ኢሀድግና አማራ

ኢሀድግ ስንል በነ አቶ መለስ የሚመራውን የትግራይ ነጻ አውጪ ድርጅት ማለታችን ነው፤ ኢሀድግ የሚለው ስም ሌሎች ብሄረሰቦችን ያካተተ ለማስመሰል የተፈጠረ ማደናገሪያ ነው፤ ከየብሄረሰቡም ለሆዳቸው ያደሩ የነ አቶ መለስን ትዕዛዝ ያለማወላወል የሚተገብሩ ሰዎች ጥርቅም ነው።

ወደ ተነሳሁበት አርዕስት ልመለስና ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ ከ 78ሺህ ሰዎች በላይ (አማሮች) ለዓመታት ከኖሩበት ቦታ (ጉራ ፉርዳ ወረዳ ቤንች ማጂ ዞን ደቡብ ክልል) ያለ ምንም ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ተወርሰው፤ እንደተባረሩ በደረሰን ዜና ምክንያት ነው፡ ትዕዛዙ  ከነ አቶ መለስ ቢሮ ለመፍለቁ ቀጥተኛ መረጃ ባይኖረንም ሁኔታውን ለመከላከል ምንም እርምጃ ባለመወሰዱ እንዲያውም ስደተኞቹን እያፈሱ ማጎርና ወደ አልታወቀ ቦታ መውሰድ፣ በፌዴራል ማስከበብ የመሳሰሉት እርምጃዎች፤ የተባረሩትንም ለመርዳት ጥረት ባለመደረጉ፣ ትዕዛዙ በቀጥታ ከአካባቢው አስተዳደር በመምጣቱና ከዚህ በፊት የተደረገውንም በማሰብ የነሱ ስራ ነው ለማለት እደፍራለሁ፤ ለድፍረቴ አንዳንድ ከዚህ ቀደም በአማራው ሕዝብ ላይ የነ አቶ መለስ ያደረሰውን በደል እጠቅሳለሁ

  • አርባ ጉጉ 480 ሕጻናት፣ አሮጊቶች፣ ሽማግሌዎች በወያኔና በግብረአበሮቹ አማራ ስለሆኑ ብቻ ተጨፈጨፉ
  • የቀድሞው የወያኔ አሽቃባጭ ደጋፊና ውስጥ አዋቂ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገ/አብ በሰጡት ቃለ ምልልስ (march 09/2009) በበደኖ፣ በአርባጉጉና በደቡብ ምስራቅ ኢ/ያ ከ 40000 በላይ አማሮች ተጨፍጭፈዋል፡ ለበደኖና ለአርባ ጉጉው ጭፍጨፋ ዋናው ተጠያቂ ዛሬ ወደ እግዚአብሄር ተመልሻለሁ እያሉ የሚያሾፉዩት የሽግግር መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ናቸው ፤ታምራት ላይኔ ሶማሌ ክልል ሄዶ “ ምንትስ ሶማሌ” እያለ ሲሰድብህ የኖረውን እና ሊገዛህ የመጣውን ነፍጠኛ የመበቀያህ ወቅት አሁን ነው ነጸብራቅ ገጽ 73
  • April 2008 ሰፊ ግዛት ከአማራው ክልል ተነጥሎ ለትግል ባለውለታቸው ሱዳን ተሰጥቷል (ቋራ ወረዳ፣ ነፍስ ገበያ…) ሰኔ 26 1999ዓም 17 የኢትዮጵያ መንደሮች ለሱዳን እንደተሰጡ የጋዳሪፍ አስተዳዳሪ አብዱርአህማን ኢል ከድር አስታወቁ፤ (ተቃዋሚ ድርጅቶች   ሱዳን ውስጥ እንዳይደራጁና ወያኔን እንዳያጠቁ የተደረገ መላ ነው፡ ኢትዮጵያን ለማፈራረስም ከሚጠቀሙት ዘዴ በየአቅጣጫው ጠላትን ማበርከት ነው )
  • በ2007 የአማራውን ክልል ባጀት ለመዝረፍ እንዲያመችና የክልሉን ባጀት ወደ ራሳቸው ሕዝቦች ለማዛወር በታቀደው መሰረት የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥሩ በ2.4ሚሊዮን እንዳነሰና የሕዝቡ ቁጥር ዕድገትም ሌላው ክልል 2.5% ሲሆን የአማራ ክልል ግን ወደ 1.7% ዝቅ ተደርጓል
  • የአገሪቱን ክልሎች በባህልና በቋንቋ ሲከልሉ ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ከፊል ሸዋ ሰለበዛባቸው ገምሰው ወደ ትግራይ የደመሩት ሳያንስ በታሪክ የተሌዩ ናቸው በሚል ዋግ ሂመራን (አማርኛ ተናጋሪ)፣ ከጎጃም አዊ ዞንን ነጥለው አውጥተዋል
  • ዛሬ በአማራው ላይ የተነሳውን ጠቀስኩ እንጂ ጋምቤላ አኙዋኮች ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ በ genocide watch ተመዝግቦ ይገኛል፤

