አንዷለም አራጌ እና የቃሊቲው ህይወት

(EMF) – አንዷለም አራጌ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባል የነበረ ወጣት ነው። በኋላ ላይ የኢህ አዴግ ሰዎች ባቀናበሩት ድራማ አሸባሪ ተብሎ ለእስር ተዳረገ። ቃሊቲ በእስር ላይ ሆኖ ብቻውን በጨለማ ቤት ውስጥ ከመታሰር ጀምሮ ብዙ እንግልት እና መከራን እየተቀበለ ይገኛል። ይህ ሁሉ የሆነው አንዷለም በተቃዋሚው ጎራ በመቆሙ ብቻ ሳይሆን፤ ጎበዝ መሪ በመሆኑም ጭምር ነው። አሁን በ እስር ላይ ሆኖም እንኳን፤ ስሜቱን ለመጉዳት ሲባል እሱን ለመጠየቅ የሚሄዱ ጠያቂዎች ይዋከባሉ፤ እንዲጠይቁትም አይፈቀድላቸውም።

ከትላንት በስትያ አንዷለምን ለመጠየቅ ወደ እስር ቤት ያመሩት፤ ብቸኛው የፓርላማ ውስጥ ተቃዋሚ ክቡር አቶ ግርማ ሰይፉ ትዝብታቸውን ገልጸዋል። የአቶ ግርማ ትዝብት “አንዱዓለምን ለመጠየቅ ቃሊቲ ጎራ ብዬ ነበር፡፡” በማለት ይጀምሩና በአንዷለም ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት በዝርዝር ገልጸውታል። እንዲህ በማለት ይቀጥላሉ አቶ ግርማ….

አንዱዓለም እንደተለመደው በጠንካራ ሞራልና ለሰው ልጅ ክብር በሚሰጠው መንፈሱ ላይ ምንም ለውጥ አይታይም፡፡ የሚበድሉትን ቢሆን ለምን? ብሎ ይጠይቃል እንጂ የበቀለኝነት ሰሜት የለበትም፡፡ ነገር ግን በፍፁም ተሰፋ እያሰቆረጠው ምን አልባት ወደ ርሃብ አድማ ሊገፋኝ ይችላል ብሎ የሰጋው ከብዙ ሺ ከሚቆጠሩ እሰረኞች በተለየ ሁኔታ የሚሰተናገድበት አያያዝ ምቾት አልሰጠውም፡፡ መብቱን እያስደፈረ እንደሆነ ይሰማዋል፡፡

እሱን ለመጠየቅ ከባለቤቱ እና ከእኔ በስተቀር ይህን ሁሉ ኪሎ ሜትር አቋርጠው የመጡ ሰዎችን እየመለሱ ችግር እየፈጠሩበት እንደሆነ ነግሮኛል፡፡ ማንም ጠያቂ እርሱ እንዲጠይቅ አይፈቀድለትም፡፡ ይህ ደግሞ ፌዝ የሚሆነው ለእርሱ ደህንነት ብለን ነው የሚሉት መልስ ነው፡፡ በተለይ ትላንት ምሽት ድንገት በተደረገ ብረበራ ከማረሚያ ቤቱ ላይብረሪ ተውሶ ሲያነባቸው ከነበሩተ መፅኃፎች ላይ የያዛቸውን ማስታወሻዎች በሙሉ ወስደውበታል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ደንብ ላይ ይህ ክልከላ ስለመኖሩ ጠይቄው የማረሚያ ቤቱን ደንብና መመሪያ እንዲሰጡኝ ከጠየቅሁ ስድሰት ወር ያለፈ ቢሆንም እስከ አሁን እንዳልሰጡት ነግሮኛል፡፡

ማረሚያ ቤቱ ከህገ መንግሰት በተቃራኒ የሆነ መመሪያ የማውጣት መብትም የለውም፡፡ በነገራችን ላይ የአንዱዓለም ጠያቂዎች እንዳይጎበኙት የተጣለበትን ክልከላ አምሳደር ጥሩነህ ዜናም እንደሚያውቁት ነገር ግን ይህ መመሪያ ስለሆነ እንደሆነ ገልፀውልኝ፣ መመሪያው ከህገመንግሰት ጋር የሚጋጭ ነገር ካለው እንደሚያዩት መደበኛ ባልሆነ ውይይት ገልፀውልኝ ነበር፡፡ አንድ እስረኛ በተለየ ሁኔታ በዘመድ አዝማድ ጓደኛ እንዳይጠየቅ ገደብ ለምን እንደሚደረግበት ሊገባኝ ባይችልም፡፡ ማረሚያ ቤቱ ውስጥ ከመደበኛው በተለይ የሚደረጉ ተግባራትን ተዉ የሚል ያለ አይመስልም፡፡

