አንድነት ፓርቲ የጠየቀው የ”እሪታ ቀን” እውቅና ተነፈገ (ደብዳቤውን ይዘናል)

EMF – ባለፈው ሳምንት መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ የነበረው፤ የ“እሪታ ቀን” ለመጪው ሚያዝያ 5 ቀን፣ 2006 መተላለፉ ይታወሳል። የሰልፉ ዋና አላማ በአዲስ አበባ እየተከሰተ ያለውን የመብራት መቆራረጥ፣ የውሃ እጦት እና የስልክ ኔትዎርክ አለመስራትን በመቃወም የሚደረግ ነበር። እናም ባለፈው ሳምንት ሊያደርግ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ሰርዞ፤ ፓርቲው ሰልፉን በአንድ ሳምንት ወደፊት ያራዘመው፤ መንግስት ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የሚያካሂደው ዝግጅት አለው… በመባሉ ነው።

አሁን ደግሞ ሚያዝያ 5 ቀን ደግሞ “ታላቁ ሩጫ” ስለሚደረግ የአዲስ አበባ መስተዳድር “በቂ የፖሊስ ሃይል የለኝም” በማለቱ፤ አንድነት ፓርቲ ሰልፉን ለቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን ለማድረግ ወስኖ ነበር። በጉዳዩም ላይ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ጋር እየተነጋገሩ ነበር። በዚህ መሃል ነው እንግዲህ ሌላ ደብዳቤ ለአንድነት ፓርቲ የደረሰው።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ የጻፈው ደብዳቤ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ለአንድነት ፓርቲ የጻፈው ደብዳቤ

የደብዳቤው ይዘት “ያቀረባችሁት የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ እውቅና አግኝቷል። ነገር ግን የተመረጠው መንገድ ወደ ሲ.ኤም.ሲ፣ ኮተቤ እና ጉርድ ሾላ የሚሄዱ መንገደኞች ያለበት ስለሆነ… የቀረበው አማራጭ እና ቀን እውቅና አላገኘም” የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ነው ለፓርቲው የደረሰው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአዲስ አበባ የኔትዎርክ ችግር እየተቀረፈ መሆኑን በሰፊው ዜና በመስራት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞረ ያለ ይመስላል። በአዲስ አበባ መስተዳደር አማካኝነት ሰላማዊ ሰልፉ በተራዘመ ቁጥር ደግሞ “ውሃ እና መብራትም በሚገባ አለ።” የሚሉ ዜናዎች ሳይሰሩ አይቀሩም።  ለማንኛውም የአንድነት ፓርቲ በዚህ ጉዳይ የሚለው ካለ ተከታትለን እናቀርብላችኋለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 9, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.