አሜሪካውያን ባለስልጣኖችን ያጃጃለ አለማቀፍ አራዳ፤በብርሃኑ አስረስ መጽሐፍ መነሻነት (ክፍሉ ሁሴን)

መግቢያ
ራሱን ካልናቀ እና ጣል ጣል ካላደረገ በቀር ማንኛውም ጎልማሳ የተካበተ፣ሊወሳ እና በታሪክ ሊዘከር የሚችል የሕይወት ልምድ አለው።አንዳንዶች እንዲያውም የራሳቸውን ግለ ሕይወት ብቻ ሳይሆን ጠቅላላ የአንድን ማህበረሰብ ታሪክ በእጅጉ ሊመለከት ከሚችል ሁነት ጋር ባጋጣሚ ይገናኙና የታሪክ ሁነቱ አካል ወይም ማዕከል እስከመሆን ይደርሳሉ።የሚያሳዝነው በኛይቱ አገር ይህንን አውቀን ማስታወሻ በመያዝ ለሚቀጥለው ትውልድ ትምህርት እንዲሆን ትውስታችንን በጽሁፍ የምናበረክት እጅግ ጥቂቶች ነን።ለዚህም ነው በቅርቡ ያነበብኩትን የ “ማን ይናገር የነበረ–የታኅሣሡ ግርግር እና መዘዙ”ን መጽሐፍ ደራሲ አቶ ብርሃኑ አስረስን ለማድነቅ፤ከማድነቅም አልፎ በመጽሐፋቸው የተነሱት አንዳንድ የታሪክ ሁነቶች እኔንም በትውስታ ብልጭታ (flashback )ወደኋላ ስለወሰዱኝ ይህንኑ በማነሳሳት ሌሎች ልክ እንደ አቶ ብርሃኑ አስረስ የተካበተ ልምድ ያላቸው እንዲሁም አገራችንን በሚመለከት የታሪክ ሁነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተሳተፉ እንዲጽፉ ለመጎንተልም ጭምር ነው።እርግጥ ባሁኑ ወቅት የግለ ሕይወት ታሪክ (Autobiography )መጽሐፍ ትንሳኤ የሆነ እስኪመስል ድረስ ታዋቂም፤ እጅግም ታዋቂ ያልሆኑ ግን ባንድ የታሪክ ክስተት የተሳተፉ ሰዎች የጻፏቸው መጽሐፍት በብዛት እየታተሙልን በማንበብ ላይ እንገኛለን።በዚህ አይነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አአዩ) ፕሬስ ከታተሙት መጽሓፍት ይህን እንድጭር የጎነተለኝ የአቶ ብርሃኑ መጽሐፍ አንዱ ነውና ዩኒቨርሲቲውንም በዚህ አጋጣሚ ይበል ይበል ማለት ተገቢ ይመስለኛል። Read story in PDF: አሜሪካውያን ባለስልጣኖችን ያጃጃለ አለማቀፍ አራዳ…

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on February 9, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.