አንዱዓለም ቃሊቲ ከገባ ጀምሮ በልዩ ቅጣት ክፍል የሚገኝ ሲሆን በዚህ ክፍልም ልዩ ጥበቃ ይደረግበታል፡፡ አንዱዓለም የሚላኩለት መፅሃፎች በጊዜው እንደማይገቡለትና ከተላከለት ስምንት መፅሃፍ ውስጥ 2 አይገባም ከተባለ በኋላ ወደ ቤተሰቦቹም አለመመለሱንም ገልጾልኛል፡፡ ለክፉም ለደጉ አንዱዓለም ለመጉዳት የሚንቀሳቀሱ የመንግሰት ኃላፊዎችም ሆኖ ልወደድ ባይ የማረሚያ ቤት ሹሞች ከዚህ ተግባራቸው ቢቆጠቡ ጥቅሙ የጋራ ነው፡፡ አንዱዓለም ሰርቆ ወይም ሀገር ከድቶ አይደለም በእስር ላይ የሚገኘው፡፡ ለሀገሩ ነፃነት የድርሻዬን እውጣለሁ ብሎ በሰላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀስ ይህ ዜጋ ለወንበራችን ጠር ነው ብለው በፈሩ እና በሀሰት በወነጀሉት አካላት ምክንያት ነው፡፡ ሌቦችን ወንጀለኞች እንደፈለጉ በሚሆኑበት እስር ቤት ጀግኖችን ማሰቃየት ማንገላታ አሁንም ፍርሃታቸው እንዳለቀቃቸው ከማሳየት ውጭ አንዱዓለምን መንፈስ እንደማይጎዳው እርግጠኛ ነኝ፡፡ የአሳሪዎቹን በቀለኝነት ግን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 29, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to አንዷለም አራጌ እና የቃሊቲው ህይወት

 1. andnet berhane

  April 29, 2014 at 1:09 PM

  አስፈራርተውና አላማውን ለማሳት አንገቱን ለማስደፋት የሚያደርጉት ያልተሳከ ጥረት ጀግና ለሕዝብና ለሃገር የቆመ ከውስጥ ጠላት ቀርቶ የባእድ ጠላት ሊያደርገው ያልቻለ በመሆኑ ያለው ሕገ ወጥ አገዛዝና የስልጣን ጥማተኞችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው በፍርሃት ድባብ ብቅ የሚሉትን ጀግኖች መሰወርና ለጋሸ ሃገራት ለሚጥሉላቸው እርጥባን እንድይቀርባቸው ለመግደል ባይችሉም በስር ቤትውስጥ ሕሊና ቢሶች የነገን የማያስቡ ሆድ አደሮች የሚያደርጉት ሕገወጥ ተግባር ነገ ከዚህ አረመኔ አገዛዝ መገርሰስ መድረሻቸው የት እንድሆነ ማወቅ የተሳናቸውና ራሳቸውውን የዘነጉ በደመነፍስ የሚኖሩ ድካሞች በመሆናቸው ለጀግንኖቻችን ጥንካሬ ጽናትና ጤንነት እድሜ በመመኘት በሩቅ ሆነን ምን እናድረግ ሳይሆን የሁላችንን ነጻነትና የመኞር መብታችንን ለማረጋገጥ ኑራቸውን የቤተሰብ ኃላፊነታቸውን እውቀትና ራሳቸውን ክቡር ሕይወታቸውን ለሰጡን እንዲህ ላሉ ጀግኖች ተጋቢውን ደርሻችንን ባለማበርከታችን ከሰር ተጥለው የሚሰቃዩት ዝቡ በነቂስ ወጥቶ እነኝህን ብርቅዮ የኢትዮጵያ ልጆች አንዱዓለም አራጌኤን እስከደር ነጋ ውብሸት ታዮ ርዮት አለሙ በቀለ ገርባ እሱታዝ አቡበከር ሌሎቹንም ለማስፈታት ሕዝባዊ ሰልፍ አለመውጣታችን የወያነእን ድንፋታና ንቀት ትምክህት ማኮላሸት ባለመቻላችን ጀግኖቻችንን ለዲህ ያላ አረመናዊ የጨካኝኦች እንግልት ዳርገናቸው እንገኛለን ስለዚህም እውነት ስቃያቸውና እንግልታቸውን ተካፋዮች ከሆን ተነስተን በሰልፍ ለማስፈታት ጥረት እናደግ
  አንገቱን አይደፋ ወርዶ ከዛብጥያ
  ቃሉን የማይለውጥ የቆምው ለኢትዮጵያ
  ጠያቂው ብዙነው ሕዝብ ያመነበት
  በግንባር የቆመ ፍትሕን ለመስጠት
  ጠንካራ ተሟጋች ፍርሃት የሌለበት
  ድንግጦ የጠፋው የግር ቆራጭ ቁንጮ
  በሶስት የሚመራ በፍርሃት ተጨንቆ
  ብርሃኑ መጣልህ ልቦናህን አይቶ
  ተገርሥሦ ሊወድቅ የፋሽሽት ቀረርቶ
  ትግልህ ተበራክቶ ወጣቱ አድሶ
  አንድነት ሰማያዊ ሕዝቦችን ቀስቅሶ
  ጨነቀው ወያኔ መውደቂያውም ደርሶ