አስተያየት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” ላይ – ፈቃደ ሸዋቀና

engana-abyotu.fwየሻምበል ፍቅረ ስላሴን ባለ 440 ገጽ መጽሐፍ ላነብ ስነሳ ጸሐፊው በሃያ ዓመታት የእስር ቤት ቆይታቸው በስልጣንና የሃላፊነት ዘመናቸው የነበሩትን ብዙ ክንዋኔዎች ፣ ውሳኔዎችና ተዋናዮችን አስመልክቶ የነበራቸውን እይታ እንደገና ለማጤንና ለማሰላሰል እድል አግኝተው የጻፉት ሊሆን ስለሚችል ሚዛናዊ የሆነ ዕውቀት፤ እንዲሁም የመንግስታቸውን የውስጥ ለውስጥ ሥራዎች ከሩቅ እናይ የነበርን ተራ ዜጎች ሳናውቃቸው የቀሩ ነግሮችን የምናገኝበት ይሆናል የሚል ጉጉት ነበረኝ። በተጨማሪም በመግቢያው ሊተርኩልን ቃል የገቡትን የደርግን የግዛት ዘመን ዋና ዋና ቁም ነገሮችና ክንዋኔዎች እንደወረደ አቅርበውልን አንባቢዎች የሁሉንም ነገር ፋይዳ የራሳችንን ሚዛን ተጠቅመን እንድንረዳው ይተውልናል ብዬ አስቤም ነበር። ይህ ከንቱ ምኞት መሆኑን ወደ ገጾቹ ውስጥ ርቄ ሳልሄድ ነው ያረጋገጥኩት። በሁሉም የደርግ የግዛት ዘመን ክንዋኔዎችና የፖለቲካ ተዋናዮች ላይ የራሳቸውን ዳኝነቶች አመለካክቶችና ግለ-አይታዎች (bias) ጨምረውበታል።

ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ከእስር በወጡ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜያቸውን ወስደው ይህን መጽሀፍ በመጻፋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። ወደፊትም ሌሎች መጽሐፎች እንደሚጽፉ ቃል ገብተዋል። የሚቀጥሉት ላይ በበለጠ የሃላፊነት ስሜት እንዲጽፉ ለማሰቢያ የሚረዳ ነገር ካስተያየቴ ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። እውነት በመናገርና በሀቅ በመመስከር ከሚገኘው ብዙ ጥቅም ውስጥ አንዱ ለተናጋሪው የህሊና ፈውስ የሚያስገኝ መሆኑ ነው። ለሻምበል ፍቅረስላሴና ለቤተሰባቸው መልካሙን ነገር ሁሉ እመኝላቸዋለሁ። መጽሀፋቸው ላይ በማቀርበው አስተያየት ላይ ግን ርህራሄ የለኝም። የምንሟገትበት ጉዳይና ታሪክ ከያንዳንዳችን ስብዕና በላይ ስለሆነ። Read full story in PDF: አስተያየት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” ላይ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 4, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to አስተያየት በሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ “እኛና አብዮቱ” ላይ – ፈቃደ ሸዋቀና

 1. Abebech

  March 4, 2014 at 8:25 PM

  You must be one of those writers who still think people will read you
  and believe your word. I have read the book and I find it fascinating
  and honest. Fikre Selasei WogDeres has done great service to the people
  and he is gonna write more so that pseudo-revolutionaries like you
  Will be kept in check. I am disappointed by your dishonesty.