ኑ! እንዋቀስ፤ ኢህአዴግንም እናፍርሰው! -ተመስገን ደሳለኝ

Journalist Temesgen Desalegn

Journalist Temesgen Desalegn

(ይህ “ኑ! እንዋቀስ” የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም) ኢህአዴግ ራሱ በይፋ ሲናገር እንደተደመጠው፣ በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ገደማ ደርሷል። ይህም የአገሪቱ ቁጥር አንድ ግዙፍ የፖለቲካ ፓርቲ ያደርገዋል። በርግጥ ግዙፍ እንጂ ጠንካራ እንዳላልኩ ልብ ይሏል። ምክንያቱም ጥንካሬ የሚለካው በአባላት ቁጥር ሳይሆን በድርጅት ፍቅር፣ በዓላማ ፅናትና በሚሰጡት ልባዊ አበርክቶ ነው።

እንዲህ ያለ አቋመ-ብርቱነት ደግሞ ድሮ በያ ትውልድ ጊዜ ቀርቷል፡፡ በዘመነ-ኢህአዴግ የተንሰራፋው ጥቅመኝነት (በእነርሱ ቋንቋ ኪራይ ሰብሳቢነት) ብቻ ነው፡፡ ለዚህም በደቡባዊቷ አዋሳ ከተማ ስድስተኛው የድርጅቱ ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት፣ አቶ በረከት ስምኦን በብስጭት እየተትከነከነ በደፈናው ለጥቅም ድርጅቱን የተቀላቀሉ አባላት በርካታ መሆናቸውን አምኖ በአደባባይ መናገሩ አስረጂ ሊሆነን ይችላል፡፡ ይህን ንግግሩንም አፍታተን ስናብራራው እንደሚከተለው ሆኖ እናገኘዋለን፡- የግንባሩ አባላት ቁጥር ሰባት ሚሊዮን ገደማ የደረሰው በጥቅም በመደለል፣ በአንድ ለአምስት የጥርነፋ መዋቅር በፍርሃት ተጠፍንጎ በመያዙና በመሳሰሉት ነው (መቼስ አቶ በረከት ከድርጅቱ ጉምቱ መሪዎቹ አንዱ ነውና ዘርዝሮ እንዲያስረዳን አይጠበቅበትም) Continue reading –>

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on March 25, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.