አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር (ክንፉ አሰፋ)

በሳውዲ የተነሳው የወገን ሰቆቃ ገና አልበረደም። ስቃዩ የበለጠ ሲከፋ እንጂ ሲቀንስ አላየንም። ለውጭ ምንዛሪ ማግኛ ሲባል ልክ እንደ ባርያ ንግድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል የተላኩት ምስኪን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በገዥው ፓርቲ እንደታሰበው አልሆነም።  እንዲያውም ሌሎች መዘዞችን አስከትሎ መጥቷል።  ዲያስፖራው እንደገና ተነሳ።  ለቦንድ ግዢና ለግንቦት ሃያ በዓላት የሚሰባሰቡትም ጭምር ገዢው ፓርቲን ማውገዝ ጀመሩ። የስደተኛው ጎርፍም እንደሱናሚ ማእበል ያንን ጎራ ማጨናነቁ ግልጽ ነው።  ወቅት እየጠበቀ የሚነሳው የክረምቱ ነቀርሳ አሁን በነበረከት ስምዖን ላይ ጠና ያለ ይመስላል። ይህ ህመም ማስታገሻ ያስፈልገዋል።  ዘላቂ ሳይሆን ግዚያዊ ማስታገሻ። መቼም ለነቀርሳ ዘላቂ መፍትሄ የለውም። ለግዜው ግን እድሜ ማራዘሚያ … የድርድር ጥያቄ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ….

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 3, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

6 Responses to አዲሱ ነጠላ ዜማ፣ ድርድር (ክንፉ አሰፋ)

 1. Kebede

  December 3, 2013 at 3:19 PM

  ሰላም አቶ ክንፉ

  አንድ ጥያቄ አለኝ:: ምነው እንደራደር የተባለውን ድርጅት ወይም እንቅስቃሴ ስሙን መጥራት ተጠየፍክ? ወያኔን ጠቅሰህ ለድርድር የተጠየቀውን ድርጅት ስም መጥቀስ (በአሽሙርም ቢሆን በቀጥታ) እንዴት ተናነቀህ ልጄ? ግንቦት7ን ምንም ቢሆን ከወያኔ በላይ ትጠላዋለህ እንዴ? በጣን ይገርማል?

  ከጋዜጠኛነትም ሆነ ከአንድ አገር ወዳድ የማይጠበቅ ባህርይ ነው:: ከግንቦት 7 የሚመጣ ነገር ፖስት አታደርግም:: የግድ ማድረግ የለብህም:: መብትህ ነው:: ግን ድርድሩን ካነሳኽው ዘንድ አንደኛውን የተደራዳሪ ስም ለምን ሳንሱር እንደምታደርግ አይገባኝም:: ቀናህ እንዴ? ለምን እኔን ወያኔ አልጠየቀኝም ነው?

  ብታምንም ባታምንም ጠመንጃዋን ካላነሳህ ዞር ብሎ አያይህም:: ሺ ጊዜ ብትጽፍ ወያኔ ስሜትም አይሰጠው:: ወያኔን የምታንቦቀቡቀው ያንን ነገር ስታነሳ ነው:: ለዚህም ግንቦት7 ምስክር ነው:: የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ መሳርያዋ ናት የምታስከብር:: እያየነው እኮ ነው:: ይህን ቁልጭ ያለ ሃቅ በግል ቂም ተወጥሮ ለመካድ መዳከር ትንሽ ያሳዝናል:: ከንተ አልጠበኩም ነበር:: በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተዘዋዋሪ ወያኔን መደገፍ ነው የሚሆነው::ወያኔን የመደገፍ መብትህን ግን አልቃወምም:: ወያኔ መኖሩን አምኖ ና እንደራደር የተባለውን ድርጅት ስም አለመጥቀስ የጋዜጠኛ ሙያ አለኝ የምትለውን ሁሉ ጥያቄ ውስጥ ሊያስገባ የሚችል አጠያያቂ ተግባር ነው::

  በነገራችን ላይ ወያኔን አንቦቅቡቆ እንደራደር ብሎ ግንቦት7ን ሲጠይቅ (በሸፍጥም ቢሆን) አይተህ ለግንቦት7 ትንሽ እንኳ CREDIT ለመስጠት እንኳ አልቃጣህም:: እንዲያውም ግንቦት7ን በጠረባ እየመታህ ነው በግል ቂም ምክንያት:: የአንተ የግል ቂም ነው ወይስ የአገራችን ጉዳይ ነው ዋናው ጥያቄ? እስከመቼ ነው ግለሰቦች ለራሳቸው ኢጎና በቂም በቀል ሲሉ ብቻ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አንድነታችንን እየሸረሸሩ ኢትዮጵያን የሚያደሙት?

