‘አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሞቱ ኢትዮጵያ በእስላምና አስተዳደር ስር ልትወድቅ ትችላለች’ (እንዴት?)

(ኢ.ኤም.ኤፍ. ልዩ ትንታኔ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ይሞታሉ ተብሎ ሳይጠበቅ ነው፤ ህይወታቸው ያለፈው። ይህ ድንገተኛ ሞት ደግሞ ምክትላቸውን አቶ ኃይለማርያምን የአገሪቱ ከፍተኛ የስልጣን ባለቤት አድርጓቸዋል። ሆኖም ሰው ተሰባሪ በመሆኑ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር በድንገት ከዚህ አለም በሞት ቢለዩ በኢትዮጵያ ውስጥ ሊኖር የሚችለውን የስልጣን ገጽታ አስበውት ያውቃሉ? የዛሬው የኢ.ኤም.ኤፍ. ልዩ ትንታኔ በዚህ ላይ ያተኮረ ይሆናል። (ይህ ትንታኔ “ቢሆንስ?” ከሚል መነሻ የተዘጋጀ እንጂ፤ ከሃይማኖት ድርጅት ወይም አማኞች ጋር በተቃራኒ በመቆም የተዘጋጀ አይደለም)

በአንድ አገር ውስጥ በከፍተኛ እርከን ላይ የሚገኙት የአገሪቱ መሪ፣ ምክትሉ፣ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣ መከላከያ ሚንስትሩ፣ ኤታ ማዦር ሹሙ፣ የገንዘብ ሚንስትር፣ እና የሲቪል ሰርቪስ በዋናነት ይጠቀሳሉ። በኢትዮጵያ ሁኔታም እነዚህ ባለስልጣን እና ሚንስትሮች ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። ቀደም ሲል እንዳልነው፤ ዋናው የአገሪቱ መሪ ቢሞት፤ ምክትሉ ይተካዋል። ሁለቱም ቢሞቱ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ (አፈ ጉባዔ) ስልጣኑን ይረከባል። ይህ ካልሆነም ወታደራዊው ክፍል መከላከያው እና ኤታ ማዦር ሹሙ በጦር መሳሪያ ጭምር በመታገዝ የአገሪቱን ስልጣን የመውሰድ አቅም አለው። ከነዚህ መካከል ማናቸውም ስልጣን ቢይዙ ደግሞ፤ የገንዘብ ምንጫቸው እንዳይደርቅ የገንዘብ ሚንስትሩን ከጎናቸው ማድረግ የግድ ነው።

ይህ እንዳለ ሆኖ… በድንገት ከፍተኛ ባለስልጣን ቢሞት ወይም ቢሞቱ፤ በአገሪቱ ውስጥ የሚደረገው እንቅስቃሴ እንዳይቆም ያስፈልጋል። ለዚህም የሲቪል ሰርቪስ ሰጭ መስሪያ ቤቶች ስራቸውን እንዲቀጥሉ፤ ሰራተኛው ወደ ስራ እንዲገባ፣ ነጋዴው ንግዱን እንዲከውን ማስደረግ ማስፈለጉ አይቀርም። እዚህ ድረስ ከተግባባን… “ለመሆኑ እነዚህን ከፍተኛ እና ቁልፍ ቦታዎች የያዙት እነማናቸው?” የሚል ጥያቄ ሊመጣብዎ ይችላል። ከዚህ ቀጥሎ እናስተዋውቃችሁ።

