አስደንጋጭ ዜና! ተጠንቀቁ! (ሹክሹክታ)

ወሬውን በዜና መልክ ለማቅረብ ተጨማሪ መረጃ ባለማግኘታችን፤ “ሹክሹክታ” ብለነዋል – ርዕሱ ላይ። አንዳንዴ በሹክሹክታ መልክ የምንሰማቸው ወሬዎች እውነት ሆነው ይገኛሉ፤ አንዳንዴም ሹክሹክታው ህዝብ ጆሮ ከመድረሱ በፊት ቶሎ እርምት ይደረግለታል። ዛሬም  በሹክሹክታ መልክ የተሰራጨውን ወሬ ወደናንታ እንደወረደ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በኤች. አይ.ቪ በሽታ ህዝብን በመጨረስ እርዳታ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ምንጮች አረጋገጡ፡፡ ኤች. አይ.ቪን ለመከላከል ተብሎ ለኢትዮጵያ መንግስት ከምእራባውያን የሚሰጠውን እርዳት በመቆሙ አዲስ አበባ የሚገኙ ከጤና ጣቢያ እስከ ሆስፒታል በተለይም ዘውዲቱ ሆስፒታል ኤች አይቪ መመርመሪያ ኪት በማጣታቸው ኤች. አይ.ቪ ያለባቸው እናቶች ፖዘቲቭ የሆነ ህጻን እየወለዱ ይገኛሉ፡፡ እርዳታው የሚቆምበት ምክንያት ኢትዮጵያ ኤች. አይ.ቪን በመከላከሉ ረገድ የተሳካላት በመሆኑ እና ምንም ታማሚ ስለሌለ እርዳታ ሰጪ ሀገራት ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር በማዞራቸው እና በተለያዩ ጊዜ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ገንዘብ በባለስልጣናት በመዘረፉ እንዲሁም ሂሳባቸውን በወቅቱ ማወራረድ ባለመቻላቸው እንደሆን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው እርዳታ ለጸረ ኤች. አይ.ቪ መድሃኒት መግዣ ብቻ ሲሆን ይህንንም በአግባቡ ገንዘቡን ባለመጠቀማቸው ምእራባውያን ርዳታውን ለማቆም ቢፈልጉም ከሰብዓዊነት አንጻር ብለው እንደሆነ የሚረዱት ተብላል፡፡ ባለፉት ዓመታት በርካታ ረጂ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የአፈጻጸም ስምምነት ለመፈራረም ቢመጡም አንዳንድ ባለስልጣናት ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ አቃቂር እያወጡ ተቋማቱን በማጉላላት አንፈራረምም በማለታቸው ምክንያት ረጂ ተቋማቱ ፊታቸውን ወደ ሌላ ሀገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የሆኖ ሆኖ በኤች አይቪ ምክንያት የሚሞትና ስርጭቱ ቀንሷል በሚል ርዳታ ያጣው መንግስት የኤች አይቪ መመርመሪያ ኪቶችን በመደበቅ ለጤና ተቋማቱ ባለመስጠት ኤች. አይ.ቪ ሆን ተብሎ እንዲሰራጭ እና ትኩረት በማግኘት የኤች. አይ.ቪ ብር ለመብላት በሚል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት የኤች .አይ.ቪ መሳሪያዎች በጤና ተቋማቱ አይገኝም፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 7, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to አስደንጋጭ ዜና! ተጠንቀቁ! (ሹክሹክታ)

 1. Tuffaa bekele.

  April 7, 2014 at 11:59 AM

  Another very sad day for the poor Ethiopians who are ruled by those weyans who hate the people and the cantry.

 2. Goytom

  April 7, 2014 at 9:18 PM

  TPLF has been doing this for so long(killing Ethiopians),so what’s new! Ethiopians must stand unite.

 3. ትዝብት

  April 8, 2014 at 2:12 AM

  አዎ!! እኔም ይህን በተመለከተ ጭራቁና የባንዳው ልጅ በህይወት በነበረበት ወቅት እኔ ያለሁበት ሃገር የጤና ጥበቃ መ/ቤት የራሱን ክሊኒክ በመክፈት በመመርመርና መድሃኒቱን በነጻ ለመስጠት ታስቦ ልኡካኑ ከመለስ ጋር ተገናኛቶ የፕሮጀክቱን ዓላማ የልእኩ መሪ በአጭሩ ካስረዳ በሁዋላ: መለስ የሰጠው መልስ ግን ልኡኩን ያስደነገጠና ያስደመመ ነበር;;
  መለስ ያለው;-ይህ ህዝብ አንድ ብር ለኮንዶም ማውጣት አይችልም: ለምድሃንኒቱ ግን እስከ አሥር ሽህ ብር በየወሩ ያወጣል ብሎ ሲናገር: አብሮ ከልኡካኑ ጋር የነበርና አብሮ የሄደው በቁዋንቁዋው ማስታወሻ በመጻፍ የመለስ ፍላጎት ገንዝቡን እንድትሰጡት እንጅ ለዚህ ክሊኒክ እንዲከፈትና ህዝቡ እንዲረዳ አይፈልግም ብሎ ጽፎለት አንብቦ ሳይጨርስ: መለስም ንግግሩን በመቀጠል ይልቁን ገንዘቡን በእኛ በኩል ገቢ ይሁንና ለየሆስፒታል እናከፋፍል ሲላቸው: እናስብበታለን ብለው ተሰናብተው ወጡና በዚያው ቀሩ::
  ግን አሥር ሽህ ብር በየወሩ የሚያወጣው ማን እንደሆነ እያወቁ መጠየቅ ያልፈለጉት ምን ያህል ለህዝቡ ግድ እንደሌለው ግንዛቤአቸውን ስላጠናከረላቸው ነው::

  እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያስባት!!! ኣሜን!!!