አርቲስት አበበች ደራራ አረፈች

ለረጂም ዓመታት በራስ ቴአትር በድምጻዊነት ስትሰራና ለአድማጮችዋ ዜማዎችን ስታቀርብ ኖራ በስተመጨረሻው ወደ እስራኤል ሀገር ከትማ ስትኖረ የነበረችው ታዋቂዋ ድምጸ መልካሟ አበበች ደራራ ዛሬ ሜይ 16 ቀን ባደረባት ህመም ሳቢያ ሕይወቷ አልፏል፡፡

Abebech Derara passed away

Abebech Derara passed away

አበበች ደራራ በሕመም ተይዛ ለበርካታ ወቅት በአልጋ ላይ ከመቆየቷም ባሻገር ጨርሶ ከሰዎች ጋር ግንኙነት አቋርጣ በሽታዋን ለብቻዋ ስታስታምም እንደነበረች በቅርብ የሚያውቋት ይናገራሉ፡፡

የአበበች ደራራ አስከሬን በኖረችበት የቴል አቪቭ ከተማ በዛሬው እለት ከቀኑ 3:00PM ላይ ወደ ቀብር በወዳጅ ዘመዶች ታጅቦ በመሄድ ሥርአተ ቀብርዋም ይፈጸማል፡፡

የአበበች ደራራ ወላጅ አባት፤ ከአመታት በፊት በኦህዴድ/ኢህአዴግ ታጣቂዎች ከቤት ተወስደው በግፍ መገደላቸው የሚታወስ ነው።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 16, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

3 Responses to አርቲስት አበበች ደራራ አረፈች

 1. Lena

  May 16, 2013 at 11:20 AM

  RIP

 2. ፊትሱም

  May 19, 2013 at 8:59 AM

  ረስት ኢን ፐአቸ

 3. ፊትሱም

  May 19, 2013 at 9:00 AM

  ረስት ኢን ፐአቸ አበበችህ