ይህ የወሮበላ መንግስት ለቻይና ለሕንድና ለአረብ ሀብታሞች መሬት ሲቸበችብ የአገሪቱ ሕዝቦች ግን ከኖሩበት አካባቢ እንዲፈናቀሉ፣ የውስጥ የድብቅ መመሪያ ያወጣል፤ በሕዝቦች መሃል መተማመን እንዲጠፋና እርስ በርስ ሲናጩ የስልጣን ግዜውን ለማራዘም የዚህ ዓይነት ተንኮል ይከተላል።

እንዘርዝር ከተባለ መቀጠል ይቻላል ነገር ግን ምን መደረግ አለበት የሚለው ላይ ማተኮር አለብን፤ የአማራውን በደል ለመታገል ከተነሱት ጥቂት ቆራጥ ሰዎች ፐረሮፌሰር አስራት ወልደየስ ይገኙበታል፡ ዋና ዓላማቸውም ከላይ የተዘረዘሩትን ዓይነት በደሎችን ለማስወገድ ነበር፤ እኚህ ቆራጥ መሪ ከበደኖና ከአርባ ጉጉ ጭፍጨፋ ማግስት በ1984 መህአድን ይመሰርታሉ፤ ድርጅቱን ሲመሰርቱ ዓላማው የአማራን የበላይነት ለማንጸባረቅ ሳይሆን የሚደርስበትን ጭፍጨፋ፣ ስደትና አስተዳደራዊ በደል ለመግታት ነበር፤ ነገር ግን በወያኔ እስር ቤት ማቀው፣ በወቅቱ ሕክምና እንዳያገኙ ተከልክለው የጀመሩትን ትግል ከግብ ሳያደርሱ ሕይወታቸው አለፈ፤ የተረከቧቸውም ድርጅቱን አፍርሰው በምትኩ ሌላ ድርጅት መስርተው እንኳን የአማራውን የድርጅታቸውን መብት እንኳን ማስከበር አቅቷቸው፤ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆነው ይገኛሉ።

የወያኔ አስተዳደር የሚገባው ቋንቋ ጥይት ብቻ ነው፡ በሰላም ያልተደረገ ሙከራ የለም  ወያኔ ግን ጭራሽ እንደ ፍራቻ አይቶት ሕዝቡን በራሱ አገር ባይተዋር አድረጎት ይኖራል፤ ስለዚህ የሚኖረው አማራጭ በሚገባው ቋንቋ ማናገር ነው፤

ይህ መንግስት ናላው በዘር የዞረ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይህን የዘር ካርታ አሽቀንጥሮ መጣል ይኖርበታል፤ በተለያየ ዘር የተደራጁ ድርጅቶች ይህንን በደል በግልጽ ሊቃወሙና አቋማቸውንም ሊያሳውቁ ይገባል፤ ስልጣን ቢይዙ ከወያኔ ሊለያቸው የሚችለው አቋም ዋንኛው ይሔ መሆን አለበት፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ መኖር፣ መማር ፣መስራት፣ መነገድ ወዘተ ሙሉ መብቱ ሊሆን ይገባል።

ወያኔ አማራ ላይ ጥላቻ፣  ሌሎች ጎሳዎች ላይ ንቀት ይታይበታል፤ ከራሱ ጎሳ ውጭ ያለም ከራሳቸው በታች አድረገው ይቆጥሩታል፤ የአገሪቱ መሪ የራሳቸውን ዘር ከወርቅ የነጠረ በሚል ተናግራዋል፤ በጎሳቸው መኩራታቸው ሳይሆን ቅር የሚያሰኘን ለሌሎች ያላቸው ደካማ አመለካከት ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊያውቅ የሚገባው በመሃከላችን ያለው አንድነት (በጎሳዎች መሃከል) ጥንካሬአችን መሆኑን ነው አለበለዚያ በየተራ እንመታለን፤ (divide and rule) ድል በድሎት አይመጣም ሁላችንም መስዋእትነት መክፈል መቻል አለብን፤ ለትጥቅ ትግል የተነሱትን፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን በሃሳብ፣ በገንዘብ፣ በዕውቀት በመሳሰሉት መርዳት መቻል አለብን፤ በተቻለ መጠን የወያኔ የንግድ ተቋማት ላይ ማዕቀብ መጣል አለብን፣ የወያኔ ረዳቶችን ማግለል አለብን ወዘተ.  ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሚሰራውን ነገር ወይ ነዶ እያሉ ከንፈር መምጠጥ የወያኔን ዕድሜ ያራዝማል እንጂ ትግሉን የታለመበት እንዲደርስ አይረዳውም።

የሰማነውን፣ያነበብነውን ከልቦናችን ያሳድርልን

ታዛቢው

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 15, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.