አብርሃ ደስታ… ታስሮ ተፈታ!!

EMF – በትግራይ ውስጥ የሚደረጉ ግፍ እና በደሎችን ያለመሰለስ በማጋለጡ ይታወቃል:: ለሰብአዊ መብቶች መከበር በመቆሙ ከህወሃት ሰዎች ተደጋጋሚ ማስፈራሪያ እና ዛቻዎች ሲደርሱበት ነበር:: ባለፈው ሳምንት ቃሊቲን ለመጎብኘት የፖለቲካ እስረኞችንም ለመጠየቅ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በነበረበት ወቅት “እንዴት የፖለቲካ እስረኛ ለመጠየቅ ከትግራይ ድረስ መጣህ?” በሚልም ለእስር ዳርገውታል:: ሁኔታውን እራሱ አብርሃ ደስታ እንዲህ በማለት ገልጾታል::

አዲስ አበባ ነበርኩ። ሰኞ ጧት ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌና ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ለመጠየቅ ቃሊቲ ማረምያቤት ሄድኩኝ። ጥበቃዎቹ ወደ ማረምያቤቱ አስተዳዳሪ ወሰዱኝ። አስተዳዳሪው ምርመራ ይሁን ዛቻ በማይታወቅ መልኩ ካስፈራራኝና ከሰደበኝ በኋላ ከማረምያ ቤቱ ተባረርኩ። አስተዳዳሪው “አንተ ከትግራይ አክራሪ አማራዎችን ለመጠየቅ ስትመጣ አታፍርም?!” አለኝ። ከፈለኩ ብሄር ብመጣም የፈለኩትን ሰው የመጠየቅ መብት አለኝ። የታሰረ ሰው መጠየቅ አያሳፍርም” መለስኩለት። ካሁን በኋላ “ወደ ቃሊቲ የምትገባው ታስረህ ካልሆነ በቀር እነ አንዱኣለምን ለማየት ድርስ አትላትም!” ብሎ ፖሊሶችን እንዲያስወጡኝ አዘዘ።

ወደ ቂሊንጦ ማረምያ ቤት ተጓዝኩ፤ ኡስታዝ አቡበክር አህመድን ለመጠየቅ። “አሸባሪ ለመጠየቅ መጣ” ተብዬ ለሦስት ሰዓታት ታሰርኩ። የቂሊንጦ ማረምያቤት ዋና አስተዳዳሪ እምባዬ ህቡዕ “አሸባሪዎችን ለማበረታታት መጣህ፣ ማረምያቤቱን ለመበጥበጥ ነው የመጣኸው። እንዳውም አሁን በማረምያቤቱ ረብሻ ተነስቷል። ስለዚህ ይታሰር” ብሎ በማዘዙ ወህኒቤት ዉስጥ ቆየሁ።

ዝርዝር ጉዳዩን ለመፃፍ እሞክራለሁ። አንዱኣለም አራጌና ርእዮት አለሙን አላየኋቸውም። አቡበክር አህመድ (ና ሌሎች ጉደኞቹ) ግን አግኝቻቸዋለሁኝ። እነ አቡበክር አህመድን በማግኘቴ ደስ ብሎኛል።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 27, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

5 Responses to አብርሃ ደስታ… ታስሮ ተፈታ!!

 1. አለም

  February 27, 2014 at 11:04 AM

  የማይመስል ነው። እስላም አሸባሪ ተብለው የታሰሩትን ጠይቄ እነ አንዱ አለምን ሳልጠይቅ መጣሁ ነው የሚለው? የአብርሃ ደስታን ጽሑፎች ባነበብኩ ቁጥር ጥያቄ እየፈጠረብኝ መጥቷል። ከአውራምባው ዳዊት ከበደ አካሄድ ጋር በጣም እየተመሳሰለብኝ ነው። የምለውን ለማረጋገጥ የሚፈልግ የአብርሃን ጽሑፎች አከታትሎ ማንበብ ይበቃዋል።

 2. Bertu

  February 28, 2014 at 6:12 PM

  “The ultimate measure of a man is not where he stands in moments of comfort and convenience, but where he stands at times of challenge and controversy.” Marin Luther King Jr.

  Ethiopia will never forget you. NEVER.

