ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል? ከተመስገን ደሳለኝ

ብርዱ የጥቅምት ነው፤ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚያንቀጠቅጥ ኃይለኛ ቅዝቃዜ። አዲስ አበባ ገና ከእንቅልፏ በመንቃት ላይ ነች። ለስራ የቸኮሉ መንገደኞች ትራንስፖርት ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይካለባሉ። ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ “መገናኛ ራዲዮ” በያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ። የትራፊክ ፖሊሶቹ ስራ የበዛባቸው ይመስላሉ። 12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ሲል በሁለት የሞተር ብስክሌት በተፈናጠጡ የትራፊክ ፖሊሶች ፊት አውራሪነት አንዲት ሳይረን የተገጠመላት የፖሊስ ታርጋ የለጠፈች መኪና የ”መንገድ ልቀቁልኝ” ጩኸቷን እያንባረቀች አቋርጣ በማለፍ ወደ ሳር ቤት አቅጣጫ ከነፈች። ሶስት “ቪኤት” መኪና ሰለሱ።

PDF ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል?

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 11, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.