጋር በማያያዝ አጠንክረው አውግዘዋል። “ማን እንዳደረገው አናውቅም። ሆኖም ድርጊቱን የፈጸመውን ግለሰብ ወይም ቡድን እንከታተላለን፤ እርምጃም እንወስዳለን።” ብለዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት የመጨረሻ ደቂቃ ድረስ ፍንዳታውን ማን እንዳደረገው አልታወቀም።

የቦስተን፣ ማሳቹሴትስ ክፍለ ግዛት ይህንን እለት “የአርበኞች ቀን” በማለት ላለፉት 238 አመታት በልዩ ልዩ በዓላት ሲያከብሩት ቆይተዋል። ይህ የአሁኑ አይነት ሁኔታ ግን በከተማው ፈጽሞ አጋጥሞ አያውቅም።

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 15, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.