አርቲስት ደበበ እሸቱና ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጐስ ተፈቱ

ታዋቂ አርቲስት ደበበ እሸቱና ወጣት ጋዜጠኛ ስለሺ ሀገስ ከታሰሩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ዓርብና ቅዳሜ መለቀቃቸውን ከቤተሰቦቻቸው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል፡፡ እንደ ዜና ምንጮቻችን መረጃ አርቲስት ደበበ እሸቱ ዓርብ ዕለት አመሻሽ ላይ ተለቆ ከቤተሰቡ ጋር ሲቀላቀል፤ጋዜጠኛ ለስሺ ሀጎስ ቅደሜ ጠዋት ተለቋል፡፡”ብለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎች በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ከቤተሰብና ከሥራ ጓደኞቻቸው ጋር ሳይገናኙ ከ3 ወር በላይ የታሠሩ ሲሆን በጊዜ ቀጠሮ በሚቀርቡበት ፍ/ቤት “ፖሊስ በቂ መረጃ አለኝ፣ምርመራዬን አላጠናቀቅኩም…” በማለት 3 ጊዜ 28 ቀነ ቀጠሮ እየጠየቀ ማስፈቀዱ ይታወቃል፡፡ አርቲስት ደበበ እሸቱ በታሰረበት ወቅት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የመንግሥት ሚዲያዎች የአርቲስቱን ወንጀለኝነት ለማሳመን ዶክመንተሪ ፊልም በመስራትና ዜናዎችን ለሕብረተሰቡ ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡

በዚህ አጋጣሚ አርቲስት ደበበ እሸቱና ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ በመፈታታቸው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ የተሰማውን ደስታ ይገልጻል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on November 15, 2011. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.