አርቲስት ደበበ እሸቱ ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ተጠየቀበት

በ ”ሽብር” ተጠርጥሮ ማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኘው አርቲስት ደበበ እሸቱ ጥቅምት
24 ቀን 2004 ዓ.ም አራዳ ምድብ ችሎት ተቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል ፡፡
አርቲስት ደበበ በቀጠሮው ቀን ከማዕከላዊ እስር ቤት ወደ ችሎት ቀርቧል፡፡
ችሎቱን ለመከታተልም የተጠርጣሪው ቤተሰብም ሆነ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ የተከለከለ
ሲሆን ተጨማሪ የ28 ቀን ቀነ ቀጠሮ ተጠይቆበታል ሲሉ ጠበቃው በተለይም ለዝግጅት
ክፍላችን ገልፀዋል፡፡
ተጠርጣሪውም ጥቅምት 24 ቀን 2004 ዓ.ም ችሎት እስከቀረቡበት ጊዜ
ድረስ በማዕከለዊ እስር ቤት ከጠበቃቸው ጋር እንዲገናኙ ባለመፈቀዱ ጠበቃው ችሎት
ፊት ከደንበኛቸው ጋር እንዲመክሩ በጠየቁት መሠረት ተፈቅዶላቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን
ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ክቡር ፍ/ቤቱ ተጠርጣሪው ከጠበቃቸው ጋር የመገናኘት ሕገ
መራግሥታዊ መብታቸው መሆኑንና ሊከለከሉ እንደማይገባ ለመርማሪው ፖሊስ
በማሳሰባቸው ጠበቃቸውም ተግባራዊ መሆኑን ለማረጋገጥ ዛሬ ወይም ነገ ማዕከላዊ
እስር ቤት ሄደው ደንበኛቸው አርቲስት ደበበ እሸቱን ለማነጋገር መወሰናቸውን በተለይም
ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ – ፍኖተ ነጻነት

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 9, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.