አርከበ በትግራይ ተወላጆች ላይ የተጫወተው ቁማር በላስቬጋስ

ኤፕሪል 9ና 10 በየደረሰበት የተዋከበው የአርከበ ቡድን የጨዋታቸው ማሳረጊያ ወደ ሆነው ላስቬጋስ ሲመጣ በሌሎች ከተሞች ከገጠመው ፈተና ተምሮ በቁማርዋ ከተማ ውጤታማ ለመሆን መክሮና ዘይዶ መዘጋጀቱ የማይቀር ነበር። ቬጋስም ቢሆን እንዲሁ።

ታዲያ አስገራሚው የአርከበ ቡድን ዘየድኩ ብሎ የተጠቀመበት ስልት ለተራበው ውጤት ሳይሆን በቁማርዋ ከተማ ሊጫወት ላሰበው ቁማር የትግራይ ተወላጆችን መድቦ ያስበላበት ብሎም ራሱንና ተወላጆቹን እርቃናቸውን አጋልጦ ከሜዳ ያወጣበት ሆኖ ተጠናቀቁ ነበር። የነአርከበ ስልት በእለቱ ከሚገኘው ጭብጨባ ያላለፈ ነገርግን በዚህች ከተማ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በትግራይ ተወላጆችና በቀሪው ኢትዮጵያዊ መካከል በቀላሉ ሊደፈን የማይቻል አደገኛ ገደል የማሰበት በመሆኑ ኪሳራው የከፋ ሆኖ አላፏል።

ያለመታደል ሆኖ አርከበና ቡድኑን ከአየር ማረፊያው ጀምሮ አጅበው የቁማር አይነት ሲያሰለጥኑዋቸውና ሲያስመነዝሩዋቸው ያደሩት ግለሰቦች ለመለስ ኢንቨስትመንትና ትራንስፎርሜሽን የሚያውቁትም ሆነ ግድ ያላቸው ሳይሆኑ ለርካሽ ፍላጎታቸው ያውም ከቁማር የተራረፈ ሳንቲም እናገኛለን ከሚል.. ግፋቢል 300 ካሬ ሜትር ቦታ እናገኛለን በሚል ተስፋ የተሞሉ ራስ ወዳዶች በመሆናቸው አርከበንና ቡድኑን እንደራሳቸው ቆሻሻ ጌም አጫውተው ቆሻሻ ውጤት እንዲታቀፍ አድርገውታል። ምስኪን አርከበ…..ወይ ያለማወቅ…..

እስቲ የነአርከበ የቬጋስ ጨዋታ በጥቂቱ እንቃኝ።
እደሌሎቹ ከተሞች ሁሉ የከተማችን ሆድአደር አስተባባሪ ተብዬዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ መጋበዙን በአደባባይ እየለፈፉ በጓዳ ግን ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በስብሰባው ከተገኛችሁ በትግሬነታችሁ መሬት ታገኛላችሁ በማለት ሲቀሰቅሱ መቆየታቸውን ወደ አዳራሽ ከመጡ ጥቂት ከማይባሉ ሰዎች ማረጋገጥ ተችሏል።ሌሎች ደግሞ በትግሬነታቸው ብቻ የተገኙ እንጂ ስለጉዳዩ አንዳችም እውቀት እንደሌላቸው ሲናገሩ መሰማቱ ደግሞ በዘር ማንነታቸው ብቻ እንዲገኙ ሲነገራቸው መክረሙንም ያረጋግጣል።

በአጭሩ እንዲህ ባለ ሁኔታ በአደባባይና በጓዳ ጥሪና ቅስቀሳ ሲደረግለት የሰነበተው የነአርከበ ጨዋታ በተባለለት እለት ኤፕሪል 13 በጎልድ ኮስት ሆቴል አዳራሽ ተከፈተ።በትግሬነቱም የተጠራው በኢትዮጵያዊነቱ የሰማው ሁሉም ከስፍራው ተገኘ።በተለይ በዘር ማንነቱ የመጣው ላለመታየት የሚያደርገው ጥረት < ቀድሞም ገበያ ባልወጣሽ…….> የሚያሰኝ ነበር።

በዚህ በፖለቲካ አመለካከት ሳይሆን በዘር ማንነት ጥሪ በተደረገለት ስብሰባ ላይ ቀድሞ ከስፍራው የተገኘው በኢትዮጵያዊነቱ የመጣው ሲሆን በዝቶ መታየቱ ድንጋጤ ፈጥሮ ሁሉን አሯሯጠ…የአዳራሹ በር ይከፈታል ከተባለለት ሰአት በሀያ አምስት ደቂቃም እንዲዘገይ አደረገ።ሌላው አርከበ ሽንት ቤት ሄዶ በገጠመው”ዘራፍ!” ከገባበት ድንጋጤ ወጥቶ ነብሱ እስኪረጋጋ የወሰደው ጊዜ ቀላል አልነበረም። አርከበ ልብሱን ሳያበላሽ ተረጋግቶና በዘሩ ተጠርቶ ግን በየእስላት ማሽኑ ስር ተደብቆ የነበረው ሰው ወጥቶ ወደ አዳራሽ እንዲገባ ከተደረገና ከፊኒክስ ከሳንዲያጎ ከሎሳንጀለስና ከዴንቨር ያመጡዋቸው ቦታ ከያዙ በሁዋላ ሌላው እንዲገባ በር ከፈቱ።አርከበ ለቁማር ጨዋታው ባዘጋጃቸው የትግራይ ተወላጆች አዳራሹ ሞልቶ ሲመለከት ይበልጥ ተረጋጋ። አብላጫ ቁጥር ያለው የመሰለው የኢትዮጵያውያን ቁጥር ከአምስት እስቴት በተሰበሰበው የአንድ ብሄር ሰው ተዋጠ።

