አሜሪካ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጎን ትቆማለች? ከፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጋር ከወገነ፤ አሜሪካስ ለምን አትወግንም?

ፕሬዜዳንት ኦባማ አክራ፤ ጋናን በ2009 ሲጎበኙ ሁለት አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክቶችን አስተላልፈው ነበር፡፡ ‹‹ታሪክ ከጀግኖች አፍሪካውያን ጋር ወግኗል›› ሲሉ: ለአፍሪካ መሪዎችና ገዢዎች ደግሞ ጠበቅ ያለ መልክት ኣስተላፈው ነበር፡፡

………እንዳትሳሳቱ፡ ታሪክ ወገናዊነቱ ከጀግኖቹ አፍሪካውያን ጋር እንጂ በሥላጣን ላይ እራሳቸውን እንዳነገሱ ለማቆየት መፈንቅለ መንግሥት ከሚያካሂዱ ጋር አለያም ሕገ መንግሥታቸውን እንዳሻቸው ከሚለዋውጡት ጋር አይደለም፡፡ አፍሪካ የሚያስፈልጓት ጡንቻቸው የፈረጠሙ መሪዎች ሳይሆን የዳበሩ ተቋሞች እንጂ … የሕዝቦቻቸውን ፈቃድ ከማያከብሩት እጅጉን በበለጠ ሕዝባቸውን የሚያከብሩ መንግሥታት የከፍተኛ ሃብታም፤ በጣም የተረጋጉ እና የበለጠ የተዋጣላቸው ይሆናሉ… የልማት መሰረቱ መልካም አስተዳደር ነው፡፡ በበርካታ ቦታዎች እጅጉን ለረዘመ ብዙ ጊዜ ጎድሎ የነበረው ቅመም ይህ ነው፡፡ ይህ ነው የአፍሪካን እምቅ ችሎታ ሊያወጣው የሚችለው፡፡ ይህም ሃላፊነት በአፍሪካውያን ብቻ ነው ግቡን ሊመታ የሚችለው፡:

ለአፍሪካውያን ህዝቦች የላኩት መልእክት አነሳሽ ተስፋ ሰጪ፤አደፋፋሪ ነበር፡፡

Brave Africans Amharic Translation

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on December 18, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.