ኢትዮጵያዊነት – ሄኖክ የሺጥላ

ኢትዮጵያዊነት በተቃርኖ የተሞላ የግሳንግስ ስብስብ አይደለም። ኢትዮጵያዊነት የወጪት ሰባሪዎች ትግል፣ ለኔ በገሌ ነው ባዮች ምክር አይደለም። ኢትዮጵያዊነት በበግ ጸጉር ቡክርናውን እንደቀውማው ያዕቆብም ( ” አታላይ ማለት ነው”) አይነትም አይደለም። በጎሳ አሽክላ ተተብትበን፣ በቂም ቆመን፣ ጭረት አመርቅዘን ቁስል አርገን ፣ የዛሬ ውድቀታችንን ፣ የዘምን ምክነት አስመስለን፣ ላለመቻላችን መወጣጫ፣ ላለመቆማችን የ ምክንያት መቆናጠጫ ብንፈልግ ፣ ካለፈ ጥፋትም ሆነ ሕዝብ ካለፈለት እውነት ጀርባ መዶለታችንን እስካልተውን ፣ የድርሻችንን ለመወጣት ታጥቀን እስካልተነሳን ድረስ ፣ ትግላችን እንደ እስከ ዛሬው ” ለ አፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል” ሆኖ ስለመቀጠሉ አዋቂ መሆን አይጠይቅም። Continue Reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 11, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to ኢትዮጵያዊነት – ሄኖክ የሺጥላ

 1. አቢይ ኢትዮጵያዊ-ሥጋዊ

  May 11, 2014 at 12:10 PM

  ይገርማችኋል አንባቢዎቼ ሆይ፥
  ይህቺ የሔኖክ የሺህጥላ”ኢትዮጵያዊነት” ጦማር የምትነበብ ብቻ ሳትሆን የምትደመጥ እና የምትታይ ልትሆን ይገባታል።በተለይም ኢትዮጵያ ካስተማረቻቸው ምሁራን መካከል የተኙት ሲበዙ “ተዉ አስገቡኝ ዛሬ”ያሉትም ሾሃቸውን ደብቀው ሊታገል ያለውንም ከመነጀስ አይታቀቡም፤ለነዚህ ዓይነት ምሁራን ይህ ጦማር መድኀኒት ነው።

  ስንት ዕውነቶች መነገር አሉባቸው???ስለዓለም ብናወራ ቃላት እየመረጥን የማይጠገብ ንግግር ብናደርግ ነገሩን እስካልቀየረን ድረስ ወሬያችን ሁሉ ፍሬ አልባ ሆኖ እናገኘዋለን።ልቦና ይስጠን እንጂ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣት ጀግኖች ይመጣሉ፤ሔኖክ የሺጥላም አንዱ ነው።

  ጠላቶቻችን እነዚህን የጉጅሌ ቡድኖች አዲስ አበባ አስገብተው እንደ አረም ሲዘሯቸውና በጋራ መርዛቸውን መርጨት ሲጀምሩ መጀመሪያ ያነጣጠሩት*”ኢትዮጵያዊነት”*ላይ ነበር።በዚያንም ወቅት በጣም ጥቂቶቻችን ብቻ ነበርን የሥጋ ትልነታቸውን በግልፅ የተገነዘብን። ስለተገነዘብኩም ነበር በግል ኢትዮጵያዊነቴን አላስነካም በማለት በዚያ የኑሮ ውድነት እና በዘመነ-ወያኔ አሳዳጅነት ወቅት “የአዲስ ዘመን እንኳን አደረስዎ”ካርድ ያዘጋጀሁት።ከእነዚያ የታደሉት ካርዶች ውስጥ የአምስት ዓመታት የቀን መቁጠሪያ ስሌትን የያዙ ሲሆኑ”ግንቦት ፳” ደግሞ የ”ሰላም”ሳይሆን የ”አብዮት” በዓል መሆኑን አፅንዖት ይሰጣል።

  ወደተነሳንበት ርዕስ ስንመለስ የተዘጋጀችው ካርድ ኢትዮጵያዊነትን በ”መንፈሳዊ” እና በ”ሥጋዊ” ሕይወታችን ውስጥ አድርገን እንድንመለከተው የምታግዝ የግጥም መልዕክት ይዛለችና ለስደት ዳርጋኛለች:: ሔኖክ የሺህጥላም ይህንን የትግሌን ሰበብ አስታወሰኝ፣ተቛደሷት።

  ወንድሜ ሔኖክ ጠላት እና ወዳጅህን ስለለየህ ብርታቱን እግዚአብሔር ይስጥህ።በርታ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ኢትዮጵያዊነቴ፤ሥጋዊ እና መንፈሳዊ ተብላ ተከፍላለች።

  ኢትዮጵያዊነቴ;
  መንፈሳዊ ፤
  +++++++
  የትንቢት ሕይወቴ
  የማህፀን ቤቴ
  ሰማያዊ ዕድሌ
  ሥጦታ የግሌ
  ዘመን የማይሽረው
  ትውልድ የሚያኖረው
  ክቡር ነፃነቴ
  ልደቴና ሞቴ

  ኢትዮጵያዊነቴ
  ሥጋዊ ፤
  =======
  የሰው ዜግነቴ
  በደሜ ባጥንቴ
  በውስጥ ሰውነቴ
  በመልኬ በፊቴ
  በመላ አካላቴ
  የኔ ለእኔነቴ
  የተፈጥሮ ሀብቴ
  አለኝታ እና መብቴ

 2. ዝም አልልም

  May 11, 2014 at 1:19 PM

  ሄኖክ
  ከዚህ በተሻለ በተሳካ ሁኔታ መግለጽ አይቻልም::ወንድሜ ዛሬ ያገራችንን ውስብሰብ ችግር ለመፍታት በሚደረገው ትግል አንድ እርምጃ ወደፊት እንድንል ከፈለግን አንተ እንዳስቀመጥከው ማለሳለስና ማድበስበሱ ቁሞ ነገሮችን በግልጽ በስማቸው መጥራቱ ለትግላችን ጥራትና ለተጠናዎዘን እንዲህ ካልኩ እከሌን አስቀይማለሁ አባዚ ማብቂያ ወሳኝ ነው::

  ምስጋና ይግባህ ውድ ያገር ልጅ!

 3. Dagmawi

  May 12, 2014 at 6:51 PM

  አንጀቱ ያረረ ሄኖክ የሺጥላ በድፍረት በመናገሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ከወያኔ ይልቅ ትግሉን በማኮላሸቱ ስራ ላይ የተሰማሩት በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉ እንደ እንጉዳይ የፈሉት ተቃዋሚዎች ትግሉን ለመምራት ዝግጁ መሆን ብቻ ሳይሆን ወደላይ ከመግፋት ወደጎን መጋፋትን መሻኮትን የመረጡና አጋጣሚው ከፈቀደላቸውም ወደ ምኒሊክ ቤተመንግስት በአቋራጭ ለመግባት የሚመኙ ስለሆኑ ነው።አሁን ደግሞ እንደ ፋሽን ጥርስ የሌለው የማይናከስ ሰላማዊ ሰልፍ ብለው ህዝብ ያምሳሉ። ወይ አያድጉ ወይ አያረጁ ወይ ልብ አይገዙ ወይ ገለል አይሉ እንዲሁ የወያኔን እድሜ ማራዘም ብቻ ሆኗል ሥራቸው። ልቦና ይስጣቸው ከማለት ባሻገር ሌላ ምን ማለት ይቻላል።