አቶ ኃይለማርያም እና ኤርትራ – ግርማ ካሳ

(muziky68@yahoo.com)

“Hailemariam Desalegn a perfect mimic of Meles” በሚል ርእስ ሥር በኢትዮሜዲያ የቀረበች አጭር ትንተና አነበብኩ። የአቶ ኃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬን እንዲሁም ልጃቸው ዮሃናን በተመለከተ በተጻፈው ላይ ትንሽ የግሌን አስተያየት እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።

የአቶ ኃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ኤርትራዊት እንደሆኑ ተገልጿል። አቶ መለስ እናታቸዉ አዲ ቋላ የተወለዱ ኤርትራዊት በመሆናቸዉ «ለኤርትራ ያደላሉ» ይባሉ እንደነበረዉ፣ አቶ ኃይለማርያምም ባለቤታቸው «ኤርትራዊት» በመሆናቸዉ ልባቸው ሻእቢያ ጋር ነዉ የሚል እድምታን ለማሳየት የተሞከረ ይመስላል።

ወ/ሮ ሮማን ኤርትራዊት መሆናቸዉን ለማሳየት ፣ ለመጀመሪያ ሴት ልጃቸው የተሰጠዉ «ዮሃና» የሚለዉ ስም እንደ ዋና መረጃነት ቀርቧል። «ዮሃና» የሚለው ስም «እንኳን ቀናህ፤ እንኳን ተሳካልህ» (Congratulation) ማለት እንደሆነና የብዙ ኤርትራዉያን ስም መጠሪያ እንደሆነ በመግለጽ ነዉ የወ/ሮ ሮማን «ኤርትራዊነት» የታወጀዉ። Read full in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 20, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.