“የሰይጣን ጆሮ አይስማና…” አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሞቱ ተተኪያቸው፤ አቶ ደመቀ መኮንን ሃሰን ናቸው። ደመቀ መኮንን ሃሰን የወሎ ተወላጅ ሲሆን፤ በወሎ ድርቅ ጊዜ፤ ደርግ ሰፈራ ሲያደርግ ወደ ጎጃም ቻግኒ ወረዳ ከሄደ በኋላ ትምህርቱን ተከታትሎ፤ በስነ ህይወት ተመርቆ፤ በኋላም በጎጃም ቡሬ ወረዳ መምህር ሆኖ ሲሰራ ከተማሪዎቹ መካከል አንዷን አግብቶ አሁን ሶስት ልጆች ወልደው አብረው ይኖራሉ። በአማራ ክልል ውስጥ በቅድሚያ ተፈራ ዋልዋን፣ ቀጥሎም አዲሱ ለገሰን በመተካት እስከ ትምህርት ሚንስትርነትና አሁን ደግሞ ምክትል ሚንስትር ደረጃ የደረሰ ሰው ነው። ዝርዝር ታሪኩ ላያስፈልግ ይችል ነበር።እግረ መንገዳችንን ሙስሊም ምክትል ጠቅላይ ሚንስትራችንን… ለማስተወቅ ያህል ግን ይሄ ይበቃል።

ከላይ እንዳልነው፤ ዋናውም ሆኑ ምክትሉ ድንገት ከተለዩን ደግሞ፤ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ በትረ ስልጣኑን ሊቀበሉ ይችላሉ። አባዱላ ገመዳ የኦሮሞ ብሄር ተወላጅ በትጥቅ ትግሉ ዘመን በኢህአዴግ ተማርከው፤ በዚያው ትግሉን የተቀላቀሉ፤ በኋላም እስከ ብርጋዴር ጄነራልነት ማዕረግ ስልጣን፤ የመከላከያ ሚንስትር፣ የኦሮሚያም ፕሬዘዳንት እስከመሆን ደረጃ ደርሰዋል። በተለይ በጅማ ከተማ በክርስቲያኖች ላይ ጭፍጨፋ እና አብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ ወቅት እጃቸው አለበት ወይም በክርስቲያኖች ላይ የተደረገውን ጭፍጨፋ ደግፈዋል የሚለው ክስ በመረጃ ተደግፎ በመቅረቡ ከኦሮሚያ ፕሬዘዳንትነት ስልጣናቸው እስከመወገድ ደረጃ መድረሳቸው ይነገራል። ከዚያ ውጪ የእስልምና እምነት ተከታይ እና በሙስሊሞች የረመዳን በዓላት ላይ ጭምር ተገኝተው በሶላት ስግደት የሚሳተፉ ናቸው።

በቀጣይ ከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኘው የመከላከያ ሚንስትር ናቸው። አቶ ሲራጅ ፈጀታ ይባላሉ። በትውልዳቸው የስልጢ ተወላጅ ናቸው። ከዚህ ቀደም በህዝብ ቆጠራ የበላይ ኃላፊ ከዚያም የፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር ሆነው የሰሩ ሲሆን፤ የስልጢ ማህበረሰብ ከሌላው የጉራጌ ህብረተሰብ እንዲገነጠል በተደረገበት ወቅት፤ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ብሎም “የስልጢ ህዝብ ሙስሊም በመሆኑ፤ በሃይማኖትም ጭምር ከጉራጌ ህብረተሰብ ሙሉ ለሙሉ የተለየ ነው።” የሚል መከራከሪያ በማቅረብ የሚታወቁ ናቸው። በፖለቲካው ረገድ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆነው ሬድዋን ሁሴን (ሙስሊም) ሙሉ ድጋፍ አላቸው።

