አባባሱባት…! (ወንድሙ መኰንን)

ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌ ጥቃት እንደተሰነዘረባት ነው። ክፉ ክፉው መዘዝ የሚመዘዝባት፣ ሁዳዴ ጾም አካባቢ ነው። በዙ አሳልፋለች። ይንከባከቧታል ተብለው ታምነው የነበሩ ትላልቅ አባቶች እየመዘበሯት ስላስቸገሩ፣ መነኲሴ አንዴ ሙቶ ተገንዟልና አደራ አይበላም ለገንዘብና ለሥልጣን አይጓጓም ተብለን ለመነኲሴ ነኝ ባዩ ግለሰብ ቢያስረክቧት፣ እንኳን ሊሻላት እንዲያውም አባባሱና፣ አረፉ..
Click here for PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 29, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to አባባሱባት…! (ወንድሙ መኰንን)

 1. Abiy Ethiopiawi+Segawi/wemenfesawi+አቢይ+ኢትዮጵያዊ+ሥጋዊ-ወመንፈሳዊ

  March 31, 2013 at 11:17 AM

  “አባባሱባት”ተው አትበለኝ።
  ፨፨፨መቼም የለንደን ደብረፅዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን ታሪክ እኔም ስኖረው ከአቶ ወንድሙ መኮንን ባልተለየ ሁኔታ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ሆኖኛል፤ምንም እንኳን ፊት ለፊት ባልጋፈጥም።ምክንያቱም በውቅቱ የነበሩት ተሟጋቾች ሁሉ አዲስ ሰው ሃሳብ እንዲሰነዝር ፋታ አይሰጡም ነበር፤እናም ማንንም ኢትዮጵያዊ የለንደን ኗሪን ከዚያም ጀምሮ ሆነ ዛሬም ባለመሳተፋቸው አልወቅስም።ያ ችግር አሁንም ድረስ በጉልህ አለ።የሚናገሩት፣የሚሯሯጡት፣የሚሾሙት፣ የሚሽሩት እና ሌሎችንም ተግባራት የሚያደርጉት ከዛሬ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት የማውቃቸው ሰዎች ናቸው።በዚያን ወቅት ችግሮቹ ቅርጻቸው ሌሎች ነበሩ።እኔ እንኳን የቤተክርስቲያን የተራ ዕድር ስብሰባም አይመስለኝም ነበር።
  እኔስ ስመጣም ለፀሎቷ ስለነበር ደጇን ተሳልሜ የልቤን ተማክሬ እመለሳለሁ እሷም የማይከፈል ምልጃዋን አበርክታልኛለች።ለዚህም ነው ይህን ሥነ-ግጥም ለእነ አቶ ወንድሙ መኮንንም ሆነ ለእነ ቄስ አባተ የማበረክትላቸው።በይቅርታ ፍቅርን እንዲያመጡልን።

  የጭንቅ አማላጇ ለሁላችንም ቀናውን መንገድ ትምራን።

  “አባባሱባት”ተው አትበለኝ።

  በዚህች ፅዮን የቅድስት ደጃፍ፤
  በልቤ ፅላት ምልጃዋ ሲጻፍ፤
  በስደት ቤቴ ምን ሌላስ አለኝ?
  “አባባሱባት”
  ተው አትበለኝ።
  እባክህን ሆድ-አይባሰኝ፤
  እንደአባቴ ተስፋ አውርሰኝ።
  የ”ወላላይቱ”ቤተ-መቅደስ፤
  በርኩስ ልሳን ሲታመስ፤
  ቅዱስነቱን እያወቁት፣
  ምእመናኑን ንቀው በሽሙጥ ቃል ሊያስቁት፤
  ይሆናል እንጂ ለእምነት-ቢስ ለቧልተኞች፤
  አይሆንም ቃሉ ለተዋህዶ፣
  ለክርስቲያን ለአማኞች።
  ተው አይገባም፤ቦታው አይደለም፤ይሄ ሕብረ-ቃል፤
  ቅስፈት ነውና መርዝ ሆኖ፣በቃሉ ብቻ ሰው ያንቃል።
  እናም፣
  ያለእሷ ደጃፍ ስለሌለኝ፤
  “አባባሱባት”
  ተው አትበለኝ።
  መብቱ ተርፎልን በፍትህ አገር፤
  እንደው ስንችል መነጋገር፤
  አልፈን ተርፈንም ለመከራከር፤
  ለመገላለጥ አንዲቷም እንከን ሳትቀር፤
  በንፁህ ሕሊና በአመኔታ፤
  ተስፋ ሳንቆርጥ ልብ ሳንፈታ፤
  ማየት ስንችል በዕድሜ ፀጋ፤
  በጎም አይደለም ከኃጢያተኞች፣እየቦደንን ስንጠጋ።
  ዕውነቱን አውቀን ሐቁን ለማየት፤
  ከእኛ መካከል አጥፊን መለየት።
  ታጋሽ ሰው ሁኖ ሁሉን አክብሮ፤
  መፍታት ሲቻለን ቅን ተነጋግሮ፤
  በሕብር ቃላት ማደነባበር፤
  በጎን ተኺዶ ሓቅን ለመቅበር፤
  አያስፈልግም ብዙ መናገር፤
  ይልቅ ተንኮልን ይቅርታ ይስበር።
  ወንድሜ ቃሉን ሳውቅ አታታለኝ፤
  “አባባሱባት”
  ተው አትበለኝ።
  ሰውን ማዋረድ ክብርን ማሳጣት፤
  በጥፋት ላይም ወንጀልን መስራት፤
  በመጠራጠር ዕምነትን መናድ፤
  በጎ የተሰራውን አውቀውት መካድ፤
  ከእምባችን ጀርባ ለሥጋ ማደር፤
  ጥቅም በመሻት ለጥፋት ማበር፤
  ይህ ክፋት እንጂ የዚያ የሰይጣን፤
  ፍጹም አይደለም የቅን ክርስቲያን።
  እናም ወንድሜ አባክህ ስማኝ፤
  የኔንም ጩኸት ተው አትቀማኝ።
  ወንድሜ ዕውነትም አለህ፤
  ባለመታገስ ታምታታዋለህ።
  እናም…..
  ያለእሷ ደጃፍ፣
  እኔ እንደሌለኝ፤
  “አባባሱባት”
  ተው አትበለኝ!!!