አሜሪካ የተደበቀው ወንጀለኛ – ከኢየሩሳሌም አርአያ

የህወሃት አባል ነው ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ስልጣን እስከተቆናጠጠበት ጊዜ ድረስ ያለው የጀርባ ታሪክ በንጹሃን ደም የተጨማለቀ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህ ግለሰብ ተስፋዬ መረሳ ይባላል። ህወሃት ጫካ በነበረበት ጊዜ ተራው ታጋይ ከሴት ጋር የፍቅርም ሆነ የግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ እንደማይፈቀድለት አስገራሚው የፓርቲው ህግ ይደነግጋል። ይህ ህግ እስከ 1981 አ.ም የቆየ ሲሆን የበላይ አመራሩ ግን የፈለገውን የማድረግ መብት ነበረው። ፆታዊ ግንኙነት ሲያደርጉ የተገኙ ተራ ታጋዮች ይፈፀምባቸው የነበረው ቅጣት በጥይት ተደብድቦ መገደል ነበር። በሺህ የሚቆጠሩ የፓርቲው ተራ አባላት የዚህ ቅጣት ሰለባ ሆነዋል።

እነዚህ ታጋዮች እንዲረሸኑ ሲወሰን ለመግደል ይጣደፉ ከነበሩት እና በርካታው የፓርቲ አባላት ከሚያስታዉሷቸው ገዳዮች አንዱ እና ቀንደኛው ተስፋዬ መረሳ ሲሆን ፣ ከእርሱ በተጨማሪ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ፣ ወ/ስላሴ ፣ሃይሉ (ሳንቲም) … በጭካኔ የግድያ ተግባራቸው ይጠቀሳሉ። ፊደል ያልቆጠሩት እነዚህ ወንጀለኞች የገዛ የትግል ጓዶቻቸውን ለመረሸን እጅ በማውጣት “እኔ… እኔ” እየተባባሉ ያሳዩ የነበረው ሰይጣናዊ ፉክክር እና ጥድፊያ ብዙ የፓርቲው አባላት አሁን ድረስ ያስታውሱታል።

Read full story in PDF

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on January 6, 2013. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.