አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ሆኑ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትሪያርክ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ በኋላ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያለ ፓትሪያርክ ላለፉት ስድስት ወራት ቆይታለች። በዛሬው እለት ግን ምርጫው ተጠናቆ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛ ፓትሪያርክ መሆናቸው ተገልጿል።

በተባለው የምርጫ ቆጠራ መሰረት፤ 806 መራጮች ከጳጳሳት፣ ከገዳማት፣ ከአብያተ ቤተ ክርስቲያናት ተመዝግበው የነበረ ሲሆን፤ በምርጫው ውጤት መሰረት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – 39 ድምፅ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – 70 ድምፅ፤  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – 98 ድምፅ፤  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – 98 ድምፅ አግኝተዋል። ሆኖም ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ፤ ከሌሎቹ የላቀ ውጤት በማግኘት የተመረጡ መሆናቸው ተገልጿል።

ከ806 መራጮች ውስጥ አንድ የድምፅ መስጫ ወረቀት፤ ምርጫ ሳይደረግበት ባዶውን ስለተገኘ፤ ከቆጠራው ውጪ ሆኗል። ፡

Abune Mathias

Abune Mathias

ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስም ከምርጫው ሂደት በኋላ፤ የምርጫውን ውጤት እና ሲመቱን የሚቀበሉ መሆናቸውን፤ እንዲህ በማለት አጭር ንግግር አድርገዋል። ‹‹ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋራ አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፤›› ብለዋል፡፡

እሁድ በዓለ ሲመቱ ከተፈጸመ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ተመልክቷል፡፡

ለምርጫው በአጠቃላይ ብር 3,650,000 ወጪ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተናግረዋል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው አራት ንኡሳን ክፍሎች ነበሩት – የመራጮች ምዝገባና ቁጥጥር፤ የሕዝብ ግንኙነት ንኡስ ክፍል፤ የሎጅስትክ ንኡስ ክፍል፤ የሒሳብና በጀት ንኡስ ክፍል ነበሩ።፡

ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የተሳተፉት መራጮች፡- ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ፣ ብፁዕ አቡነ ራፋኤል፣ ብፁዕ አቡነ ቢነም፣ ብፁዕ አቡነ ቢሾይ፣ ብፁዕ አቡነ ሂድራ ሲኾን በታዛቢነት የተወከሉት ካሚል ሚሸል ናቸው፡፡ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ጣቢያ(ሲቲቪ) የምርጫ ውሎውን በቀጥታ ሥርጭት አስተላልፏል፤ ለበዓለ ሢመቱም ተመሳሳይ ሽፋን እንደሚሰጥ ተገልጧል፡፡

ራሳቸውን ከምርጫው ሂደት አግልለው የቆዩት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በምርጫው የቀትር በኋላ ውሎ ተገኝተዋል፡፡

በሌላ ማስታወሻ:

እ.ኢ.አ በ1993 ዓ.ም. ምኒሊክ መጽሄት ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ነበር። በቃለ ምልልሱ መጨረሻ ላይ “ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦላቸው ሲመልሱ እንዲህ ብለው ነበር።
አቡነ ማቲያስ፡- እኔ በእውነቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የማስተላልፈው መልዕክት ጥንታዊ ፤ ታሪካዊ እና መሰረታዊ የሆነው ታሪካችንን መጠበቅ አለብን ፡፡ ሰው ኃላፊ ነው ፤ በስልጣን ላይ የሚወጣ ሰው ለዘላለም አይኖርም ፤ ታሪክ ግን ዘላለማዊ ነው ፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰላም ሀገር የአንድነት የሕብረት ሀገር መሆን ይኖርባታል፡፡ እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ሁሉ ኢትዮጵያም አንዲት ናት ብለን ነው እኛ የምናምነው ፡፡ ስለዚህ ስለ አንድነቱ እና ስለህብረቱ ማሰብ አለበት ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ሁሉ ነገር ሃላፊ ነው ፡፡ ነገር ግን ታሪካችን የሚቆይና የነበረ ስለሆነ ታሪካችንን መጠበቅ ይገባናል፡፡ ተባብረን ተስማምተን ተፈቃቅረን ተረዳድተን እገሌ እገሌ ሳንባባል በቋንቋ ፤ በጎሳ ፤ በወንዝ ፤ በሸንተረር ሳንለያይ ህብረታችንን ጠብቀን መኖር አለብን፡፡ የፖለቲካ ጉዳይ እንደሆነ ተለዋዋጭ ነው፡፡ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአለም ላይ የሚካሄድ ነገር ነው፡፡ ያለውን ችግር ተደጋግፈን አንድ ላይ ሆነን ነው እንጂ ልናስወግድ የምንችለው በጎሳና በቋንቋ ተለያይተን ምንም የምናስወግደው ችግር አይኖርም፡፡ ተባብረን ችግራችንን ፤ ርሀቡን ፤ ድንቁርናውን በሽታውን ጦርነቱን ቸነፈሩን የምናስወግድበትን መንገድ ነው መፍጠር ያለብን ፡፡ በድህነታችን ላይ እርስ በእርሳችን ስንጣላ ተጨማሪ አጥፊ የሆነ ነገር ነው የምንገዛው ፡፡ ልጆቻችን መጥፎ ነገር እንዳይማሩ ፤ መለያየት እንዳይወርሱ ፤ ለእነርሱ መልካም የሆነውን ነገር እንድናወርስ ድሮ አባቶቻችን ያቆዩልንን እንድናስረክባቸው አደራ እላለሁ ፡፡ ሀገራችን አንድነትና ሰላም የሚመጣበት ጊዜ ይኖራል፡፡

 

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 1, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to አቡነ ማትያስ 6ኛው ፓትርያሪክ ሆኑ

  1. ኦይቻ ኦኒ_ኦኔ

    March 6, 2013 at 5:06 PM

    1.አቡነ ማትያስን በመጠኑ አውቃቸዋለሁ::ለኔ በ”ምርጫ”ና በ”ሹመት” መካከል ልዩነት ያለው ይመስለሻል::ይህ የአሁኑ ሹመት ነው ወይስ ምርጫ የሚለውን ለማጣጣም ጥቂት ቀናትና ትንሽ ተጨማሪ መረጃ ያሰፈልገኛል:: ኣዲስ አድማስ ባለፈው እትሙ አንዳንድ መላ ያለው ነጥቦች አንስቶ ነበር::የዚያ አይነት ማለቴ ነው:;

    2. ከአሰር አመት ይሁን ከዚያ በፈት አቶ አሰፋ ጫቦ ስለአቡነ ማትያስ አንድ ይሁን ሁለት ጊዝ መጣጥፍ አቅርቦ ነበር:;አቡነ ማትያስም መልስ ሰተዋል::ሁሉም የታተመው አሁን በተዘጋው ቤኢትዮጵ ነበር:;ዝርዝሩን አሁን በሙሉ አለስታውስም:: አግኝታችሁ ብታወጡት ጥሩ መለለኝ;;ገላጭም አነጋጋሪም ሊሆን ይችላል
    አንደ ስራቸው ይስጣቸው!!