አቡነ ጳውሎስ ታገዱ

አውራምባ ታይምስ (13 July 2009) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሲኖዶስ ጉባኤ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ፓትሪያርኩ አቡነ ጳውሎስን ከአስተዳደራዊ ስራዎችና ከሲኖዶስ ሰብሳቢነት ማገዱን የስብሰባው ተሳታፊ የነበሩ ብጹአን አባቶች ለአውራምባ ታይምስ ገለጹ፡፡

ፓትሪያርኩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪ የሆኑትን አቡነ ሳሙኤልና በሲኖዶሱ የተቋቋመውን ስራ አስፈጻሚ እንዲታገዱ ማድረጋቸውን ተከትሎ በሲኖዶሱና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መካከል የከረረ ውዝግብ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡

የጉዳዩን ጡዘት ተከትሎ ሲኖዶሱ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ፓትሪያርኩ የወሰዱት የእግድ እርምጃ አግባብ አለመሆኑን መርምሮ በአቡነ ጳውሎስ ላይ እገዳ እንዳደረገባቸው ስብሰባው አሁንም ዝግ ሆኖ መቀጠሉን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሊቀ ጳጳስ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on July 13, 2009. Filed under NEWS. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.