አንበሳ አውቶብስ ተገልብጦ ሰዎች ሞቱ (ተጨማሪ ዘገባ አለን)

ዛሬ ማለዳ 12:55 ላይ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ውስጥ ገብቶ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
አደጋው የደረሰው ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው 36 ቁጥር የከተማ አውቶብስ ፥ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ነው።
anbessa bus2
በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይዎታቸው ያለፈ ሲሆን 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአውቶብሱ አሽከርካሪና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት መትረፋቸው ታውቋል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በጥቁር አንበሳና ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ሲሆን አውቶብሱን ከገባበት ገደል ለማውጣትም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።
anbessa bus
———————-

(ተጨማሪ ዘገባ Nati man)

የቢሾፍቱ ባስ….???
በዕለተ እሁድ ከካራ ወደ መርካቶ ሲጓዝ የነበረው የአንበሳ አውቶቡስ ከገባበት 40 ሜትር ገደል ጉዳተኞችን ለማውጣት ከ3 ሰዓት በላይ እንደወሰደ ለማወቅ ተችሏል ፤ ውስጡ ይዞ ይጓዝ የነበረው በርካታ ተጓዥ ውስጥ ራሱን ችሎ ከአደጋው የወጣ አንድም ሰው አለመኖሩን ሁሉም በቃሬዛ እና በሰዎች እርዳታ ከገደል ውስጥ መውጣታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል ፤ 9 ሰዎች ሲሞቱ እንደ መንግሥት መገናኛ ብዙሀን ዘገባ 68 ሰዎች ከፍተኛ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

Bishofetu bus

Bishofetu bus

አውቶቡሱን ለማውጣት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ እስከ 8 ሰዓት ድረስ በተደረገ ያላሰለሰ ሙከራ ከስምንት ሰዓታት ቆይታ በኋላ ሊወጣ ችሏል ፤ የገደሉ ጥልቀትና የቦታው አለመመቸት ጉዳተኞችን በቀላሉ ለማውጣት አለማስቻሉ በተጨማሪ እርዳታ ሰጪዎችን በብርቱ ፈትኗል ፤ በቅርቡ ከዓመት በፊት ‹‹ቢሾፍቱ›› እየተባሉ የሚጠሩት በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተመርተው ወደ ሥራ የገቡት አውቶቡሶች ከቀድሞዎቹ ጋር ሲነጻፀሩ ከፍተኛ አደጋ እየበዛባቸው በየቦታውም ከቀላል እስከ ከባድ እክልም እየገጠማቸው ይገኛል ፤ አንበሳ አውቶቡስ ለእነዚህ አገር ውስጥ ለተገጣጡ ባሶች 500 ሚሊየን ብር መክፈሉ ይታወቃል ፤ በአንበሳ አውቶቡስ ታሪክ ሙሉ ሰው ይዞ ገደል የገባው በቢሾፍቶ የተገጣጠመው የመጀመሪያው የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ነው ፤ አውቶቡሱ የተገጣጠመበት እቃ ስታንዳርዱን ያለመጠበቁ ፤ ከፍተኛ ሰው ሲጭን ወደ አንድ ጎን ማጋደሉ ፤ የፍሬንና መሰል ችግሮች አሉበት በማለት ሹፌሮች አስተያየታቸውን ቢሰጡም ሰሚ ያገኙ አይመስሉም ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከ3 ወር መፊት ከፈረንሳይ ወደ ስድስት ኪሎ ሲመጣ የነበረ አንድ የከተማ አውቶቡስ(ቢሾፍቱ) በአንዲት ድንጋይ ድጋፍ ከ100 በላይ ሰዎች መትረፋቸው ይታወቃል ፤ በሌላ በኩልም ይህው ባስ ከ6 ወር በፊት መሀል ካሳንቺስ ላይ ሁለት የፊት ጎማዎቹ ተነቅለው በመብረር መሀል አስፋልት ላይ በቸርኬው መቆሙ የሚታወስ ነው…..
አውቶቡሱ የመገጣጠሚያ ዋጋ ማነስ ላይ እና ሀገር ውስጥ መገጣጠሙን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት በመቁጠር ጥራቱን ያልጠበቀ አውቶቡስ ወደ ገበያ ማስገባት ለእንደዚህ አይነት አሰቃቂ አደጋ ይዳርጋል ፤ ስለዚህ የሚመለከተው አካል የሕዝብ ሕይወትን ለመታደግ ያስችለው ዘንድ ጥራቱን ጠብቆ አለማቀፋዊ መስፈርቱን አሟልቶ መመረቱን ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 23, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to አንበሳ አውቶብስ ተገልብጦ ሰዎች ሞቱ (ተጨማሪ ዘገባ አለን)

  1. ዘላለም ብሩ

    March 23, 2014 at 9:58 AM

    የሚያሳዝን አደጋ ነው:: “ድልድይ ውስት ገባ” ማለት ምን ማለት ነው ? ከ ድልድይ ላይ ተገለበተ ለማለት ነው ? ከድልድይ ላይ ወደ ታች ተከሰከሰ ለማለት ነው ?

  2. TERUBE

    March 24, 2014 at 7:54 AM

    ZEM BELO YETQTEQET QOREQORO TERATUN YALTBQE TESHKREKARI GENA BEZU SEW YALQALE