አንዳርጋቸው ጽጌ! ከኢሳያስ ጉያ (ቦጋለ ካሣዬ፤ አምስተርዳም)

ማስታወሻ፡ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰሞኑን ከሲሳይ አጌና ጋር የደረጉትን ቃለ-ምልልስ አስመልክቶ በርካታ አስተያየቶች እና ጽሁፎች ደርሰውናል። አንዳቸውም በትክክለኛ ስም ስላልተላኩልን ላለማውጣት ወስነናል። ራሳቸውን ደብቀው በብእር ስም እየተጠቀሙ ሌላውን ስም እያነሱ ስብእናውን መንካት ነውር ነው።

አንዳርጋቸው ጽጌ! ከኢሳያስ ጉያ፤ ነጻነት? ወይስ ባርነት?

ቦጋለ ካሣዬ (አምስተርዳም፤19/9/2013)

 1. የግንቦት-7ቱ አንዳርጋቸው ጽጌ፤ ወያኔን በሽፍትነት ዘመኑ በአማካሪነት፤ስልጣን ከጨበጠ በሁዋላ ደግሞ በሹመት አገልግሎታል። ግልጋሎቱን ‘በቁጭት’ መንፈስ ሲናገር፤…« ውስጡ ገብቶ ማስተካከል ይቻላል  ከሚል  የዋህና ምናልባትም ደደብነት ሊባል በሚችል» እምነቱ የተነሳ እንደነበር ከኢሳት ጋዜጠኛ  ሲሳይ አጌና ጋር ባዳረገው ቃለ ምልልስ ነግሮናል። ይኼን እንደ ፖለቲካ እዳ ማየት አይገባም። ዛሬ ደግሞ ጎንቦት-7 ወያኔን ማስገደድ ወይም ማስወገድ የሚል አቁዋም ያራምዳል። ይሁን እንጂ ከፍሺስትና ባርነትን አፍቃሪው ከኢሳያስ አፈወርቂ ጉያ ውስጥ በመግባት ወያኔን እንጥላለን የሚል አደገኛ የፖለቲካ ቁማር ጫወታ፤ አሳሳቢ ጉዳይ ስለሆነ በግልጽ መወያየት ያሻል። ምን? ኢሳያስን እንዴት ባሪያ ትላለህ? አዎ ኢሳያስ ባሪያ ነው። ያውም ነጻነትን የሚጠላ ባሪያና የባሮች ኮርማ። የባሪያነቱን ምክንያት ለማወቅ ከፈለክ፤ የኢታሊያንን የቅኝ ግዛት ፖለቲካ እንዴት እንደሚያፈቅር በዚህ ጽሁፍ ግርጌ ማስታወሻ ላይ የተጠቀሰውን ተመልከት።[1] የአገርህንም እድሜ ከየት ጀምሮ እንደሚቆጥርና፤ የቆጠረበትንም ምክንያት በተራ-ቁጥር 13 ተጽፎአልና ልብ ብለህ እንብብ።  ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ….

 


[1] በ1995 የኢታሊያው ፕሬዝዳንት፤ ሊዊጂ እስካልፋሮ በኢትዮጵያና በኤርትራ የስራ ጉብኝት አድርጎ ነበር። ታዲያ ለዘመን መለወጫ የእንኩዋን ደስ ያላችሁ መልእክቱን ለኢታሊያውያን ሲያስተላልፍ፤ ኢሳያስ የነገረውንም አካፍሎ ነበር። “የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ፤ የለም የኤርትራው ማለቴ… የነገረኝ ልቤን ነካው። እንዲህ አለኝ። የቅኝ ግዛት ፖለቲካ ገዳይና አዋራጅ ነው። የኢታሊያ የቅኝ ግዛት ፖለቲካ ግን የተቀደሰ ነው። ለዚህም ነው ክቡር ፕሬዝዳንት የእኛ ፍቅር ሁል ጊዜ እንደጋለ(ሳይቀዝቅዝ) የቀጠለው።” ኢሳያስ እንግዲህ ይኼን ያለው፤ የገንዘብ እርዳታ ፈልጎ ወይም ከልቡ ሊሆን ይችላል። ለገንዘብ ሲል ምንም የማያደርገው ነገር የለም። ኢሳያስ አፈወርቂ የነጻነት መንፈስ የማያውቀው የፍሽት ባሪያ ነው የምንለው ለዚህ ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 26, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

