አርቲስት ታማኝ በየነ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገለፀ

[ኢ.ኤም.ኤፍ፡] አትላንታ ላይ በተደረገው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ከተደረገ በኋላ፤ አርቲስት ታማኝ በየነ በድንገተኛ ሁኔታ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ የሚታወስ ነው። የዲካብ ሜዲካል ሆስፒታል የላቦራቶሪ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ፤  ቆይታው ም ወቅት በውሃ ሽንት ውስጥ በተገኘ አነስተኛ ደም ምክንያት፤ የአትላንታ ሃኪሞች “ምናልባትየበኩላሊት ጠጠር ሊሆን ይችላል። ህክምናውንም እዚሁ በመቆየት መከታተል ትችላለህ።” መባሉ ይታወሳል። ይህ ዜና በኢ.ኤም.ኤፍ ድረ ገጽ ከታተመ በኋላ፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በድረ ገጻችን ላይ፤ “እግዚአብሄር ይማርህ!” ከሚለው መልዕክታቸው ጀምሮ፤ በስልክ እና በአካል ያገኙን ሰዎች በተደጋጋሚ የሚያነሱት፤ “አሁን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል?” የሚለውን ጥያቄ ነበር። በቀጣይ የሆነውን ለማወቅ ከአርቲስት ታማኝ በየነ ጋር አጭር የስልክ ልውውጥ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

አርቲስት ታማኝ በየነ ቤተሰቡ ወደሚገኝበት የቨርጂንያ ክፍለ ግዛት በመሄድ ህክምናውን መቀጠል እንደሚፈልግ ገልጾ እሁድ እለት አትላንታን ለቅቆ መሄዱ ይታወሳል። አርቲስቱ በቅድሚያ በግል ሃኪሙ አማካኝነት ምርመራ ያደረገ ሲሆን፤ ሃኪሙም ቀደም ሲል በአትላንታ የተደረገውን ምርመራ መሰረት በማድረግ ተጨማሪ የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲያደርግ አድርጓል። ሆኖም የምርመራ በድጋሚ የተደረገው የምርመራ ውጤት ለሃኪሞቹም ሆነ ለአርቲስቱ የሚገርም ነበር። የላቦራቶሪ ውጤቱ እንደሚያሳየው፤ የደም ሆነ የውሃ ሽንት ምርመራ ውጤቱ ከምንም አይነት ብክለት ነጻ መሆኑን የሚያሳይ ሆነ። በሁኔታው የተገረሙት ሃኪሞች በድጋሚ ምርመራ እንዲያደርግ ወሰኑ። አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ውጤቱ ኔጌቲቭ ወይም ጤነኛ መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ ተገኘ።

ይህ መልካም ዜና ነው። አርቲስት ታማኝ በየነ በአትላንታ ቆይታው ወቅት ወደ ሆስፒታል ለመሄድ የተገደደው በአንድ ጎኑ በኩል በደረሰበት የማያቋርጥ ስቃይ ምክንያት ነበር። አሁንም የላቦራቶሪ ውጤቱ መልካም ቢሆንም፤ ቀደም ሲል የተፈጠረው ህመም ከምን ተነስቶ እንደተፈጠረ ለማወቅ ተጨማሪ ህክምና ወይም የካትስካን ምርመራ እንደሚያደርግ  በተለይ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጾልናል። በአጠቃላይ አሁን ስላለው የጤንነቱ ሁኔታ ሲያስረዳ፤ “በጣም በጥሩ ጤንነት ላይ እገኛለሁ።” ካለ በኋላ፤ “በዚህ አጋጣሚ በስልክም ሆነ በአካል አግኝተው፤ ስለጤንነቴ ተጨንቀው ለጠየቁኝ እና በጸሎታቸው ያሰቡኝን ሁሉ ከልብ ለማመስገን እወዳለሁ።” ብሏል።

“ለሚደረግልን መልካም ነገር ሰውን ማመስገን መልካም ነገር ነው” ያለን አርቲስት ታማኝ ምስጋናውን በመቀጠል፤ “የግል ሃኪሜ ስለሚከፈለውም አገልግሎቱን ሰጥቶኛል። ነገር ግን ነበር። ከአትላንታ ጀምሮ የጤንነቴን ሁኔታ የተከታተሉት ዶ/ር ኤፍሬም ከዚያ ዜናውን እንደሰሙ ደግሞ በዲሲ የሜትሮ ላቭ ክሊንክ ባለቤት የሆኑት አቶ ካሳሁን ተፈራ፣ እዚያው የምትሰራው የላብራቶሪ ቴክኒሺያን ወ/ት ኤልሳቤት፤ እንዲሁም ዶ/ር ደረጀ ለገሰ እና  ዶ/ር ኃይለየሱስ ኬርቤሎ ከመስመራቸው ወጥተው ላደረጉልኝ ትብብር በውነት ላመሰግናቸው እወዳለሁ።” በማለት ምስጋናውን አስተላልፏል።

በኢ.ኤም.ኤፍ በኩል… አርቲስት ታማኝ በየነ  መታመም ተጨንቀው ከአሜሪካ፣ ከአውስትራሊያ እና ከአውሮፓ የደወሉትን በሙሉ… በጸሎታቸው ያሰቡትን ሁሉ፤ “ጤንነቱ በደህና ሁኔታ ላይ ይገኛል!” ከሚለው አጭር መልዕክታችን በተጨማሪ፤ በሚቀጥለው ሳምንት በዋሺንግተን ዲሲ፣ በዳላስ እና በልዩ ልዩ ከተሞች  በተከታታይ የሚያደርጋቸው ዝግጅቶችም የማይስተጓጎሉ መሆናቸውን በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 11, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.