አስሩ የጽልመት ቀናት-በኢትዮጵያ! በሰሎሞን ተሰማ ጂ

አስሩ የጽልመት ቀናት-በኢትዮጵያ!

(ከየካቲት 8/1929 – የካቲት 17/1929 ዓ.ም)

በሰሎሞን ተሰማ ጂ.      http://semnaworeq.blogspot.com

በመስከረም 1927 ዓ.ም የወጣው Detroit Times — (Sept. 22, 1935, p. 3) መጽሔት ከአንድ ታላቅ ሳይቲስትና የፈጠራ ባለሙያ ጋር የኢትዮጵያንና የጣሊያንን ወረራ አስመልክቶ ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር፡፡Nikola Tesla Tells How He’d Defend Ethiopia Against Italian Invasion(www.tesla.hu/tesla/articles/19350922.doc) በቃለ-ምልልሱም ላይ ጋዜጠኛው ዶ/ር ኒኮላ ቴስላን እንዲህ ብሎ ጠየቀው፤ “ካለፈው የካቲት 1935 (እ.አ.አ) ጀምሮ ኢጣሊያን ኢትዮጵያን በኃይል ወራለች፡፡ አንተ ንጉሠ ነገሥቱን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ብትሆን ምን ታደርግ ነበር?” መላሹ ዶ/ር ኒኮላ ቴስላም ትንሽ ጊዜ ትክዝ ካለ በኋላ፤ “እኔ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ብሆን ኖሮ፣ በከተሞች አካባቢ ያለውን ሕዝብ በመላ ወደገጠርና ወደዱር ገደሉ እንዲሄዱ አደርገዋለሁ፡፡ ሕዝቡ ከከተሞች ወጥቶ ወደገጠራማ ቦታዎች እንዲያፈገፍግ አዘዋለሁ፡፡” ጋዜጠኛው ጣልቃ ገባ፤ “ለምን?” አለው፡፡ ቴስላም ቀጠለ፤ “የአሁኗ ኢጣሊያ መሪዎች ክፉኛ ማስተዋል የጎደላቸው ጣሊያኖች ናቸው፡፡ የፋሺዝም ርዕዮት-ዓለም እውር አድርጓቸዋል፡፡ ስለሆነም ከፍተኛ ጭፍጨፋ በከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እንደሚፈጽሙ ይታየኛል፡፡ ስለሆነም ሕዝቡ ከከተሞች ወጥቶ ወደ ገጠራማ አካባቢዎች ወፍለስ አለበት፡፡” ጋዜጠኛው ግራ ገባው፤ ጥያቄዎቹን አዥጎደጎደ፤ “ኢጣሊያ ትልቅ አገርና በሥልጣኔም ቢሆን ከኢትዮጵያ የተሻለች ሆና ሳለ እንዴት እንደዚህ ያለ የአረመኔዎች ግፍ ልትፈጽም ትችላለች ብለህ ታስባለህ?”

Read more from Semnawork
Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 25, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.