ኢቲቪ የአንድነት ፓርቲን ስም ማጥፋቱ በፍርድቤት ተረጋገጠ

———————————-
ኢቲቪ ተመጣጣኝ የማስተባበያ አየር ሰዓት ለአንድነት ፓርቲ እንዲሰጥ ታዟል
——————————
የዘገየ ፍትህ እንደተሰጠ ባይቀጠርም በአንድነት ፓርቲ እና በኢትጵያ ቴሌቪዥን መካከል “አኬልዳማ ዘጋቢ ፊልምን አስመልክቶ ለነበረው 3 አመታትን ለፈጀ ክርክር ለአንድነት ፓርቲ ፈርዶ መቋጫ ሰጥቶታል በመሆኑም ኢ.ቲ.ቪ የአንድነት ፓርቲን ስም በማጥፋቱ ተመጣጣኝ የማስተባቤ አየር ሰዓት ለአንድነት እንዲሰጥ ፍርድቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
ችሎቱን የተከታተለው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀብታሙ አያሌው ለፍኖተ ነፃነት “ውሳኔ የአንድነት ፓርቲ ክስ ኢ.ቲቪ የሰራው አኬልዳማ ዶክመንተሪ የፓርቲውን መልካም ስም እና ክብር ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገወጥ ድርጊት ነው የሚል ነበር፡፡ ፍርድ ቤቱም በአንድነት ላይ በደል ተፈፅሟል ሲል ኢቲቪ ጥፋተኛ ነው ያስተባብል ሲል ወስኖበታል፡፡” በማለት አስረድቷል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 1, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.