  ለማንኛውም ወያኔ ይህን የድርድር ጥያቄ ያቀረበው የሳውዲ አርቢያን አንግብጋቢ ጥያቄ ወደጎን እንዲተው የፈጠረው ማደናገሪያ ነው:: ስለሆነም ይህን ሸፍጥ የተሞላበት የወያኔ የድርድር ጥያቄ መናገርም መጻፍም አያስፈልግም:: አጅንዳው በአስቸኳይ ወደ ሳኡዲ አረቢያ መመለስ አለበት::

 2. tewederos

  December 3, 2013 at 5:10 PM

  kinfu asefa ,your concern is not different than most weyanes.what you want to write is a pure weyane propagand which is similar to your brother dawit kebede of awramba times.but one thing what you can not make business is on the pure ethiopians who are suffering back in saudi.ginbot 7 negotation with weyane has nothing to do with ethiopians suffering back there.but ginbot 7 has well articulated and put it right that there is no negtiation unless weyane free all poltical prisoners and and the nogatation must be free to all ethiopians.so i don’t think they need your weyane kind advice or comment,you better get a one way ticket and join your cousin dawit kebede,

 3. Kebede

  December 3, 2013 at 6:36 PM

  ብርሃኑ ለማ መነን እንዲሁም ሮቤሌ አንድ የማሳስባችሁ ነገር አለ:: ሁላችሁም አንድ ሰው ትመስሉኛላችሁ:: በተለያየ ስም አንድ ወያኔ የሆን ሰው የጻፈው ነው:: ወያኔም ካልሆነ የኛው ደደብ ነው የጻፈው:: የሞኝ ዘዴ ማለት ነው:: አንዳንድ ሰዎች በቂጣቸው እንጂ በጭንቅላታቸው የሚያስቡ አይመስሉም::በተለይ ወያኔዎች!

  ወያኔ ሲርበተበት አይቶ አንድ ላይ እንደመረባረብ ግንቦት 7ን የሚወርፍ ወያኔ ብቻ ነው:: ወያኔም ባይሆን ወያኔ ነው እንደ ክንፋ አስፋ ማለት ነው::

  የአእምሮ ድህነት ክሆነ እስክትበስሉ ድረስ ትራክ ንዱ:: ትንሽ ስትበስሉ ብቅ በሉና ያኔ የፖለቲካ ትችት መስጠት ትችላላችሁ:: ከናንተ ጋር የማጠፋው ጊዜ የለኝም:: ጊዜው የመስዋእትነት ነው:: የወሬ መደለቂያ አይደለም:: ወሬኞች!

 4. dereje

  December 3, 2013 at 7:34 PM

  መጻፍ መቻልና የሚጽፉትን ማወቅ ለየቅል መሆኑን ከአቶ ክንፉ አሰፋ ጽሁፍ የበለጠ አስረጂ የሚያስፈልግ አይመስለኝም!!! የሌላውን ክፉትና ጥላቻ ስንዘረዝር ቢያንስ ውስጣችን ከጥላቻ የጸዳ ቢሆን ማጣፊያ ያጠረው የሚመስለው የሃገራችን ጉዳይ መፍትሄው እንዲህ ባልተንዛዛ!!!!

 5. በለው!

