ትግሉ ተጀመረ!

ኢህአዴግ የዴሞክራሲና የህግ የበላይነት ጥያቄ ሲቀርብለት ዘወትር የሚያሳው መቃብሩን ነው።የአንድነት ጥያቄ ሲቀርብ ምላሹ “እኛ ከፈለሰፍነው አንድነት ውጭ ሌላው አንድነት በኢህአዴግ መቃብር ላይ ካልሆነ በስተቀር የማይታሰብ ነው”የሚል ነው።የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ሲነሳ “የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ህያው የሚሆነው በኢህአዴግ መቃብር ላይ ብቻ ነው”በማለት ወደ መቃብሩ ያመላክተናል።አንቀፅ 39 በታኝ መሆኑን ህዝብ ሲገልፅ “የህዝብ ልጆች የተሰውለት የትግሉ የማዕዘን ድንጋይ ነው፣እኔ ካልሞትኩ በስተቀር”በማለት ለክቡር አላማ የተሰው ሰማዕታት አፅም ላይ ቆሞ ይዘምራል።ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ናት፣ላንተም ቢሆን የባህር በር ያስፈልግሃል ሲባል “ሞቼ ነው ቆሜ ኢትዮጵያ የባህር በር የሚኖራት”እያለ በማቅራራት መቃብሩን ያሳየናል።

የትምህርት ፖሊሲው አዲሱን ትውልድ እየበላው ነው ተብሎ ማሻሻያ እንዲያደርግ ሲለመን “የፍየል ወጠጤ”እያለ ይፎክራል፤መቃብር ያሳየናል።የግብርና ፖሊሲው ስህተት በመሆኑ ይታረም ሲባል “እህል ኤክስፖርት ማድረግ ጀምሬያለሁ፣የአርሶ አደሩ ህይወት ተለውጧል።እኔ ከሞትኩ አርሶ አደሩ ይራባል፣ይጎዳል፣እኔ ለገበሬው ተፈጥሬያለሁ።እኔ ከሞትኩ…”እያለ መቃብር ያሳየናል።በኢኮኖሚው መስክም ሲመከር “ሁለት ዲጂት እድገት አሳይቻለሁ።እኔ ከሌለሁ…”በማለት ወደ መቃብሩ ይጠቁመናል።በምርጫ ተሸንፈሃል ሲባል “ ኢንተርሃሞይ “ የርስ በርስ ጭፍጭፍ እያሳየ እኔ ከሌለሁ በማለት ትልቁን መቃብር ያመላክተናል።በጥቅሉ ኢህአዴግ መቃብርና ጉድጓድ ያላሳየበት ጊዜ የለም።ለውጡ የመቃብሩ መጠሪያ መቀየሩ ነው።ድሮ ኢህአዴግ ነበር አሁን አቶ መለስ ወይም የአቶ መለስ መቃብር ተብሎ መተካቱ ነው።

ከላይ በዘረዘርናቸው ጉዳዮችም ሆነ በሌሎች መስኮች ኢህአዴግ ምክርና ተግሳፅ ሲሰጠው ከመቀበል ይልቅ ‘’እኔ ከሌለሁ” በሚል መቃብሩን እያሳየ አገርም ህዘብም ክፉኛ እየተጎዱ ነው።መቃብር እያየን መቃብር ውስጥ እየገባን ነው።በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት “ፈሪ መንግስት ዘወትር የሚታየው መቃብር ነው።የሚማማለውም በመቃብር ነው”በወያኔ ጥላ ተለክተው የተሰሩት ልጥፍ ፓርቲዎችም መቃብራቸውን እያዩ አገር፣ልጅ ልጆቻቸው፣እነሱም የቁም ሞት እየሞቱ ነው።ግን እስከመቼ?የሚገርመው “እኔ በህይወት እያለሁ ለውጥም ሆነ መሻሻል አይታሰብም በማለት ስልጣን በያዘ ማግስት መቃብር ማሳየት የጀመረው ወያኔ/ ኢህአዴግ እሱ ባስቀመጠው የጫወታ ህግ መሰረት ወደ ሚመኘው መቃብሩ ሊሸኙት የተነሱትን የህዝብ ልጆች የፈጠራ ወንጀልና መረጃ እሰበሰበ፣ በፈጠራ ክስ፣ራሱ ፈራጅ ሆኖ ለስቃይ እየዳረገ መሆኑ ነው።ለመነሻ ይህን ካልን ወደ ዋናው የመግለጫችን ርዕስ እናምራ!