9 Responses to አንዳርጋቸው ጽጌ! ከኢሳያስ ጉያ (ቦጋለ ካሣዬ፤ አምስተርዳም)

 1. Nesanet

  September 26, 2013 at 4:04 PM

  Ethiomedia and ethioforum and Ethiopian review are now showing the real job here in the diaspora .all the fake opposition website will continue to follow thier way very soon.we Ethiopians are smarter than that.this website who always like us to read thier Monday article by professor Almayehu and make their money when ever we open thier website are most of them weyane friendly who do not that much care about the poor Ethiopians who are hunted by weyane killers and displaced from thier place by Arab and china investors.

 2. asteryaye

  September 26, 2013 at 4:29 PM

  @ቦጋለ ካሳየ
  ጽሁፉን በትግረኛ ብትጽፈው ትርጉም ይሰጥ ነበረ.ለሰልፉ ደግሞ 22 አመት ሙሉ የቾሁት ሁሉ አንድ ቀበለ እንኩዋን አልያዙም.ለተቅውማች ሰማይ ቅርቡ ነዉ.አንተ ደግሞ በረሃ ገብተህ የፈላ ዉሃ ልትጠጣ ቀርቶ አዲስ አበባ ማኪያቶ እይጠጣህ የምትታገል አዪደለህም.ስማ አንተ የበርገር አሪበግኛ ወያኒ በ ፈስቡክ የሚዎድቅ አዪደለም እና አታዘናጋ.አፍህን ዝምብ እንዳዪገባበት ብትዘጋዉ ጥሩ ነዉ.

 3. Gudeta

  September 26, 2013 at 8:41 PM

  The writer of this useless article must be pro woyane traitor who has no idea about the current reality of Ethiopian politics. Andargachew is fighting to free the writer from an apartheid system imposed on him by the tigre liberation front. ” wishaw yichohal tiglu gin ketilual”.

 4. ewnet yashenfal

  September 27, 2013 at 3:41 AM

  yewereket jegna andargachew bemeselew mengede hedual bezume degafe alew . Yegna awaki yemiserawen bemetechet gezahen kemetatefa antem tekekel new yalkewn besera asaye kezihe behuala yemisemahe yelam

 5. Dejach Geresu duki

  September 27, 2013 at 5:06 AM

  Wow

  It is really a very genuine analysis , I admire the writer of this article. It has been long time I read this type of article. An article based on fact;the ultimate goal of the writer is to show the destructive mission of the anti Ethiopian mercenary groups which have been lead or organized by issayas afewerki ,the alliance and role of Ginbot 7 .
  Andargachew and G7 are busy for the second round anti Ethiopia campaign Inorder to destroy Ethiopia as a country. It seems like that!!

 6. Endalkachew

  September 27, 2013 at 4:58 PM

  I am really disappointed by the article Ato Bogale wrote. It is really unnecessary and a complete waste of time. He sounds like he is more interested how to spice his words rather than tackle the problem Ethiopia is facing. He also harbors some grudges or hate for Ato Andargachew for reasons we don’t know. He spent all his time to write this long article to merely attack Ato Andargachew.

  Sometimes, it surprises me how we have become so shameless to critize and even insult someone who said I am going to go and fight. This is annoying especially when the critic does not do anything manly except to sit at a keyboard and shoot long and boring articles.

  I think he should get off his big behind and go and grab an AK-47 and fight instead of pumping insulting articles hiding here in Europe or America.

  I suggest he reads the article published on the Habesha website, ” Democracy, Tolerance, and G7’s policy on Eritrea”

 7. Bertu

  September 27, 2013 at 9:46 PM

  ለመሆኑ ይህ ፅሑፍ ማንን ለመጥቀም ነው የተጻፈው?