  December 4, 2013 at 1:09 AM

  **ግንቦት ፯ ሲደመር ግንቦት ፳ ይሆናል ግንቦት ፳፯ ይታሰባል ህዳር ፳፫ ታጠነ በለው!ግንቦት፯ የሰጠውን ጋዜጣዊ ምላሽ አስመልክቶ…እኔም አግራሞት እነሆ!!
  >> ህወአት/ወያኔ/ኢህአዴግ አሸባሪ ሆነ ማለት ነው!? “ከአሸባሪው የግንቦት፯ ጋር የተገናኘ፣ማኒፌስቶውን ያነበበ፣ ያስነበ፣ አብሮ ሻይ ቡና እንኳን ያለ የአሸባሪው አዋጅ ይከለክላል። ” ሼም የለሽ ከማል ከተጨቆኑና ከተረሱ ብሔር የብሔረ ሰዎች የሕግ ምሁር። የቀድሞው ባለዕራዩ ተ/ሚኒስትር ከኤርትራ መነግስት ፐሬዘዳንት ጋር ለመነጋጋር ፶ ግዜ ሞክረው ነበር።እኔም አስመራ ድረስ ሄጄ እግሩ ላይ ወድቄ እለምናለሁ” አቶ ኅያለመለስ ዜናው ደስአለኝ። “የኢህአዴግ መንግስት ለድርድር ከ፸፩ ግዜ በላይ ልመና አቅርቧል” ህወአት አሰልጣኝ የቀጠናው አተራማሽ አቶ ኢሳአስ አፈወርቂ። “፸ግዜ ልመና ማቅረባችን ትዝ ይለኛል ፸፩ግዜ መሆኑን እርገጠኛ አደለሁም አልቆተርኩም እነሱ ቆጥረውት ይሆናል።አራት ነጥብ። የጠተቀለሉት /ሚኒስትር አቶ መለስ ::
  *ለግንቦት፯ የቀረበው የ፫ተኛ ግዜ “የእንደራደር “ጥያቄ ምን እንደሆነ ?ለምን እንደሆነ? በማን እንደሆነ ?እንዴት እንደሆነ? ባይታወቅም አቶ ኅይለማርያም ደስአለኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆኑ በራዕዩ እየተመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ህወአት/ወያኔ የውጭ ጉዳይና የብሔር ብሔረሰብ ተወካይ ሆነው እንደፎከሩ፣ እንደተወራጩ፣ ፈገግታቸው ቀንሶ፣ ፍንጭታቸው መግጠም፣ መጀመሩ ይገርማል። በእርግጥም” ከፊትም ከኋላም ሆናችሁ ምሩኝ” አሉ። በአንድ ወንበር በ፫ ተሽከርካሪ ብሔር ብሔረሰብ ክላስተር በ፪ ተለዋዋጭ ምክትል የብሔር ጎማ በ፩ መደገፊያ ፕሬዘዳንት ተደርጎላቸው ይውተረተራሉ። አቶ ኢሳያስ ኅይለማርያም አንተ ካልመጣህ እኔ መጣሁብህ አሉን።
  *ግንቦት አልፎ በወርሃ ኅዳር ሲታጠን ይህ መታሰቡ መልካም ነው።ኢህአዴግ ምን ሰጠቶ ምነ ሊቀበል ይሆን? ግን የግንቦት ፯ አሸባሪነት በፓርላማ ተሰረዘ? ኦብነግና ኦነግ የፓርላማ አባል ሊሆኑ ነው? ወይንስ መሳሪያ የሌለውን የተኩስ አቁም ስምምነት ነው?ግን ኢህአዴግ ውስጥ ያሉት እነማን ሆኑና ባትሉኝ!?ኤርትራውያን ትውልደ ኤርትራውያንና የደርግ አማካሪዎች አደሉምን!?ኤርትራ ክእናት ሀገሯ ልትቀላቀል ይሆን?
  ————__________________——————
  **ይህ የጠ/ሚር አማካሪዎች ሽረባ ፉገራ ይመስላል። መቼም ጠ/ሚኒስትሩ እንደዚያ ደንፍተው አሁን በእሳቸው አመራር ላይ ውሃ የሚደፉ ከሆነ ትዝብት ነው ። ድሮስ ሰውዬው ከምንም አይቆጠሩም ማታ ማታ ሲገረፉ ነው ቀን የሚለፈልፉት ማለት ነው። **ይች የተዳነቀችና የተሰበረች ዜና ሕዝቡ ምን አለ? ደጋፊ ነው ተደጋፊ የሚንጫጫው? መሀል ሰፋሪውስ ምን አደረገ?ተለሳላሹ? ብሔርተኛው? ጽንፈኛው? ሙሰኛው? ነጋዴው? ኢንቨስተሩ? ዴያስፖራው? አርቲስቱ? ኪራይ ሰብሳቢው? ጥቅመኛው? እያሉ ሰሞኑን ሥራና አፍ ይከፈታል።ስለኢህአዴግ ቀድሞ የሚጮኸውና የሚታመመው ማን ይሆን? ?