ከመከላከያው ጎን ለጎን በስልጣን የማይተናነስ ኃይል ያለው የኤታ ማዦር ሹሙ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤታማዦር ሹም ደግሞ ሳሞራ የኑስ ነው። ሳሞራ የትግል ስሙ ሲሆን፤ ትክክለኛ ስሙ መሃመድ የኑስ ነው። ሳሞራ የኑስ እንደኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1947 ዓ.ም. አክሱም፣ ትግራይ ተወለደ። በአባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ እናቱ ኤትራዊ ናት። በልጅነቱ ወቅት አክሱም ቤተ ክርስቲያን እየገባ “አላህ አኩበር” በማለት ቄሶቹን ያናድድ እንደነበር አንዳንዴ እንደጀብዱ የሚያወራው ታሪኩ ነው። በሙስሊሞች ስብሰባዎች ላይ እየተገኘ አንዳንድ መመሪያ እና አቅጣጫዎችን ያስይዛል። አሁን ኢህአዴግ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸውን የሙስሊም አመራር አባላት የሚደግፍና የሚቀበል ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ “አክራሪ” ወይም “አሸባሪ” የሚል ስም የሰጧቸውን የሚነቅፍ ሰው ነው። በዚያም ተባለ በዚህ ኤታ ማዦር ሹማችን መሃመድ የኑስን አስተዋወቅን። በ ኤታማዦር ሹሙ በኩል የሚወርድ ትዕዛዝ ካለ ደግሞ ለመላው ኢህአዴግ አባላት ለማሰራጨት፤ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የስልጤው ተወላጅ አቶ ሬድዋን ሁሴን መሆናቸውን በድጋሚ ገልጸን ወደ ሌሎቹ እናምራ።

እንግዲህ መነሻችንን ያደረግነው ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት በድንገት ቢለዩ ሊሆን የሚችለውን ገጽታ በማሳየት ነው። እነዚህ ሰዎች በመንበረ ስልጣኑ ላይ ቢቀመጡ ደግሞ፤ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት እና የገንዘብ ምንጩን፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚንስትሩን፣ ንግድ እና ሰራተኛውን የሚያዘውን የስራ ሚንስትሩን ከያዙት በቂ ሊሆን ይችላል። ለ3ኛ ጊዜ ልንደግመው ነው። የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በሬድዋን ሁሴን ስር በመሆኑ ብዙም ጭንቀት ላይገባቸው ይችላል። የገንዘብ ሚንስትሩ ሱፍያን አህመድ ሲሆን፤ የሲቪል ሰርቪስ ሰጪ መስሪያ ቤቶችን የሚመራው ጁነዲን ሳዶ፣ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚንስትር አብዱልፈታህ አብዱላሂ በአዲሱ ለውጥ ቁልፍ ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ከዚያ ውጪ የበረከት ስምኦን (በነገርዎ ላይ አቶ በረከት ሃይማኖት የለውም) ምክትል ሽመልስ ከማል ወይም የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሌላኛው ሃላፊ ሙክታር ከድር ወይም የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዘዳንት አብዱልአዚዝ መሃመድ ወይም የባህል እና ቱሪዝም ወይም የሌሎች መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ገና ለገና “ሙስሊም ናቸው” በሚል… እዚህ ዝርዝር ውስጥ አላካተትናቸውም። በዚህ ትንታኔ ውስጥ ለማሳየት የፈለግነው አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ድንገት ቢለዩን ሊኖር የሚችለውን ገጽታ ነው። ይህ ትንታኔ ሌላም ፋይዳ አለው። አንድ ቀን ከእንቅልፍዎ ሲነቁ፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ሞቱ ቢባል፤ በዚህ አይነቱ የመንግስት አወቃቀር መሰረት የእስልምና አስተዳደር አገሪቱን ቢቆጣጠራት እንዳይገረሙ ለማድረግ ያህልም ይረዳል።

በመግቢያችን ላይ እንዳልነው፤ ከላይ ያቀረብነው ትንታኔ የሌላ እምነት ተከታዮች ‘ለምን በሃላፊነት ደረጃ ይቀመጣሉ?’ የሚል አንደምታ ለመፍጠር ወይም አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ከቢኔያቸውን እንዲቀይሩ ለመጠየቅ ሳይሆን፤ ያለውን እውነት እንዳለ በማሳየት፤ ለጠቅላላ እውቀት ያህል የአገርዎን የስልጣን ገጽታ እንዲመለከቱ ያህል የቀረበ ነው።

(ትንታኔውን ሌሎች የፌስ ቡክ ጓደኞችዎ እንዲያነቡት እና ሃሳባቸውን እንዲሰጡበት ከፈለጉ ከዚህ በታች ያለውን Like የሚለውን ሊንክ ይጫኑ)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 28, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.