አንድነት ፓርቲ በአራት ከተሞች ቅስቀሳ እያደረገ ነው (መቐለ ያሉት ታሰሩ)

EMF – የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት በሚል መሪ መፍክር ስር እየተንቀሳቀሰ እና ህዝቡን እየቀሰቀሰ የሚገኘው አንድነት ፓርቲ፤ ከዚህ ቀደም በደሴ እና በጎንደር ከተሞች በአስቸጋሪ ሁኔታም ቢሆን፤ ህዝቡን አስተባብሮ ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ደግሞ በመጪው እሁድ ህዝባዊ ስብሰባ ከማድረጉ በፊት… በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በጅንካ እና በወላይታ ሶዶ ከተሞች ህዝባዊ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል። (ቀሪውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

በባህር ዳር ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በማገት፤ የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ ጭምር ነጥቀዋል።

በባህር ዳር ለቅስቀሳ የወጣውን መኪና በማገት፤ የሹፌሩን መንጃ ፈቃድ ጭምር ነጥቀዋል።

ተጨማሪ ማስታወሻ፡ በባህርዳር ከተማ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚደረገው የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ የጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አባላቱ በከተማዋ በተሸከርካሪ መኪና እና ድምፅ ማጉያ በመታገዝ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ ከድምፅ ቅስቀሳው ጎን ለጎን በከተማዋ ፖስተሮች የመለጠፍና በራሪ ወረቀቶችንም የመበተን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እሁድ ሐምሌ 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ መነሻውን የፓርቲው ጽህፈት ቤት ከሚገኝበት ግሽ አባይ ቀበሌ ፊትለፊት በማድረግ በጊዮርጊስ ቤተክርስቲን ፣ ጊዮን ሆቴል፣ ሙሉዓለም አዳራሽ በማድረግ መዳረሻው መስቀል አደባባይ እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on August 2, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.