ዘወትር መቃብሩን እያሳየ የሚምለው ኢህአዴግ፣ባለፉት 20 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ “የሹም ዶሮ ነኝ…”እንዲሉ አገሪቱንና ህዝቦቿን ወደ መቃብር ከሚወረውር የአፈና ርምጃው ከማፈግፈግ ይልቅ ወደ መቃብሩ በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተግባራት ማከናወኑን ገፍቶበታል።እስር፣ቶርቸር፣የጅምላ ግድያ፣የመብት ረገጣና ንጹሃን ዜጎችን ማሳደዱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።አስገድዶ መድፈር፣የአገር ንብረት ማሸሽ፣ህፃናትን መሸጥ፣… በተግባር የምናየውና የምንሰማውም ፈር የለቀቀ የአምባገነናዊ ስርአት መገለጫ የሆኑትን ግብሮች ነው።

ህወሃት/ኢህአዴግየኢትዮጵያህዝብለመብቱናለነፃነቱቀንዓዊከመሆኑምባሻግርእነዚህየዕልውናውመሰረትየሆኑዕሴቶችተጠብቀውናተከብርውእንዲኖሩደረጃበደረጃመወሰድየሚገባውንእርምጃጠንቅቆየሚያውቅመሆኑንየዘነጋይመስላል።

የህዝቡንመብትለማስከበርበቡድንምሆነበተናጥልጥያቄየሚያነሳኃይልብቅሲልህወሃት/ኢህአዴግየማጥፊያሰይፉንመዞ”ህግመንግስቱንሊንዱ”፤”የህዝቡንሰላምሊያደፈርሱ”፤”ሽብርሊነዙ”…ወዘተእያለሲያስፈራራ፣ሲያስር፣ሲገድል፣ሲያሳድድይታያል።

ህወሃት/ኢህአዴግማስፈራሪያየሚያደርገውህገመንግስትየህዝብመብትማስከበሪያ፣ነፃነትማስጠበቂያመሣሪያሆኖካላገለገለእሱበጀመረውየ“አስቀድማችሁቅበሩኝ” ጥሪመሰረትመፍረሱአይቀሬመሆኑንየዘነጋውይመስላል።

ሕዝቦችመብታቸውንለማስከበርህይወታቸውንከመስጠትጀምሮሁሉንምዓይነትመስዋእትነትለመክፈልበቋፍላይናቸው።

በየትኛውምአጋጣሚህዝቦችከአምባገነኖችመንጋጋነፃለመውጣትያደረጓቸውትግሎች”ካልደፈረሰአይጠራም”እንዲሉሰላምደፍርሶከባሰደግሞደምፈሶመሆኑንተዘንግቶ፣ዛሬህወሃት/ኢህአዴግስለሰላምመከበርአቀንቃኝበመሆንየነፃነትትግልሂደትንየሰላምማደፍረስተግባርአድርጎየሚያላዝነው።

ያ!የሚፈራውየህዝቦችንቅናቄአፍጥጦሲመጣበትቀደምሲልጀምሮየኖረበትንየአደገኛአሸባሪነትባህሪውንይፋያወጣውራሱኢህአዴግነው።እውነትንበመፃፋቸውመአትእንዳመጡአድርጎያሰራቸውጋዜጠኛውብሸትታዬእናአምደኛርዕዮትዓለሙየህወሃት/ኢህአዴግውስጣዊርደትየፈጠረውየድንጋጤዕብደትሰለባዎችናቸው።“መቼነውቶርቸርየምታቆሙት?መቼነውማሰቃየትየምታቆሙት?መቼነውከኢትዮጲያህዝብጫንቃላይየምትወርዱት፣ህዝብጠልቷችዃል፣መሮታል፣አይፈልጋችሁም”በማለትባደባባይየጠየቁትንናኢህአዴግከፓርቲአምባገነንነትወደግለሰብአምባገነንነትተለውጦ፣አባላቱየጠቅላይሚኒስትሩንዙፋንከማስጠበቅናእሳቸውየተናገሩትንእንደበቀቀንከማስተጋባትየዘለለስራእንደሌላቸውየተናገሩትንየአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህፓርቲምክትልፕሬዝዳንትአቶአንዱዓለምአራጌ፣እዉቁጋዜጠኛእስክንድርነጋ፣የአንድነትለዲሞክራሲናለፍትህፓርቲብሄራዊምክርቤትአባላትአቶአሳምነውብርሃኑእናአቶናትናዔልመኮንን፣የመላውኢትዮጵያዲሞክራሲያዊፓርቲአባልዘመኑሞላ፣አንጋፋውየኪነትባለሞያውየሆኑትአርቲስትደበበእሸቱ፣

የኦሮሞሕዝብኮንግረስአመራርየሆኑትአቶኦልባናሌሊሣ:

በአዲስአበባዩኒቨርሲቲየእንግሊዝኛቋንቋመምህርየሆኑትናየኦሮሞፌደራላዊዴሞክራስያዊንቅናቄምክትልሊቀመንበርበቀለገርባየሚመሩትትግልህዝባዊመሆኑንእናከኋላቸውያሰለፉትንኃይልከቶውንምሊቋቋመውእንደማይችልያወቀውህወሃት/ኢህአዴግመሪዎቹንናቀላጤዎቹንአስሮበሀሰተኛክስ “አሸባሪናችሁ” ማለቱበጭንቀትየመንፈራገጡማሳያነው።

 የወገኖቻችንን እስር አምርረን የምንቃወምና ከእስር እንዲለቀቁ የበኩላችንን የምናደርግ ቢሆንም፣ ቀደም ሲል ሂውማን ራይትስ ዎችና ቢቢሲ፣በቅርቡ ደግሞ ዊኪሊክስ ይፋ ያደረገው የስርዓቱ ገመና፣የወያኔ አባላት ንጹሃንን አጉረው ከሚያሰቃዩበት ከማዕከላዊ ቶርቸር ማዕከል ሰራተኞች የወጣው የእማዋይሽ አለሙና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ላይ ሚፈፀመው ግፍ ምስክርነት እንደሚያስረዳውና እኛም ባለን መረጃ በእስር ቤት የሚፈፀመው አውጫጪኝ የሰብአዊ መብትን የሚጥስ፣ርህራሄ የጎደለው በመሆኑ የዜጎቻችን ደህንነት በጅጉ ያሰጋናል።

በአንድ ጀንበር ህግ እያዘጋጀ፣በህግና በአዋጅ ስር ተጠልሎ ወገኖቻችንን እያሰረና እአሰቃየ  ያለው ወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት አንዳንድ ባለስልጣኖቹ በተስፋ መቁረጥና በልዩ ጥበቃ ስር መሆናቸው የሚታወቅ ቢሆንም ሰርዓቱን በመቃወም ሊከፍሉት የሚገባውን ዋጋ አልከፈሉምና በደምና በወንጀል ከተጨማለቀው ስርዓት ጋር አብረው ከመጠየቅ እረሳቸውን እንዲያድኑ አበክረን እንጠይቃቸዋለን።ከታሪክና ከዓለም የቅርብ ቀናት እውነታ እንዲማሩም ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

አገሩን የሚጠብቅ፣ህዝብን የሚያከብር፣ለህግና ለስርዐት የሚገዛ፣የአገሪቱን ሃብት ባግባቡ የሚንከባከብ፣ለዲሞክራሲ መብቶች ተግቶ የሚሰራ፣በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት እየናፈቀን ስንት ትውልድ አለፈ።ህዝብ “አንቱ”የሚለው መንግስት እየተመኘ ስንት ዘመን ቆጠርን?ህዝብ “በቃ”ሲል “አሜን ”ብሎ የሚቀበል አገልጋይ መሪ እንደተመኘን ይኸው አለን።የምንመኘውና የገጠመን ተለያይቶ አገረም፣ህዝብም እየማቀቁ ነው።መገለጫው ፀረ ኢትዮጵያዊነት፣ፀረ ህዝብነት፣ፀረ አንድነት፣ፀረ ዴሞክራሲ፣ፀረ ፕሬስ፣ህዝብ ለሚፈልገው ሁሉ ፀር የሆነ ስርዓት እስከመቼስ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጦ ይዘፍናል?የወቅቱ አንድነት የሚሻ ጥያቄ ነው።

ይህ ፀረ ኢትዮጵያ ስርዓት የመንግስትነት ጠረኑ የጠፋ ለመሆኑ ምልክት እየታየ ነው።ዛሬ ባገራችን ህገወጥነት ነግሷል።ዛሬ ባገራችን ህግ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።ዝርፊያና አስገድዶ መድፈር ይፈፀማል።ባለስልጣናት ገንዘብ ያሸሻሉ።እስርና ቶረቸር ይበዛል።የሚፈሩ ተቃዋሚዎች ይታደናሉ።በርካታ ማጎሪያዎች ይከፈታሉ።የጦር መሳሪያ ሸመታ ይጧጧፋል።የፋይናንስ ፍሰት ይናጋል።ስራ አጥነትና ዝርፊያ ይስፋፋል።የሚበሉና የማይበሉ ህዝቦች መተያየት ይጀምራሉ።……….ወዘተ፤እንግዲህ ባገራችን ያልታየው የቱ ነው?ከያቅጣጫው የሚወጡት ሪፖርቶች ሁሉ የሚያረጋግጥልን ይህንኑ እውነት ነው።

