ነዳጅ የያዘ ቦቴ ተገልብጦ አደጋ ደረሰ (አስደንጋጭ ዜና)

አስደንጋጭ አደጋ (በጽዮን ግርማ)
(ኢ.ኤም.ኤፍ) እኛ ዘግይተን ስላቀረብነው እንጂ፤ ይህ አስደንጋጭ ዜና በጽዮን ግርማ በትላንቱ እለት የቀረበ ነው። ቢዘገይም ዜናውን ማካፈሉ አይከፋም በሚል የጽዮን ግርማን ሙሉ ዘገባ ከዚህ ቀጥሎ አቅርበነዋል።

የደረሰው የእሳት አደጋ በጣም የከፋ ነበር (ፎቶ በጽዮን)

የደረሰው የእሳት አደጋ በጣም የከፋ ነበር (ፎቶ በጽዮን)


ዜናውን ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ቄራ በጓዝ ላይ የነበረ ነዳጅ የጫነ የፈሳሽ ማመላለሻ መኪና ከነተሳቢውና ተሳፋሪ ጭኖ ከቄራ በኩል ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ታክሲ ሞሐ ለስላሳ መጠጦች ፋብሪካ(ፔፕሲ) ፊት ለፊት ራሳቸውን ከመጋጨት ለማትረፍ ባደረጉት ጥረት ተሳቢው ታክሲው ላይ ተገልብጦ በደረሰ ከፍተነኛ የእሳት አደጋ ሰዎች ተቃጠሉ።በአሁኑ ሰዓት የተቃጠሉ አስክሬኖች እየተለቀመ ነው።ተጎጂዎች ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው። አደጋው ከደረሰ አንድ ሰዓት ሆኖታል።
የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ተሳቢው ታክሲው ላይ በወደቀበት ቅጽበት ሚኒባስ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለማትረፍ ርብርብር የተደረገ ቢሆንም ተሳቢው ውስጥ የነበረው ነዳጅ በመፍሰሱ በድንገት ከፍተኛ እሳት ተነስቷል።በዚህን ጊዜ ሁሉም ራሱን ለማዳን መራወጥ ጀመረ።እንደምንም ከሚኒባሱ ውስጥ የወጡ ሰዎች እሳት እየነደደባቸው ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሞክሩ ታይተዋል። አደጋውን ተከትሎም በአካባቢው ወዲያው የደረሱ መኪኖች ተጋጭተዋል። አካባቢው በከፍተኛ ጭስ ታፍኖ ነበር።

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on May 11, 2014. Filed under Uncategorized. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.

2 Responses to ነዳጅ የያዘ ቦቴ ተገልብጦ አደጋ ደረሰ (አስደንጋጭ ዜና)

 1. ትዝብት

  May 12, 2014 at 3:59 AM

  ጉድ ነው!! እንዴት ነዳጅ የጫነ መኪና በከተማ መሃልና ብዙ ተሽከርካሪ ባለበት እንዲጓዝ ይደረጋል??? ይህን ቀላሉን ነገር ልማት አድጓል እያለ የሚያደ.ነቁረው ዘነጋ?? የጥፋት ትልዕኮው እየተጋለጠ ነው:: ይህ ጉዳይ አደጋ ለማስመሰል ሆን ተብሎ የተቀነባበረ የበረኽኛውና የአውሬው የኢህአደእግ ደህንነት ዓላማ ለማስቀየስ ያቀነባበረው ሴራ ይሆናል!!!!!!

  ኤግዚአብሄር ኢትዮጵያን ያስባት!!!!!!! ኣሜን!!!!!

 2. ab

  May 12, 2014 at 1:28 PM

  ከማውራት በፊት አገሪቱ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ማወቅ አለብን ዝም ብለን ባንቀባጥር ጥሩ ነው