ይህ ሁሉ ያላረካው አርከበ ሊቋቋሙኝ ይችላሉ ያላቸውን በፖሊስ ሀይል እንዳይገቡ አስደረገ።ባጠቃላይ እርሱና ቡችሎቹ ባላቸው አቅም ሁሉ አዳራሹ በትግራዮች እንዲሞላ አደረጉ።ከቡችሎቻቸው አይን አምልጠው ወደ አዳራሽ ከገቡትም አብዛኛው በፖሊስና ሴኩሪቲ ታግዘው ለቅመው እንዲወጡም አደረጉ።ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አርከበ የጓጓለትን በጭብጨባ አስጀምሮ በጭብጨባ መጨረስ ማስገኘት ሳይቻለው ቀርቷል።ምስኪን አርከበ……

አዎ… እንዲህ ከመሰለው የማጥራት እርምጃ አምልጠው በአዳራሽ የቆዩት ጥቂቶቹ በግፍ የጨፈጨፏቸው ንፁሀንን ድምፅ እያንገፈገፋቸው እንዲሰሙት አድረገዋል።ወያኔም የተራ ነብሰ-ገዳዮችና ዘራፊዎች ስብስብ መሆኑን ……ወያኔ ለልማት ሳይሆን ለጥፋት የተነሳ… ሀገሪቷንም በዘር በቋቋንቋና በሀይማኖት ከፋፍሎ ለማጥፋት የተነሳ …. ህዝቧን ለአስከፊ የኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት የዳረገ….. የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት ከዜጎችዋ ነጥቆ ለባእዳን እየቸበቸበ የሚገኝ ቡድን መሆኑን….. ወዘተ ተናግረው ከእንግዲህ ግን ወያኔ በቃህ መባል እንዳለበት እየተናገሩ ወጥተዋል። እስከ መጨረሻው ሰአት ድረስም በየጣልቃው የሚፈሩትን መራራ እውነት እንደ ተጎነጩ ስብሰባው ተጠናቋል።

በአጠቃላይ በሌሎች 13 የአሜሪካና ካናዳ ከተሞች ውርደትን የተከናነበው የአርከበ ቡድን የቀረች ትንፋሹን አሰባስቦ ለመጨረሻ ጊዜ በቁማርዋ ከተማ ላስቬጋስ ላይ የትግራይ ተወላጎችን መድቦ የተጫወተው የፖለቲካ ቁማር ውጤቱ ከቀድሞው የከፋ መሆኑን በአዳራሽ ከተገኙ የትግራይ ተወላጆች አንደበት < የተዋረድነው ዛሬ ነው>የሚል ቃል መሰማቱ ያረጋግጣል። መጨረሽው ይህ ቢሆንም ለአርከበ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ የተመደቡት የትግራይ ተወላጆች በቀሪው ኢትዮጵያዊ ላይ ያላቸውን ንቀትና ጥላቻን አቅማቸው በሚፈቅደው መጠን ሁሉ ያሳዩበት ቀን እንደ ነበርም መዘንጋት የለበትም።ወያኔ እንዳሻው ቢገድል… ቢያስር…ቢያሳድድ ቢያፈናቅል….. በስራ አጥነትና ኑሮ ውድነት ቢጠብሰው……. ለነርሱ በትግሬነታቸው መሬት ይሰጣቸው እንጂ ግድ እንደ ሌላቸው በገሃድ ያሳዩበት እለት መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ያውም በሰለጠነው አለም እየተኖረ።

ብቻ ወያኔ ላለፉት 20 አመታት ይህ ቀረሽ የማይባል ወንጀል ሲፈፅም በግልፅ እየታወቀ..የፈፀመውም ወንጀል የሚቀሰቀሰው ህዝባዊ ቁጣ እንዳይበላው ሰግቶ ላዘጋጀው የማደናገሪያ ቁማር በትግራይ ተወላጅነት ብቻ አይኔን ግንባር ያድርገው ማለቱና….አልፎ ተርፎ በቀረው ኢትዮጵያዊ ፊት < ወያኔ ጀግና ነው….ተዋግቶ ያገኘው ነውና ወንድ ከሆንከ ተዋጋ>የመሳሰሉ ፍፁም ዘረኛ ፉከራዎች በእለቱ በግልፅ መሰማታቸውን ተከትሎ መታየት የጀመረው ትልቅ የልዩነት ገደል ማንን ሊጠቅም ማንንስ ሊጎዳ እንደ ሚችል መገመት የፈጣሪዎቹ ሲሆን መቼ እንዴትና ምንስ ቢደረግ ይህ አደገኛ የልዩነት ገደል ሊደፈን እንደ ሚችልም የማሰቡ ሀላፊነት የፈጣሪዎቹ መሆኑ ታውቆ ከወዲሁ ቢታሰብበት ማለት።

ሳይቃጠል በቅጠል!!!!!!

በአርከበ ንግግርና የአዳራሹ ድራማ በሚቀጥለው

አንደበት ነኝ ከቬጋስ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on April 20, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.