የዚህ ሁሉ ድምር መጨረሻው ጥፋት ብቻ ነው።ወያኔ/ኢህአዴግ ዓላማው ጥፋት ቢሆንም ድርጅታችን የጋራ ንቅናቄ ላዲሲቷ ኢትዮጵያ ጥፋት ሳይከተል ከጎሳ ይልቅ ለሰብአዊነት ቅድሚያ እንስጥ በሚለው የፕሮግራሙ መሰረታዊ መርህ መሰረት መቃብራችንና መቃብራቸውን ከሚያሳዩን አምባገነኖች ኢትዮጵያን የማላቀቁ ሂደት ከመቼውም በበለጠ በቅንጅት እንዲቀጥል ጥሪውን ያቀርባል።ተሳታፊነቱንም ያረጋግጣል።

በሌላም በኩል በሊቢያ አምባገን መሪ ልጅ ቤት በሞግዚትነት እየሰራች የፈላ ውሃ ተደፍቶባት ለከፋ አደጋ የተዳረገችው እህታችን ሸዋዬ ጉዳይ ለተራ የፖለቲካ ገበያ ለማዋል የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁሉ አጥብቀን እንኮንናለን።የሸዋዬ የሌሎች ኢትዮጵያውያን ስደት ያገሪቱ ፖለቲካና የአቶ መለስ እኔ ብቻ አውቃለሁ ፖሊሲ ውጤት ነውና  ኢህአዴግ ለሸዋዬ ተሟጋች የመሆን ሞራሉም ሆነ ውክልናው እንደሌለው ለማረጋገጥ እንወዳለን።

እህታችን የደረሰባት አጥንት ዘልቆ የሚገባ ህመምና ስቃይ እያቃጠለን ሌሎችስ ብለን ለመጠየቅ እንገደዳለን።”ድረሱልን”ሲሉ የነበሩ ዜጎች የት ደረሱ?ስንቱ አገራቸው ገቡ?ስንቶች ሞቱ?ስንቶች የባህር ሲሳይ ሆኑ?ለህዝቡ የሚጨነቅ መንግስት የሚመልሰው ጥያቄ ነውና በሊቢያ ስለነበሩት ዜጎቻችን ለሸዋዬ ብቻ አልቅሰን ሌሎችን በሃሳብ ቀብረን ዝም የምንለው አይሆንም።በተለያዩ አረብ አገራት ብዙ ሸዋዬዎች ግፍ ደርሶባቸዋል።በርካቶች ተከራካሪ በማጣት ከነስቃያቸው አልፈዋል………..መገለጫችን በሆነው ስደት ጉዳይ ብዙ ብዙ ጣጣ አለ! ከፎቅ ላይ የተወረወሩ፣በእሳት የተቃጠሉ፣በተለያዩ እስር ቤቶች የተጣሉ፣ጤናቸው የታወከ፣ለቤተሰቤ ምንም ሳላደረግ በሚል ካገር እንደወጡ የጠፉ፣አሁን ደግሞ እሳት በሚነድባቸው በየመንናበሶሪያያሉት ወገኖቻችን ጉዳይእረፍት የሚነሳ ነውና አገር ወዳዶች የችግሩ ሰንኮፍ ላይ ማተኮር ግድ ይለናል።

በመግቢያው ላይ እንደተጠቆመው ወያኔ/ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ለውጥ የሚመጣው በመቃብሩ ላይ ብቻ እንደሆነ በመግለጽ በሰላማዊ ትግልና በሰላማዊ ታጋዮች ላይ ጦርነት ያወጀው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ነው።ከ20 ዓመት በፊት በልዩነት እንደማያምን አስረግጦ የተናገረው ዘረኛው የወያኔ መንግስት በመረጠው መንገድ ወደመቃብሩ ሲገፋ ብቻየን ለምን በሚል ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ላይ እየፈፀመ ያለው ዘግናኝ ስቃይ፣በአገራችን ላይ የወደቀው መከራ እንዲወድቅ ይበልጥ የሚያነሳሳ እንጂ ትግሉንም ሆነ የወያኔ/ኢህአዴግን ቀብር የሚያራዝም አይሆንም!! እንደውም ትግሉ ተጀመረ እንጂ!

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ

************************************************************************************************************

ለዚህ ደብዳቤ ምላሽም ሆነ ለተጨማሪ መረጃ ዋና ዳይሬክተሩን ለአቶ ኦባንግ ሜቶ (obang@solidaritymovement.org) በመጻፍ ወይም ድረገጻችንን (www.solidaritymovement.org) በመጎብኘት ለመረዳት ይችላሉ፡፡

Share Button
Disclaimer: We are not responsible for any losses or damages that may have caused by using our services. EMF declines all responsibility for the contents of the materials stored by users. Each and every user is solely responsible for the posts.
Posted by on September 19, 2011. Filed under COMMENTARY. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0. Both comments and pings are currently closed.