አማረ አረጋዊ ጩቤ ጨበጠ! ከተስፋዬ ገ/አብ

አማረ አረጋዊ ከልብ የሚያደርሱ ቃላትን በመጠቀም ኢህአዴግን የሚገለባብጥበት ጊዜ አለው። የረቡእ ርዕሰ አንቀፅ የዚህ ምሳሌ ነው። ኢህአዴግን በሁለት ከፍሎ ያየዋል። ሙሰኛ ያልሆኑ፣ ለአገር አሳቢ የሚላቸው አሉት። እንዲህ ማለቱ ሚዛን ለመጠበቅ ይሆናል። ርግጥ ነው፣ እኔ ጨምቄ ያቀረብኩት የርእሰ አንቀፁን ቁንፅል አሳብ ነው። አማረ በርእስ አንቀፁ ኢህአዴግ በመጪው ጉባኤ ራሱን እንዲያፀዳ መክሮአል። የአማረ ምክሮችና የኢህአዴግ ጠንካራ ጎን ሆነው የቀረቡት አጃቢዎች ገለል ሲሉ የኢህአዴግን እውነተኛ ምስል የሚገልፀው ክፍል የሚከተለውን ይመስላል።

  • •          (የኢህአዴግ አመራር አባላት)… ከሕዝባዊ መስመር እየራቁና እየሸሹ ለግል ገንዘብ፣ ንብረት፣ ክብርና ኔትዎርክ የሚሯሯጡ፣ በጉቦ የተጨማለቁና በሙስና የተነከሩ አሉ፡፡ እነዚህ በውስጥ ትግል፣ በደፋርና በቆራጥ ትግል ካልተገለሉና ድርጅቱ ካልፀዳ ድርጅቱን እያበሰበሱ የሚገድሉት ናቸው፡፡
  • •          (ባለስልጣናትን) …በብቃት መመደብ እየቀረ፣ ‘ደጋፊ እስከሆነ ችግር የለም’ እየተባለ የተሾመው ሁሉ የድርጅቱን ዓላማ ማራመድ አልቻለም፡፡ ሕዝቡንም ማገልገል አልቻለም፡፡ ባለአቅም እየጠፋ ባለምላስ በዛ፡፡ ተንዛዛ በጣም በዙ፡፡ ሕዝብ ይህንን እያየና እያስተዋለ ‘ምንድን ነው ነገሩ?’ እያለ ነው፡፡ አይወስኑም፣ ቢሮ አይገቡም፣ አያሳምኑም፡፡ አንዳንዶቹም ይህን እያወቁ ሀቅን ከመጋፈጥ ይልቅ ሽሽትና ድብብቆሽ እየመረጡ ናቸው፡፡ ሕዝብ በድርጅቱ ላይ አመኔታ እንዲያጣ እያደረጉ ናቸው፡፡
  • •          (የኢህአዴግ አመራር አባላት) ….ራሳችንን አናታልል፤ የዓለም ሁኔታ ከሚጠይቀው አንድነትና መጠናከር ከሚጠይቀው መመዘኛ አንፃር ሲታይ ያለው አንድነት ጠንካራ አይደለም፡፡ ተደፋፍሮ መገማገም፣ ቆራጥና ደፋር ትግል አካሂዶ አንድነትን እውን የማድረግ ሁኔታ በአጠቃላይ በኢሕአዴግ፣ በተናጠልም በእያንዳንዱ ድርጅት እየታየ አይደለም፡፡
  • •          ጠንካራ አንድነት በሕወሓት ውስጥ አይታይም፣ ጠንካራ አንድነት በብአዴን ውስጥ አይታይም፣ ጠንካራ አንድነት በኦሕዴድ ውስጥ አይታይም፡፡ ጠንካራ አንድነት በደኢሕዴን ውስጥም አይታይም፡፡ እርስ በርስም ጠንካራ አንድነት እየታየ አይደለም፡፡ (ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎምህወሃት ውስጥ መካፋፈል አለ። ብአዴን ጎራ ለይቶአል። ኦህዴድ በቡድን ተለያይቶአል። ደኢህዴን ሲዳማና ወላይታ ብሎ እየተናቆረ ነው። በጥቅሉ የኢህአዴግ ጃንጥላ ተቀዶአል።
  • •          ልማት እየቆመ ነው፡፡ የፍትሕ ሥርዓት እየተደረመሰ ነው፡፡ መንግሥት በቂ ገንዘብ ማሰባሰብ እያቃተው ነው፡፡ በብዙ ቦታዎች ንብረትና ገንዘብ እየባከነ ነው፡፡ የሕዝብ ጉጉትና ምኞት በተፈለገው ፍጥነት እውን እየሆነ አይደለም፡፡
  • •          ሕዝብ መንግሥትን ለመደገፍ ጨዋነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን ለማሳየትና ለማረጋገጥ በእጅጉ ዝግጁ ነው፡፡ በሐዘን ጊዜም በጋራ እንደ አንድ ሰው አልቅሷል፤ አዝኗል፡፡ ጨዋነቱንና ኢትዮጵያዊነቱን በግልጽ ለዓለም አሳይቷል፡፡ በእግር ኳስ ደስታም ማንነቱን በየጎዳናው አሳይቷል፡፡ ያኮራል፣ እውነትም ወርቅ ሕዝብ፡፡ ግን… ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያዊያን ተንቀሳቀሱና ማንነታቸውን አሳዩ ማለት ከመሪው ፓርቲ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በአዎንታ አንፀባረቁ ማለት አይደለም፡፡ ፍትሕ ሲጠፋ አቤት የምንልበት ጠፋ፡፡ ወደ ሕዝብ ቀርቦ፣ ወደ ሕዝብ ወርዶ የሚያነጋግረን ሹም ጠፋ እያሉ ነው፡፡ ይህ ማለት ሕዝቡ የሚፈልገውን ግንኙነትና ትስስር እያገኘ አይደለም፡፡

 

Also: click here to read reporter’s editorial in amharic.

 

 

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on October 24, 2012. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.