አንዳንድ ወሬዎች ከትግራይ (አብርሃ ደስታ -ከመቐለ እንደዘገበው)

ስኳር የገዙ ሁለት ካድሬዎች ታስረው ዋሉ!

በሑመራ አደባይ በሚባል ቦታ ነው። ባከባቢው ከፍተኛ የሆነ የዘይትና የስኳር እጥረት አለ። የንግድ ፍቃድ ያላቸው ነጋዴዎች የካድሬዎች ፖለቲካዊ ተልእኮ ካልፈፀሙ ስኳርና ዘይት አያገኙም። በስኳር እጥረት ምክንያት ብዙ ሻይ ቤቶች ችግር ላይ ወድቀዋል።

ሁለት የህወሓት ካድሬዎች (ሴቶች ናቸው) ከአደባይ ወደ ሑመራ ከተማ ተጉዘው የተወሰነ ስኳር አገኙና በዉድ ዋጋ ገዘተው ወደ ሰፈራቸው ሲመለሱ ‘ስኳር ገዝቷችኋል’ ተብለው ታስረው ዋሉ። የያዙት ስኳርም ተነጠቁ። ካድሬዎቹ አሁን አኩርፈው ይገኛሉ።
በመቀሌም ከፈተኛ የስኳር እጥረት መኖሩ ለመገንዘብ ችያለሁ።

———————————

ህዝብ እየጠየቀ ነው!
————————-

ዜጎች ይጠይቃሉ፤ መንግስት ያስራል። የመቀሌ ከተማ (የሰራዋት) ኗሪዎች የሰፈሩበት መሬት ለግሪን ኤርያ (Green Area) ይከለላል ተብሎው ከቀያቸው ተፈናቀሉ። አሁን ግን ለግሪን ኤርያ ይከለላል የተባለው ቦታ ካድሬዎች ለሃብታሞች እየሸጡት መሆናቸውን ተፈናቃዮቹ ስለሰሙ ተቃውሟቸው እያሰሙ ነው። ከመንግስት አካላት ጋር ባለመስማማታቸው ባከባቢው ዉጥረት ነግሷል። ህዝብን መሸወድ ካልቀረ እንዲህ በጠራራ ፀሐይ።

በተያያዘ ዜና የዓይናለም ከተማ ኗሪዎች በመሬት ጉዳይ ከክልል መንግስት አለመግባባት ተፈጥሯል። የዓይናለም ህዝብ የመሬት ባለቤትነትና የከተማነት ጉዳይ በተመለከተ የክልል መንግስት መፍትሔ እንዲሰጠው ጥያቄ ቢያቀርብም የመንግስት አካላት ግን ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ‘እኛ የምንላቹ ብቻ ፈፅሙ! ካልሆነ ግን መፍትሔ የሚሰጣቹ አካል ካለ እናያለን’ የሚል ማስፈራርያ ተሰጥቷቸዋል። የህዝቡ የተወካዮች ትናንት ወደ ፌደራል መንግስት (አዲስ አበባ) መሄዳቸው ተሰምቷል።

ዜጎች የፈለጉትን ጥያቄ የመጠየቅ ሙሉ መብት አላቸው፤ መንግስት ደግሞ ለተጠየቀው ጥያቄ ተገቢ መልስ የመስጠት ግዴታ አለበት። መንግስት ዜጎችን የማስፈራራት መብት የለውም።

————————–
ትንሽ ስለ Mekelle Institute of Technology (MIT)
————————-

የመቀሌ የቴክኖሎጂ ኢንስቲቱት (Mekelle Institute of Technology) ሲመሰረት ጎበዝ ተማሪዎችን በልዩ ስልጠና ለማብቃት ነበር። ድብቅ ዓላማውም ጎበዝ የትግራይ ልጆችን በቁሳዊ ነገር በመግዛት የህወሓት አገልጋዮች የሚሆኑበት መንገድ ለማመቻቸት ነበር፤ ተገዝተው ለስርዓቱ አገልጋዮች እንዲሆኑ ለማድረግ።

