አውስትራሊያ ለሀገሯ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

(ኢትዮ እማማ)አዲስ አበባ የሚገኙት የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኪቨን ሩድ ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ዒላማ ልትሆን እንደምትችል አስጠነቀቁ።

የሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ ድረ ገፅ ፤ የዲፕሎማቲክ ቃል አቀባይ የሆነው ፤ አደም ጋርቲል በድረ ገፁ ላይ እንደዘገበው ከሆነ፤ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱን ተንተርሶ በጉባሄው ላይ ለመካፈል ወደ ስፍራው ከማምራታቸው በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኪቨን ሩድ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደጠቆሙት፤ ለንግድና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር የኢትዮጵያ ዋና መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ የሚያመሩ የአውስትራሊያ ተወላጆች የሽብር ጥቃት ሊፈፀምባቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው መግለጻቸውን ድረ ገፁ ዘግቧል።

ሚኒስትር ኪቨን ሩድ

ትክክለኛው ቦታ በትክክል መግለፅ ባይቻልም፤ በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔን መካሄድ ተንተርሶ ጥቃቱ ሊፈፀም እንደሚችል ገልፀዋል።አውስትራሊያ የሽብር ጥቃቱ በአዲስ አበባና በሌላ ቦታዎች እንደሚፈፀም ዕቅድና መረጃ የደረሳት መሆኑም ተገልጿል።

የአውስትራሊያ ዜጎች የግድ መጓዝ ካለባቸውም እራሳቸውን እንዴት ማዳን እንዳለባቸው ልምምድ ማድረግ እንደሚኖርባቸው የውጭ ጉዳይ ክፍሉ አስምሮበታል።

ሚስተር ኪቨን ሩድ ባለፈው ሰኞ በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይና የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ በማምራት ፤በዛሬው እለት የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ ከተለያዩ የአፍሪካ ባለስልጣኖች ጋር ተነጋግረዋል።

ሚስተር ኪቨን ሩድ በፕሮግራማቸው መሠረትም አዲሱን የአውስትራሊያ ኢምባሲ እንደሚከፍቱም ድረ ገፁ ገልጿል።ከዛም ወደ ስዊዘርላንድ፣ቱርክ፣ግሪክና ወደ ሌሽቴኒሽታን ለጉብኝት ይሄዳሉ።

ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ከኒውዮርክ ፍንዳታ አስቀድሞ የአልኢትሃድ የሽብር ጥቃት ዒላማ የነበረች ሲሆን፤በተለይም ከኒውዮርክ በፊት አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና ሐረር እንዲሁም በዶ/ር አብዱል መጂድ ሁሴን እና በፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ ከዛም በግዮን፣ በዋቢ ሸበሌ፣ በትግራይ ሆቴል እና በምድር ባቡር ላይ የአልኢትሃድ አሸባሪዎች ጥቃት ዒላማ እንደነበረች አይዘነጋም፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 26, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.