ኢትዮጵያዊው ቢንያም አሰፋ ከነቤተሰቡ ተገድሎ ተገኘ

(EMF) ከከተማው ራቅ ያለ ቦታ ነው የሚኖሩት – የ40 አመቱ ኢትዮጵያዊው ቢንያም አሰፋ፣ ጣልያናዊቷ ሚስቱ እና ልጆቹ። ድንገት በደረሰባቸው ጥቃት ባል እና ሚስቱ ከሶስት ወር ልጃቸው ጋር ሲገደሉ የአምስት አመት ልጃቸው ግን ተደብቃ ለማምለጥ ችላለች። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ፤ የ5 አመቷ ልጅ ከተደበቀችበት ወጥታ ወደ ጎረቤት በመሄድ፤ “ቤተሰቦቼ ተጎድተዋል” ብላ ነገረቻቸው። ከዚያ በኋላ ነው ለፖሊስ የተደወለውና አሳዛኙ ድርጊት ይፋ የሆነው።
ቤን አሰፋ
በመጀመሪያ የሜሪላንድ ነዋሪ የሆኑት የቤን አሰፋ ቤተሰቦች የደረሰው አደጋ፤ የርስ በርስ ግጭት ሊሆን ይችላል፤ በሚል ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቶ ነበር። ሆኖም ፖሊስ ዛሬ እንደገለጸው ከሆነ፤ ግድያው በሌላ ወገን የተፈጸመ ነው ተብሏል።

ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ይፋ አላደረገም። ይልቁንም የሟች (የቤን አሰፋ ሚስት) ቤተሰቦች ከጣልያን አገር ይገባሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው። እነሱ ወደ አሜሪካ ከገቡ በኋላ ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሁለቱም ባል እና ሚስቶች የባዮ ሜዲካል ህክምና ሳይንቲስቶች ነበሩ።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 23, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to ኢትዮጵያዊው ቢንያም አሰፋ ከነቤተሰቡ ተገድሎ ተገኘ

  1. Girum Teshome

    November 23, 2013 at 11:39 PM

    እንዴት ነው ዘገባችሁ የትኛውን እንቀበል እባካችሁን (ኢትዮጵያ ሜዲያ ፎረሞች)ስህተቱ ከናንተ ከሆነ ባስቸኳይ እርማት ይድረግ::ስለዚህ ዜና ኢትዮጵያን ሪቭው ዘ ሀበሻን ዋቢ አድርጎ እንዲህ አስነብቦናል ብዙ ልዩነት አለው ይመልከቱት እስኪ?http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9772