እንደዉጤቱም የMIT ወጪ በትግራይ ልማት ማህበር ይሸፈን ነበር። ቀጥሎም በትእምት ስፖንሰርሺፕ ነበር የሚማሩ። አብዛኞቹ ተማሪዎች በጥሩ ዉጤት (ብቃት) ሲመረቁ ነበር።

በቅርቡ ግን አንድ ችግር ተፈጠረ። ተቋሙ ብቁ ተማሪዎች ማፍራት ቢችልም ህወሓቶች የፈለጉት ዓላማ ግን ሊሳካ አልቻለም። ህወሓቶች የMIT ተማሪዎች ታማኝ የህወሓት አገልጋዮች እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። ተማሪዎቹ ግን የራሳቸው ነፃ ሐሳብ ማራመድ ጀመሩ። ምክንያቱም በቀላሉ በሆዳቸው ሊሸመገሉ አልቻሉም፤ ጎበዞች ናቸዋ። ጎበዝ ሰው ደግሞ ለህሊናው እንጂ ለሆዱ አይኖርም።

የተማሪዎቹ ገለልተኛ እንቅስቃሴ በህወሓቶች አልተወደደም። ጉዳዩ በህወሓት መሪዎች ታየ። ተማሪዎቹ የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች ሁነው ስለ ማገልገላቸው ወይ አለማገልገላቸው ጥናት እንዲደረግ ተወሰነ። ጥናቱ ተጠናቀቀ። ታማኝ ካድሬዎች አለመሆናቸው (የፈለጉትን ሐሳብ በነፃነት መናገር መጀመራቸው ተረጋገጠ)። ህወሓቶች ለMIT ተማሪዎች ስፖንሰር ማድረጋቸው እንደ ከባድ ኪሳራ ተመለከቱት። ‘እኛን ለማያገለግሉ ሰዎች ገንዘባችን በከንቱ ማፍሰስ የለብንም’ አሉ፤ ተስማሙ።

ህወሓቶች MITን ከትእምት ድጋፍ እንዳያገኝ ወሰኑ። ‘ታድያ ምን ይሁን?’ ለሚለው ጥያቄ ደግሞ የMIT ወጪ ከትእምት (የህወሓት ሃብት) ሳይሆን ከፌደራል መንግስት መሆን እንዳለበት ተስማሙ። የተቋሙ ወጪ ከፌደራል መንግስት ከሆነ ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ መጠቃለል እንዳለበት ታመነበትና ተወሰነ። በዚሁ መሰረት MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ገባ።

አሁን MIT አንድ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ አካል ነው። አሁንም ግን የMIT ተማሪዎችን ቅር ያሰኘ ጉዳይ አለ። MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ ቢገባም የግሬዲንግ ስርዓቱ (Grading System) ግን የተለየ ነው። እናም ጥያቄው ‘MIT ወደ መቀሌ ዩኒቨርስቲ መግባቱ ካልቀረ ለምን ሁሉም ነገር ተመሳሳይ አይሆንም?’ የሚል ነው።

ለሆዳችን ወይስ ለህሊናችን ተገዢ እንሁን???

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 8, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

6 Responses to አንዳንድ ወሬዎች ከትግራይ (አብርሃ ደስታ -ከመቐለ እንደዘገበው)

 1. Angereb talele

  December 8, 2013 at 3:50 PM

  Abraham,
  The more you’re sharing information about what is going on in Tigray the more you’re spilling the beans about miss ‘Oh my God I’m so spoiled I want an independent MIT institution’ called Tigray. please note that the rest of Ethiopian regions do not have a luxury of having any useful educational institution much less an institution like MIT that has been built and maintained on the cost of Ethiopian’s blood.
  Your articles about Tigray’s current convoluted temperature is sickening. So stop insulting us will ya?

 2. Tesfa

  December 8, 2013 at 8:56 PM

  Hey Angereb,
  What exactly do you want Mr. Abraham to share with us. He writes what he sees and hears. It is true the State of Tigray may have and still benefit from the loots of TPLF. That is quickly fading as his article indicates.
  To have MIT for only Tigreans is a crime. Then again, the objective was to create a mind of like thinkers. It did not work. Time has changed. Too late for TPLF to clone the Tigreans to make them their own tools.

