አምቦ በረብሻ እና በእሳት ተቃጠለች

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በትላልቅ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ከጀመሩ አንድ ሳምንት አለፋቸው። የተቃውሞው ምክንያት… የአዲስ አበባ አጎራባች በሆኑት የኦሮሚያ ዞኖች ሊሰራ በታቀደው መሰረተ ልማት ነው። ለነገሩ መሰረተ ልማቱ አዲስ አበባ እና አጎራባች የኦሮሞ ከተሞችን (ለምሳሌ ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ኮተቤ) የመሳሰሉት ከተሞችን ከአዲስ አበባ መሰረተ ልማት ጋር በትራንስፖርት እና በንግድ የማገናኘት እቅድ ነድፏል።
ይህ እቅድ ግን ገና ከመጀመሪያው በኦሮሚያ ባለስልጣናት ጭምር አንዳንድ ተቃውሞ ሲቀርብበት ነበር። ውስጥ ውስጡን ደግሞ፤ የአዲስ አበባ መስፋት እና ከሌሎች አጎራባቾች ጋር መዋደድ ወደ ውህደት እንዳይሄድ የሰጉ ሰዎች ነበሩ። እነዚህ ሰዎች የአዲስ አበባን መስፋፋት… የአማርኛ ተናጋሪዎች ባህል እና አስተዳደር መስፋፋት በመሆኑ መሰረተ ሃሳቡን ጭምር አጥብቀው ይቃወሙታል።

በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ

በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ

ይህ ተቃውሞ አይኑን አፍጥጦ እና አፍ አውጥቶ አሁን ይውጣ እንጂ፤ ከሁለት ሳምንታት በፊት በራሳቸው የኦሮሚያ ባለስልጣናት መካከል መከፋፈልን ፈጥሮ የነበረ ጉዳይ ነው። በዚያኑ ሰሞን ደግሞ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች እየታደኑ ሲታሰሩ ነበር። የዚህ የእስር እና አፈና   ዜና በይፋ ባይወጣም፤ ህዝቡ ግን ውስጥ ውስጡን ሲያዝን እና ሲያለቅስበት የነበረ ጉዳይ ነው። አሁን በኦሮሚያ ክልሎች ተማሪዎች የሚያሰሙት ተቃውሞ ዋናው ምክንያት “የአዲስ አበባ መስፋፋት…” ይባል እንጂ በውስጡ ብዙ ብሶት እና ጥያቄዎችን ያዘለ ይመስላል። ለዚህም ነው በድሬዳዋ፣ በሃረር፣ በባሌ፣ በጅማ፣ በነቀምት፣ በአምቦ እና ሌሎች ከተሞች የነበረው ተቃውሞ የምኒልክን ስም ጭምር በመጥራት ተቃውሞው ይቀርብ የነበረው። በሃረሩ አለማያ ዩኒቨርስቲ ሲያሰሙ ከነበሩት የተቃውሞ መፈክሮች መካከል ቴዲ አፍሮን ያወገዙበት አጋጣሚም አንዱ ነው።

አምቦ ላይ በተደረገው የተማሪዎች ሰልፍ ደግሞ አጼ ምኒልክ ከሞቱ ከመቶ ምናንም አመታት በኋላ፤ የሳቸውን ስም እየጠሩ አውግዘዋቸዋል። አጼ ምኒልክን መራገም ወይም የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ማውገዝ ውሃ የማይቋጥር ተቃውሞ ቢሆንም፤ የተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፎች ግን ከአዲስ አበባ መስፋፋት ውጪ የራሳቸው ብሶት… ብሶቱን ለማባባስ ደግሞ አጼ ምኒልክ እና ሌላውን ኢትዮጵያዊ (ቴዲ አፍሮን ጨምሮ) ማውገዙ እና ማግለሉ ትክክል አይመስልም።
ambo-university
አሁን በሀረር፣ በአምቦ እና በሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች የሚደረጉት ሰላማዊ ተቃውሞች ወደ ጸብ እና የርስ በርስ ግጭት እንዳይቀየሩም ያሰጋል። ለምሳሌ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ሲያደርጉ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በተከፈተው የተኩስ እሩምታ “ከሰላሳ በላይ ተማሪዎች ተገደሉ”  ከበኋላ፤ መመሪያውን ሲያስፈጽም የነበረው ኦህዴድ ግን “የሟቾቹ ቁጥር 6 ብቻ ነው” በማለት ይከራከራል። አላማው ምንም ይሁን ምን ህዝብ ሃሳቡን በነጻነት በመግለጹ ሊገደል እንደማይገባው ሁሉም የሚስማማበት ጉዳይ ይመስላል። ሆኖም የተቃውሞውን ሰልፍ በሃይል ለመበተን የሚሞክሩት የክልሉ እና የፌዴራሉ ታጣቂዎች አምቦ ላይ ሌላም ስራ ተጨምሮላቸዋል። ከተቀጣጠለው ተቃውሞ በተጨማሪ  የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው። አሁን ማምሻውን እንደሰማነው ከሆነ፤ በባንክ እና ሌሎች ህንጻዎች ላይ ቃጠሎ ደርሷል – ተቃውሞውም እንደቀጠለ ነው!!

የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም በባሌ ሮቢ በትናንትናው እለት በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፖሊሶች በተከፈተ ተኩስ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ምስል (ምንጭ፡ በኢትዮ ትዩብ)

የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን በመቃወም በባሌ ሮቢ በትናንትናው እለት በተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በፖሊሶች በተከፈተ ተኩስ የደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ምስል (ምንጭ፡ በኢትዮ ትዩብ)

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 1, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

One Response to አምቦ በረብሻ እና በእሳት ተቃጠለች

  1. AYANA NEGAWO

    May 2, 2014 at 1:02 PM

    Gaddaan naaf hin ba’u, jecha jechaan jijjiirunis hiika naaf hin fidu. Waadamen hafaakoofi irraan fayyaako walaalus deemsa eegaleera. Mutaawa borii mucuruksee darbaa kan jiru kun?… Wayyoo sabichi erga wal irratti callisee Waaqayyo atimmoo maalumaaf calliftaa? Foon Obbolootaa nyaadheen, dhiiga isaanii dhugee maal jedheen kadhadha? Enyuun enyutti akka iyyatanan wallaalee, gubataa marrummaanko argika. Fincaan ittilleerraa ta’uutu Haddaggee keessa nu qabachiise. Waliin taane maxxannee ofittii cirra jennaan ammayyu Gingilchaan akka malee hulluuqee hulluuqsu bare nu waliin hiriiree. Gaaffin afaanii qawween yammuu deebi’a jiru, Oromoon Oromoo yammuu dhidhima galchu ilaaluuf erga goote, an dhaloota abaaramaadha. Saba gaddaan, ilmaan Yeeyyin nyaatameema hafamoo? Kaleessen galmeeyyu hin qabne; Walii galee takkaama yoo ol ka’e Afrikaa rommisiisu haraamuun kan gootuu fi bakka jirtu hin beekne soqolattee garmaamtee irratti akkas jeekkartu maafan rafa?