 3. አንድነት በርሃነ

  February 28, 2014 at 10:17 PM

  አለም በመጀመርያ ዳዊት ከበደን ከአብረሃ ደስታ ጋር ማገኛኘት ማለት በጣም የተራራቀና መሰረት የሌለው በመሆኑ በመጀመርያ ለማወቅ የሚያስፈልግህ አብረሃ ደስታ በወያነ መሃል ተቀምጦ ኢሰባዊ ተግባራቸውን አፋኝ ስራታቸውን በግልጽ በመቃወም በድፍረት በትግራይ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በድህረ ገጽ በማስተላለፍ የአሪና ስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን አኩሪ የሆነ ተግባር የሚሰራ ደፋር ሙህር ነው: በመሰረቱ የጽሁፉን ይዞት በቅጡ ያልተረዳሃው ጭፍን (ጨለምተኝነት) ያለህ ትመስላለህ ባሁኑ ወቅት ለዚህች ሃገር ክቡር ሕይወታቸውን ሳይሳሱ የኑሮ ቅምጥል የስልጣን ፍቅር ስያሸንፋቸው የህዝብን ሶቆቃ መብትና ነጻነት የኛ ብለው በትግል የግል ኑሮና ቤተሰብ ሳያስቡ የሚያደርጉትን ያለ ጥፋታቸው ድምጻችን ይሰማ በማለታቸው እንዳንት ቤምሰሉ እውነት ያሸነፋቸው ሰብአዊነት የሌላቸው ደካማዎች ስም እየለጠፉ አሸባሪ የተባሉት ብርቅዮ የኢትዮጵያ ልጆች ሄዶመጠየቅ እነ ኡስታዝ አቡበከርን ብቻለማግኘት ሳይሆን እነርዮት አለሙን አንዷለም አራጌን እስክንድር ሌሎችንም ለማየት ነበር ነገርግን ለተወሰነ ጊዜ የታስረበት እነ አቡበከርን በማግኘቱ ተደሰትኩ ማለቱ ያንተን ደካማ አስተሳሰብና ያለህን የግል ፍራቻ በመሆኑ እንዲህ ያለ ገንቢ ያልሆነ ትችት ያስወቅሳል ፈረንጆች እንድሚሉት አንዷጣት ሌላውን የምያማላክተው ሥስቱ አንተን ያመላክታሉ; ስለዚህም ከመጠራጠር አንተስ ስለወገኖችህ ምን አድርገሃል? መጀመርያ ራስን መጠየቅ አስፈላጊ በመሆኑ ያልተጨበተ ማስረጃ የለእለው አሉባልታ አስፈላጊነት ስለሌለው ያትሳሳት

 4. አለም

  March 1, 2014 at 11:17 AM

  ውድ አንድነት,
  ሳይታወቅህ ስንት በታኝ ነገር ዘባረቅህ:: እኔ ያልኩት:- አብርሃ የሕወሃትን ግፍ የሚቃወም ይምሰል እንጂ ደጋፊ ነው:: መረጃ አለ; መረጃው በተከታታይ የሚጽፋቸው ጽሑፎች ናቸው:: ዳዊት ከበደም መጨረሻ ላይ ማንነቱ ተገለጠ እንጂ ተቃዋሚ ነው ተብሎ ዓለም አቀፍ ሽልማት ሁሉ ተቀብሎ ነበር:: ልሰደድ መሄዴ ነው ብሎ ግብዣ ተደርጎለት አሜሪካ ሄደ:: ድንገት ብድግ ብሎ አገር ቤት ሄጄ እታገላለሁ አለ:: አብርሃ ሆነ ዳዊት ካለነሱ በቀር ሰው ሁሉ ቂል እንደ ሆነ ያስባሉ:: ይልቅ ቂልስ እነርሱ:: አንተን ከነርሱ መደዳ እንዳልጨምርህ ብዙ አላውቅህም:: እውነቱን ከፈለግህ ግን አብርሃ የጻፋቸውን አከታትለህ አንብብ:: አንብበህ እውነቱ ካልታየህ ደግሞ ምን ይሉኛል ሳትል ሌሎች እንዲያስረዱህ ጠይቅ::

 5. Love4 Ethiopia

  March 1, 2014 at 9:02 PM

  ኣብርሃ ደስታ የታወቀ የስራቱ ተቃዋሚ መሆኑ የአለም ምስክርነጥ አይኣፈልግም:: እንድኣውም አለም
  ትF ታጠራጥራለህ አንተው ወያነ ትሆን?