 3. Keali

  December 9, 2013 at 5:34 AM

  ኣቶ ኣብራሃም ኩሉ ትፅሕፎ ብዕምቆት የንብቦ ሐቂ’ዩ
  ቅፅለሉ ብዙሕ ሰዓቢን ተኸታሊን ኣለካ ።
  በትሪ ሐቂስያ ትቐጥን እምበር ኣይትስበርን ዝብል በሊሕ ስነ ባህልና ህልዊ ኩነታት ትግራይ ባግባቡ ይገልፆ ።
  ኣነ ንመብዛሕቶኦ ናይ MIT ነባራት ተምሃሮ ስለ ዝፈልጦም ብምንም ተኣምር
  ናይ ሕ.ወ.ሐ.ት ተጎተቲ ክኾኑ ከምዘይኽእሉ ያምን።
  ካብ ብሱል ጥረ ከምዝበሃለ ሐደሀደ ድኹማት ኣይህልዉን ማለት ግን ኣይኮነን
  Angereb talele ዝሃብካዮ ሪኢቶ ጌጋ እዩ ኣቶ ኣብራሃም ካብቶም ቆራፃት ደቂ ህዝቢ ሓደ እዩ ኩሉ ዘልዕሎ ዣዕባታት ሐቂን እዋናዊን እዩ ።

 4. Ethiopia

  December 9, 2013 at 6:45 AM

  @Abrham

  What do you want from this guy. he is opposing the gov. but you are not happy b/c is from Tigray. you guys in diaspora are blinded by hate of one ethnic group you did the same and pushed away Siye and again Dawit kebede b/c of they don’t sing your song of hate.
  One of my friend told me he hate tigraians b/c he think they are not opposing the gov. as the rest of ethiopian.
  One thing he didn’t know is Tigraians are brave people when they support or oppose they do it in full they don’t talk the work.
  Look who is the highest opposition army in diaspora yes it is TPDM. one thing you have to know is the one they oppose they go out and fight not talk like you guys for 22 years with out doing nothing.
  So i am tired of hate propaganda of ESAT/G7 against the people of Tigray while they haven’t done nothing better just only doing money collection and lie propaganda using ESAT

 5. አለም

  December 9, 2013 at 2:16 PM

  አብርሃ ትግራይም እንደ ሌላው ችግር አለበት፣ ተቃውሞም ያሰማል ለማለት ዝቶ ተነስቷል። የዛሬውና ያለፉት ዘገባዎቹ የሚያጎሉት ትግራይ ውስጥ ራሱን የቻለ የከፍተኛ ትምህርት አደረጃጀትና ለሌሎች ያልተፈቀደ ገቢና ወጪ እንደሚደረግ ነው። ለመሆኑ “ጎበዝ ሰው ደግሞ ለህሊናው እንጂ ለሆዱ አይኖርም?” ስትል እውነትህን ነው ወይስ ማንን ልታሞኝ ነው?

 6. kebede

  December 9, 2013 at 4:51 PM

  Dear Abraha Desta,

  ሁሉን ያወቁ የሚመስላቸውና ለመማር (ለማወቅ) ፍላጎት የሌላቸው ካድሬዎች የሚሉትን እንደማትሰማ አውቃለሁ። የሚናገሩት ሲያጡ ያልተጻፈ እያነበቡ የማይነበብ ይፅፋሉ። የአስተሳሰብ አድማሳቸው በዘርና በክልል የታጠረ ስለሆን በረጅሙ (በነገና ተነግ ወዲያ) በሰፊው (በአገርና በዓለም) ልክ ለማየት አይቻላቸውም።
  መቸም መምህር ነህና ማስተማርህን ትተዋለህ ብየ አልገምትም። ጉዳዩ የአገር ጉዳይ ስልሆነም ተጨማሪ ዕዳ ሊሆን ይችላል። ግን እንዳንተ ያሉ ልጆች ስላሏት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች። Thank You Mr. Abraha!!!!