  ከምንም ነገር በላይ ወያኔን የሚያክል ከእርቅ በላይ የሆነ የኢትዮጽያ ጠላት ተቅመጦ ባቅሙ የዘላለም ጠላት ወያኔን (እንደ ዲያብሎስ ያለ ማለት ነው) ሊያጠቃን የተነሳን ሃይል ለማውገዝ ይሄን ያህል መድከም እጅግ የማይርሳ ክህደት ነው። “አባይ የሚያድርበት የለው፤ ግንድ ይዞ ይሄዳል” የተባለውም ይሄንኑ ነው።

  ሁሉም በየፊናው ባመነበት መንግድ እንደ ደቡብ አፍሪካ ታጋዮች አንዱ አንዱን ሳያሳጣ የዘላለም የኢትዮጽያ ጠላት የሆነው ወያኔን ከምድር ላይ ለማጠፋት ብቻ ገንዘቡን፤ ጉልበቱን፤ እውቀቱን፤ ህሊናውን መስዋእት ለማድረግ ያለተንሳ ሁሉ እሱ እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው። በተለይ በአሁን ሰዓት ሃገራችን ኢትዮጽያ ያለችበትን ሁኔታ እያወቀ በተቃዋሚ ኃይሎች ላይ ብዓዕሩን የሚያንሳ ሁሉ እሱም እራሱ እኩል የኢትዮጽያ ጠላት ነው።

  መቼም ለሱም አልታዘዝንለትም እንጂ፤ እንደኔ እንደኔ 11ኛው የፈጣሪ ትዕዛዝ “የምትወዳትን ኢትዮጽያ ሃገረህን ገድሎ ለመቅበር የተነሳው ጠላትህ እስኪ ወድቅ ድረስ፤ ባቅማቸው ሊያድንዋት የተነሱትን ሁሉ ስማቸውን በክፉ አትንሳ” ቢባል በእውነት እንዴት ደስ ባለኝ ነበር።

  ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር! ዓሜን
  በርቱ

 8. Abraham

  September 27, 2013 at 10:51 PM

  ምነው እነዚ ዌብሳይቶች አይጋ ፎረም አይጋ ፎረም ሸተቱ?

 9. Samson

  October 1, 2013 at 7:27 PM

  አቶ ቦጋለ የመንገዱን ምርጫ መተቸት አደጋውንና ጥቅሙን ሚዛን ላይ ማስቀመጥ ጥሩ ነገር ነው። ተቋምን በግለሰብ መመንዘርና ይልቁን ብርሃኑና አንዳርጋቸውን ብቻ ነጥሎ መዘልዘል በግንቦት ሰባት ውስጥ ያሉትን አባላቱንና ደጋፊዎቻቸውን ማዋረድ ማሳነስና መስደብ ነው።

  ከጽሁፉ መረዳት የሚቻለው ነገር ግለሰቦችን የጥቃት ዒላማ በማድረግ ሁሉን መኮነን የፈለጉ ይመስላል። በዚህ እውቀትዎና ድፍረትዎ ከብርሃኑ ወይም ከአንዳርጋቸው የተሻለ ነገር ያልሰሩ ከሆነ የወነጨፉት ስድብ ሁሉ ወደርስዎ ተመላሽ ነው።

  ምልከታዎ በጥቅሉ በድርጅቱ ላይ ቢሆን መልካም ነበር። $500 ከፍለው ከሆነ ብሬን ምን አረጋችሁት ብሎ መጠየቅ ሳይቻል አይቀርም። ካልከፈሉ ግን ወደው የሰጡት ይሁን ባሉ እርስዎ ምን አሳሰበዎ? ስለዚህ እንትናና እንትናዎት የግል ችግር እንዳይመስልብዎ ዋንኛ የሚሉትን ጥያቄዎን አቅርበው ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር። ያሰለቸን ስድብ፣ ጠለፋና አሉባልታ ነው። ዒላማችን ግለሰቦች አይሁኑ ጉዳዮች ላይ እናነጣጥር ያኔ ልዩነታችንን ማቻቻልና መማማር አይከብደንም።

  መልካም ጊዜ