አዲስ አበባ ውስጥ በፖሊስ የታሰሩት የአንድነት አባላት ከ42 ደርሰዋል

ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2005 ዓ.ም መንግስት የአንድነት ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን የወረዳ አመራሮችንና አባላትን በዘመቻ ማሰር ጀምሯል፡፡ እስከአሁኗ ሰዓትም 42 የሚሆኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት በፖሊሲ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች ተዘዋውረው እንደዘገቡት 42 የሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አባላት በፖሊስ እንዲታሰሩ ተደርጓል፡፡ የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ እያሰራጨ ያለውን ህጋዊ በራሪ ወረቀት ለህዝብ በማደላቸው የተያዙት አባላት ከአዲስ ከተማ 15፣ ከጉለሌ7 ፣ ከየካ 9 እንዲሁም ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ናቸው፡፡

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ንቅናቄ የተደናገጠ የሚመስለው ኢህአዴግ በየአካባቢው የአንድነት አባላትን ምክንያት እየፈለገ ማገትና ማሰሩን ገፍቶበታል፡፡
ዛሬ ከታሰሩት 42 የአንድነት ፓርቲ አባላት መካከልባለፈው ሳምንት ቄራ አካባቢ ተመሳሳይ ወረቀት ሲበትኑ በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ታስረው የነበሩት ስንታየሁ ቸኮልና ዳንኤል ፈይሳ ዛሬም በድጋሚ ህገወጥ እስር እንተፈፀመባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read full story from fnotenetsanet

አንድነት ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የደሴ ህዝብ ያሳየው ተሳትፎ – Watchvideo below:

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.