አድማስ ሬዲዮ ስድስተኛ አመት በአትላንታ ሊከበር ነው

(ትዝታ በላቸው እና ሼክስፒር ፈይሳ በክብር እንግድነት ይገኛሉ)
ከተመሰረተ ስድስት አመት የሆነው የአትላንታ አድማስ ሬዲዮ 6ኛ አመቱን ፌብሩዋሪ 26 ቀን፣ 2012 አትላንታ ላይ ያከብራል። በማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው የአድማስ ሬዲዮ፤ በዚህ ዝግጅት ወጣቷን አርቲስት ዘውዲን የሚያቀርብ ሲሆን፤ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ወ/ሮ ትዝታ በላቸውን እና ከሲያትል ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳን በክብር እንግድነት ይዞ የሚቀርብ መሆኑን በተለይ ለኢ.ኤም.ኤፍ. ገልጿል።

Place – Clarkston Community Center
Date – February 26, 2012
Time – 5:00 PM
Address – 3701 College Ave.
Clarkston, GA – 30329
Entrance fee- $20.00
ከአድማስ ሬዲዮ የደረሰን ሙሉ መግለጫ ከዚህ የሚከተለው ነው።

——————————————–
የአድማስ ሬዲዮ 6ኛ ዓመት ሊከበር ነው።

ከተቋቋመ 6 ዓመታት ያስቆጠረው አድማስ የመረጃና የመዝናኛ ሬዲዮ ፣ እሁድ ፌብሩዋሪ 26 ቀን 2012 ዓ.ም 6ኛ ዓመቱን ያከብራል።

ባለፉት ስድስት ዓመታት በሳምንት የ 4 ሰአት ዝግጅት በማቅረብ ማህበረሰቡ በቋንቋው ጠቃሚ መረጃዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በህግ ፣ በጤና ፣ በትዳር፣ በልጆች አስተዳደግ፣ በሞርጌጅ ጉዳዮች፣ በኢሚግሬሽንና በሌሎችም የማህበረሰብ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ፕሮግራሞችን በመስራት ህብረተሰቡ ማወቅ ያለበትን እያሳወቀ ይገኛል። በአገራችን በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም የሚከሰቱ አንኳር ጉዳዮችን በመዳሰስ አድማጮች ከጊዜው ጋር እኩል እንዲራመዱ ጥረት ያደርጋል።

አድማስ ሬዲዮ ለ6ኛው ዓመት በዓሉ ሲደርስ፣ ለዚህ ቀን መድረስ የሁሉም ድጋፍ አለበትና ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው። ፌብሩዋሪ 26 በአትላንታ ፣ ክላርክስተን ኮሚኒቲ ሴንተር፣ ከ 5-9 ፒ ኤም በሚከበረው በዓላችን በክብር እንግድነት ወይዘሮ ትዝታ በላቸው ፣ የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ እና ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ከሲያትል እንደሚገኙ ስናስታውቅ በደስታ ነው።

አድማስ ሬዲዮ ዘወትር ቅዳሜ ከ 2pm -6pm (በአትላንታ አቆጣጠር) ፣ በኢንተርኔት www.admasradio.info በሬዲዮ (1100AM) እና በስልክ (951) 262 4343 Code 193902# ላይ በመላው ዓለም በቀጥታ ይተላለፋል።

አድማስ ሬዲዮ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 25, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.