  ***“ድርድር”ምንድነው? ሀብትሽ በሀብቴ ጋብቻ ይሆን? አትንኩኝ አልነካችሁም? ካልነካችሁኝ የተፈረደባችሁ ከሞት ቅጣት ወደ እድሜ ልክ ይቀየራል? አሸባሪነታችሁ ተሰርዞ ተባባሪ ፓርቲ (በአንድ ፖለቲካ ጥላ ሥር ትሰባሰባላችሁ) ትሆናላችሁ ማለት ይሆን? የሥልጣን መካፈል ይሆን? ኢህአዴግ የ፭ዓመቱ ህዝብ የሰጠው ኮንትራት እንደማይታደስ ገባው? የኮንትራት ተፎካካሪዎችን አስወጥተን ከምንወጣ አስገብተን እናስወጣቸው ብለው ይሆን? አሸባሪን ለማጥፋት አሸባሪ መሆን አማራቸው? ግንቦት፳ ሲደመር ግንቦት ፯= ግንቦት ፳፯ መድህኒያለም ለየት ያለ ማሊያ አስለብሶ ደግሞ ለ፳ ዓመት ሊያስለቅሰው ይሆን?
  ****የኢህአዴግ የመጨረሻዋ የሥልጣን ሹም ሽር (ክላስተር ቦምብ) አልተመቸችኝም። የስኳር ሚኒስትር የሃይማኖት መሪዎች የበላይ አካል። የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ የውጭ ጉዳይ ሰላምና መረጋጋት ተጠሪ፣ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግርኳስና የፖለቲካ አቅጣጫ የአካባቢው አየር ሁኔታ ተቆጣጣሪ ጨምሮ ይሰራል። አቤት የኅብረት አመራር (አመራር በደቦ)
  (ሀ)ኢህአዴግ አለውን እስረኛ እስኪያረጋግጥ አህያ ቀንድ ታወጣለች!
  -ለመሆኑ እስረኛውንና የእስር ቤቱን ቁጥር በውል ያውቀዋል?
  ( ለ) በተፎካካሪ ፓርቲ አባላት ወከባና እንግልት ባስቸኳይ ማቆም፣ ሰብዓዊና የዜግነት መብታቸውን ማክበር፡
  -ድንቄም! ለመሆኑ ትርጉሙን ያውቁታል? ዜግነት! መብት!ሰብዓዊነት!ሉዓላዊነት!ሰንደቅ!ሀገር! ጉድ እኮ ነው ድርድሩ ቀርቶ መማማሩ በተቻለ በለው!
  (ሐ) ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ምንም አይነት ክሶችን ማቋረጥ አለበት።
  -”በሀገር ውስጥ በፖለቲካ የታሰረ አንድም ሰው የለም!መታሰርም የለበትም!አለመታሰር ሕገመንግስታዊ መብቱ ነው። እሺ እስር ቤታችሁን አስጎብኙን? “የዓመቱ አቦ ስለሆነ የእስር ቤቱ ተረኛ ኀላፊ ጸበል ሊቀምሱ ሄደዋል። ከነገ ጀምሮም የዓመት ፍቃድ ሞልተዋል።” ይቺ ነች ኢህአዴግ !እንዲህ ከሚቀሳፍቱ ጋር ነው ‘ድርድሩ’!?ለዚያውም አንዱ የተናገረውን ሌላው ያስተባብላል።
  (መ) አፋኝ ህጎችን በአስቸኳይ ማንሳት አለበት።!
  -ህወአት ማኒፌስቶ (ሕገመንግስት) የሚከበረው ግን የማይተገበረው ለእያንዳንዱ ፻፮ አንቀጽ ፻፮ ሕጎች/መመሪያ/ ደንቦች /ወጥተውለታል። ይህ ማለት ለእያንዳንዱ ንዑስ አንቀፅ ማጥፊያ ህግ አለው።
  (ሠ)የድርድሩ ሂደት በምስልና በድምጽ ተቀርጾ በገለልተኛ ወገኖች እጅ ብቻ የሚቀመጥ፣
  – እንኳን ስለሀገር አብሮ ለመሥራት”ድርድር” ቀርቶ የግለሰቡን ራእይ ለማስቀጠል ፮ሚሊየን ኢህአዴግ አባላት ንፍጥና ለሀጫቸውን ባዶ ሳጥን ላይ በሁሉም ክልልና በቤተመንግስት ሜዳ ላይ ሲያዝረከርኩ ታይተዋል። ይህ ሀገራዊ ራእይ ከሆነ የሚያስማማውም የሚያለያየውም ሀሳቦች ለህዝብ ግልጽ መሆን አለባቸው።ሽፍንፍን በአክፋይ ዳቦ ዘመን ቀረ በለው!ዓለም አንድ መንደር ሆነች ተባለ አሉ ኢቲቪ ቆርጦ በሚቀጥለው “የግንቦት ፳፯ ሃረካት ፊልም” እዳይሰራበት ዘመኑ የሥራ ፈጠራ አደለምን አሁን ከዚህ ተሰባሪ ዜና በኋላስ ስንቶች ቆመው አድረዋል!? አክራሪ ደጋፊዎችና አክራሪ ተቃዋሚዎችስ ካራ አይመዙምን?
  ለሁሉም ሠላም በቸር ይግጠመን ከሀገረ ካናዳ<<>>>>>>

 6. tokchaw

  December 4, 2013 at 8:15 AM

  Kinfu I respecte you but the article what you wrote does not imply that you stand on the side of ltberation the ethiopian people from Weyane.What did you do on your part?
  please it is not jock time people in ethiopia are crying suffering. They need help.G7 is trying his owen part.we are not babies we know what G7 doing on the groung to topple the weyane junta.we did 40 years haterate poletics.I beg you in the suck of ihe ethiopian people to stop hetrate politics.I remember the interview you gave on amestardem esat stadio.Esat did not stop doing its work. It is doing in a greater better way.let G7 do his work and do your work in better way.what we donot accept is the opposing of another opposing force. If you are on the side oppostion force please do not hurry for unnecassary explanation. read and listen and write